Diese Präsentation wurde erfolgreich gemeldet.
Wir verwenden Ihre LinkedIn Profilangaben und Informationen zu Ihren Aktivitäten, um Anzeigen zu personalisieren und Ihnen relevantere Inhalte anzuzeigen. Sie können Ihre Anzeigeneinstellungen jederzeit ändern.

Berhanu.tadesse

training on Kaizen and 5s

  • Loggen Sie sich ein, um Kommentare anzuzeigen.

  • Gehören Sie zu den Ersten, denen das gefällt!

Berhanu.tadesse

  1. 1. DOC/UPD ለየካ ክ/ከ ወረዳ 2 የደረቅ ቆሻሻ ሰብሳቢዎች ላዘጋጀው የDry waste management ስልጠና የተሰጠ ግብረ መልስ August 1 2014 1.The kaizen change for better አስተዳደር ፍልስፍናና አነስተኛ ቡድን ስርአት አመራር 2.Safety: - the condition of being safe prevent from harm during collecting waste 3.Dry waste management 4.5s organization with a particular notion of Sorting arrange in category of waste 5. How to improve their income by selling the waste matter after sorting the important waste materials in to category for recycling purpose. በሚል ጽንሰ-ሃሳብ የቀረበ ስልጠና፡፡ አሰልጣኝ አቶ ብርሃኑ ታደሰ
  2. 2. ቀን 3/8/14 ዓ.ም (DOC/UPD) ያዘጋጀውን ስልጠና አስመልክቶ የተሰጠ ግብረ መልስ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ የጽዳት ማህበራት ከ 3/8/24 እስከ 4/8/14 የተሰጠውን ስልጠና አስመልክቶ በአሰልጣኙ በአቶ ብርሁኑ ታደሰ አማካኝነት የቀረበ ግብረ መልስ፡፡ የተሰጠው የስልጠና አይነት 1. የሙያ ስነ ምግባር፡- የስነ ምግባራዊ ግዴታዎች በስነ ምግባር ደንብ (professional code of ethics) ምንነት  ሙያና የሙያ ክብርን የሚያጎድፉ ጉዳዮች ምነድናቸው?  የጽዳት ሰራተኞች ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን መሆን አለበት?  የጽዳት ሰራተኞች ከባልደረቦቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን መሆን አለበት?  የጽዳት ሰራተኞች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን መሆን አለበት?  የጽዳት ሰራተኞች ከአመራርና አስተዳደር አካላት ጋር ያለው ግንኙነት ምን መሆን አለበት?  የጽዳት ሰራተኞች ከማህበራቸው ህግጋት ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን መሆን አለበት?  የጠንካራ የስራ ባህል፣ ስራ ምንድን ነው ሳይሰሩ መኖር ጋር ተያይዞ ያለ ችግር፣ ስራን መናቅና አጉል ማማረጥ ስራ ክቡር መሆኑን የሙያ ስነ ምግባር ሙያ ምንድነው ራስን መቻል ያለው ጠቀሜታ፣ የቢዝነስ ጽንሰ ሃሳቦች፣ መሃበራቸውን እንዴት ሃሳብን በመለዋወጥ ገቢያቸውን ማዳበር እንደሚችሉ የሚያሳይ ሂደት፣ በሳምንት አንድ ጊዜ ከ 15፡30 ደቂቃ የማህበሩ ስብሰባ ቢካሄድ በ15 ቀን አንድ ቀን ከ 30 እስከ 1 ሰዓት የማህበራቶች ስብሰባ ቢያደርጉ ሃሳባቸውን መለዋወጥና ማህበራቸው የሚያጠናክር ሃሳብ በማመንጨት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን የሚያጠናክሩ መሆናቸውን ለዚሁም የተመረጠላቸውና በጥልቅ የተሰጣቸው 1. የkaizen change for better አስተዳደር ፍልስፍናናአነስተኛ ብድን ስርአት አስተደአደር ከመሃበራቸው አንጻር፤ የዩኒየን አመሰራረት ከወረዳ ሲጀምር 2. Safety:- the condition of being safe prevent from harm during collecting waste 3. Dry waste management 4. 5s, with a particular notion of Sorting arrange in category of waste 5. how to improve their income by selling the waste after sorting the important ones
  3. 3. ለእድገታቸው በስራቸው ላይ ያጋጠሟአቸው ችግሮች 1. የተጠራቀመ ቆሻሻ ገንዳ ላይ ካሰባሰብን በኋላ መኪና ቶሎ አይመጣልንም አድሎ አለ ለሌሎቹ ቶሎ ሲመጣ ለኛ ግን ይዘገያል የሚመጣልን በሳምንት ሁለት ጊዜ ነው ይህ ማለት ደግሞ በሳምንት 80(ሰማንያ ብር) ነው የምናገኘው ይህ ብር እንኳን ለቤት ኪራይ ሊሆነን ቀርቶ ለምግብ የማይሆን ነው፡፡ 2. አንድ አንድ ደንበኞቻችን ትክክል ያልሆነ ስራ እንድንሰራ ያደርጉናል ይኸውም የውሻ አር ሌሎች ሽንት ቤት መግባት ያለባቸውን የሰው አር እና የሰው ሽንት በሀይላንድ በማዳበሪያ ተሸክማችሁ ጣሉ እንባላለን፡፡ 3. በስራ ላይ ለሚደርስብን ጉዳት ማን ነው ካሳ የሚከፍለን እኔ ለምሳሌ ጠርሙስ ቆርጦኝ ከወር በላይ ተሰቃየሁ ማንም ሊረዳኝ አልቻለም፡፡ 4. የሼድ አገልግሎት ስለማናገኝ እቃዎቻችን ለጉዳት የተጋለጡ ናቸው፡፡ የሁሉም መሀበራት ችግር ነው የምንሰራበትን ማዳበሪያ ጨምሮ ለሽያጭ ያዘጋጀናቸውን ይሰርቁናል፡፡ 5. ገቢያችንን ለማሳደግ ያልቻልነው የሼድ አገልግሎት ስለማናገኝ ነው፡፡ሌቦች የሚሰርቁን ቆሻሻንም ገንዳዎች ላይ እየደፋን አይደለም ሁሉም ገንዳ ማስቀመጫ ሼዶች በፍርድ ቤት አስተያየት ነው፡፡ 6. የማህበሩ ስም ምሳና ዝናሽ የተባለ ማህበር ያቀረቡት ጥያቄ የምንሰራው ጫካ ነው፡፡ አንድ መሀበር ከ 700 እስከ 1000 አባወራ ይዞ የጽዳት ስራ ይሰራል ቢልም የኛ ግን 50 አባወራ አይሞላም በዚህ የተነሳ ደረቅ ቆሻሻ ስለሆነ አመድ ውሰዱ እንባላለን ከቆሻሻ እጥረት ገንዳ አይሞላም ስለሆነም ገቢ የለንም፡፡ በተጨማሪ የምናመላልስበት ጋሪ የለንም፡፡ 7. የሁሉም መሀበር ጥያቄ የሆነው ከስራ በኋላ የምንታጠብበት ሳሙና ቢኖረን የተሻለ ነው ስለሆነም ሳሙና እርዳታ ቢደረግልን ጥሩ ነው፡፡ 8. የሁሉም ጥያቄ የነበረው የተሰራው ሼድ ውስጥ አትግቡ እየተባልን ነው የተሰበሰበው ቆሻሻም መንገድ ላይ እየጣልነው ነው፡፡ 9. የሁሉም ጥያቄ የነበረው ቆሻሻ ከተሰበሰበ በኋላ መኪና መቶ አያነሳልንም ቆሻሻ ባብዛኛው ሀብት ነው ትሉናላችሁ የሰበሰብናቸውን ቆሻሻ ደጅ ላይ ስለሆነ የምናስቀምጠው የአውሬ መፈንጫ ነው የሆኑት ነዋሪዎች መግባት መውጣት እስኪያቅታቸው ድረስ፡፡ አስተያየት  በመሆኑም መሞላት ያለባቸው ነገሮች እነዚህም የተሰራው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ሼድ ተብለው የተገነቡት ለስራ (ለጽዳት ሰራተኞች) ክፍት ቢሆንላቸው፡፡ የሚሰራውም በወረዳው የጽዳት አስተዳደር አማካኝነት ሲሆን የመኪናን ምልልስ ፍትሀዊነትን ቢያረጋግጥላቸው የእኩል ተጠቃሚነታቸው ይጨምራል፡፡  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በወረዳው የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት አማካኝነት ለደንበኞቻቸው ማቅረብ ቢችሉ የተሻለ ነው፡፡ የተሰሩት የጽዳት ማስፋፊያ ሼዶች አገልግሎት እንዲሰጡ ቢደረግ በተጨማሪ ለሰርቴንግ በሚያመች ተጨማሪ ሁለት ወይም አንድ ቢጨመር የተሻለ ነው፡፡
  4. 4.  የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጋሪዎችና መሀበራቶቹ እኩል የመካፈል መብታቸውን ቢያረጋግጥላቸው ይኸውም በመመሪያቸው መሰረት እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ አንድ ማህበራዊ ከ 700- 1000 አባላት (አባወራና እማወራ) በመያዝ የቤት ለቤት ጽዳት ይሰራል ነው የሚለው ይህንንም ለማጠናከር በተጨማሪ በዩኒየን በማደራጀት እኩል ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይላል ነገር ግን ይህ አልተከናወነም፡፡ ከአሁን ወዲያ ከወረዳ ቢጀመር፡፡  ለጋሽ ድርጅቶች የድጋፍ በአቀፍአቸውን በማስፋት የአቅም ግንባት ስራን ጨምሮ ሰርተው ሲጨርሱ የምጸዳዱበት የሳሙናና ኦሞ ግዢንና መሀበራቱን ለማጠናከር የሪሳይክል ማሽነሪዎች ቢገዙላቸው የተሻለ ስራ መስራት ይችላሉ ለጽዳት የሚገዙላቸውን ሳሙናዎች ከጽዳት ስራ በኋላ በህብረተሰቡም ዘንድ ተቀባይነታቸውንና የሚደረግላቸው ማናቸውም ድጎማ በገቢያቸው ከማንኛውም ሰው ያነሱ እንዳይሆኑ ስለሚያደርግ የስራው ተወዳጅነትን ይጨምራል ስራውንም ጠልተው የሚወጡትን ሰዎች ይቀንሳል፡፡  የኢንሹራንስ ጥያቄን አስመልክቶ ጉዳት የሚደርስባቸው ሰራተኞች ጉዳቱን የፈጠረው አካል እንዲከፍል ቢደረግ ምክንያቱም ከስራ አደገኝነት ጋር ተያይዞ ጉዳት እየደረሰ ስለሆነ ቅድመ ዝግጅት ቢደረግ፡፡ ደረቅ ቆሻሻን በተመለከተ  በየመንገዱ መንገደኛው የሚጥልበት በየ 100ሜ ልዩነት ማስቀመጫ ቀላል የሆኑ እና ለመንገደኛው አመች የሆኑ ሳጥኖች ቢቀመጡ፡፡ በተጨማሪ ስራ አጥ ገቢ ማስገኛ ቢሆን፡፡  የደረቅ ቆሻሻ አስወጋጆች ከእነዚህ ሳጥኖች እያወጡ ወደ ትልቁ ገንዳ ይጨምራሉ፡፡  ይህም አንድ ገንዳ ለ 200-300 ሳጥኖች እና ለ 40-60 ቤቶች አወቃቀር ታሳቢ ተደርጎ እንዲቀመጥ ማድረግ  በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ አገልግሎት መስጫ ቤቶችን በተመለከተ የደረቅ እና የፍሳሽ አወጋገድ ችግር ስላለ በሚከተሉት መንገድ ቢዋቀር  ፍትሃዊ ክፍፍል እንዲኖር እና የገንዳዎችን መቆለፍ ለማስቀረት የመፍትሄ ሀሳብ (ሀ) የገቢ ምንጫቸው፡- በሚሰጡት አገልግሎት እንዲወሰን ማድረግ (ለማህበሩ ሙሉ ሀላፊነት መስጠት) ይህም ማህበሩ (እያንዳንዱ) በተወሰነ የቦታ ስፋት ውስጥ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶችን፣ሱቆችን እና ድርጅቶችን እራሳቸው ፕሮጀክት ነድፈው ኮንትራት በመያዝ ለተቋማት የተሟላ የጽዳት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እና ድርጅቶች የራሳቸውን የጽዳት ሰራተኛ ከመቅጠር ኮንትራት እንዲሰጧቸው እና በራሳቸው የገቢ ምንጭ የገንዳዎችን ግዢ አያያዝ እና ሌሎችን ሂደቶች እራሳቸው የሚያካሂዱ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡ (ለ) መኖሪያ ቤቶች፡- የመኖሪያ ግቢ ጽዳት በኮንትራት እንዲወሰዱ ማድረግ (ሐ) ለአገልግሎት ሰጭ ተቋሞች (ሽንት ቤት እና ደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ስላላቸው)
  5. 5. -ማህበሩ በአካባቢው ሽንት ቤት፣ሻወር እና ደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ በራሱ ወጭ በየአካባቢው ይገነባሉ ተጠቃሚው በገንዘቡ ይጠቀማል፡፡ ፈሳሽ ቆሻሻን በተመለከተ  በየ 100-200 ሜ እርቀት (መንገድ ላይ) በሳንቲም የሚሰሩ ሽንት ቤቶችን ይገጥማሉ፡፡ ማጠቃለያ  በወረዳው ያሉትን ማህበራት በጥልቀት ሁሉንም ያሉትን ነባራዊ ሁኔታ ማጥናት  የደረቅ ቆሻሻ ማስወገድ አገልግሎቱ በወረዳው ውስጥ ላሉ ህብረተሰቦች በአግባብ ለሁሉም መዳረሱንና የመጣውን ለውጥ (በበጎ) ወይም ያልተዳረሰ ከሆነ ያለውን ችግር መለየት፡፡  በወረዳው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ለመሀበራቱ የሚሰጠውን ድጋፍ በየሳምንቱ በማካሄድ ያሉትን ችግሮች መለየት (በክፍፍል፣በአወጋገድ፣ በሰው ሀይል ምደባ በመሳሰሉት) ያለውን ችግር በመፋታት ዙሪያ ትልቁን ድርሻ መወጣት አለበት  ከድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ጋር ያለውን ግንኙነት በወረዳው ጽዳት ከአ/ር ጽ/ቤት አማካኝነት እንዲጠናከር ማድረግ፡፡ የድጋፍ መአቀፍውን ለማህበራቱ ለራሳቸው እንዲደርስና ገቢያቸውን ለማጠናከር የሚያስፈልጋቸውን ግብአት የማሟላት ስራ ቢደረግ፡፡  የክ/ከተማው የመኪና አቅርቦት በቀረበው የቆሻሻ ሁኔታ (የገንዳ መሙላት ጋር የተያያዘ መሆን) የመረጃ ልውውጥን (ከወረዳው ጋር) በፍጥነት መሆን አለበት መሀበራቱ የከተማ ጫፍ ላይ ስላሉ ተጠቃሚነታቸው አናሳ ነው የሚሰበስቡት ቆሻሻ ለጅብ መጫወቻ በመሆኑ ገቢያቸው ቀንሷል፡፡  ዩኒየን በመፍጠር ረገድ በከተማ ደረጃ ያለው ኤጀንሲ በእቅድ ደረጃ ላይ ቢሆንም ወደ ተግባር ባለመግባቱ የማህበራቶቹ ተጠቃሚነት ፍትሃዊ ስላልሆነ በዩኒየን የሚደራጁበትን ሁኔታና ሁሉንም ማህበራት ተጠቃሚ ለማድረግ ለጋሽ ድርጅቶች ከጥናት ጀምሮ እስከ ተግባራዊነት ድጋፍ ቢደረግ Trainer: Berhanu Tadesse Coordinator Yonas Getachew

×