SlideShare ist ein Scribd-Unternehmen logo
1 von 205
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የመጽሐ ቅዱስ ጥናት
ለተተኪ መምህራን ደረጃ 2 ሥልጠና የተዘጋጀ
አራጋው ብርሃኑ
ሐምሌ 23/2009 ዓ.ም
ባሕር ዳር
• ሐምሌ 02ና ግንቦት 15 ስንክሳር የቱ
• የእግዚአብሔርን ድምፅ ከምንሰማባቸው ነገሮች ቀዳሚውና
ዋነኛው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
• ይህን የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት ደግሞ ፈቃደኛ ልብ
በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡
• በሌላ መልኩ ደግሞ “ጠርጥር ከገንፎም አለ ስንጥር”
እንዲሉ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ፈቃደኛ ልቡናችንን
ከፍተን (ሰጥተን) ስንሰማ ሌሎቹ ደግሞ በውስጥ ለውስጥ
የላኩብንን ስንጥር መለየት ይገባናል፡፡
• ይህ ካልሆነ ግን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉን
እንደሚችሉ የማንክደው ሀቅ ነው፡፡
መግቢያ
• አባቶቻችን የመጽሐፍትን ምንነትና ጠቀሜታ ተረድተው ቅዱስ እግዚአብሔር
በቅዱሳት መጽሐፍት የነገራቸውን ተግብረው እንዲያውም ከዚያ በላይ
(በትሩፋት፣ በገድል) ፈጽመው እግዚአብሔርን አገልግለውና አስደስተው
አልፈዋል፡፡
• ለእነርሱ ብቻ አይደለም ለእኛም እንዲደርሰን ብራና ፍቀው በቀለም ብቻ ያይደለ
በደማቸው ጽፈው፣ በዋሻ በፍሩክታ እየተሰደዱ በእሳት እየነደዱ
አቆይተውልናል፡፡
• በመሆኑም የእሳት ልጅ አመድ እንዳንባል ቅዱሳን በኖሩበት ሕይወት መኖር፣
የእነርሱንም ቅርስ መጠበቅ ኃላፊነት ሳይሆን ግዴታችን ነው፡፡
• ለዚህ ደግሞ አባቶቻችን የተማሩበትን፣ የኖሩበትን፣ እነርሱ ያገኙትን አምላካዊ
ስጦታ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን ልናውቀው፣ ልንረዳው፣ ልንጠብቀውና
ልንጠቀምበት ይገባል፡፡
• በመሆኑም በዚህ ሥልጠና የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም፣ ታሪክና ምንነት፣ ቀኖና፣
የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ምንነት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ባህል፣ አባባል፣ ትውፊትና
አዋልድ መጻሕፍትና ሌሎች ጉዳዮችን እንዳስስበታለን፡፡
• የጥበብና የእውቀት ሁሉ ባለቤት የጠመመውን አቅንቶ የጎደለውን ሞልቶ ቅዱስ
ቃሉን እንድንሰማ ፈቃዱ ይሁንልን የድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት አይለየን፡፡
ምዕራፍ 1 - የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ምንነት፣ ዓላማና ጥቅም
• የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከሌሎቹ ጥናቶች /Research/ ሁሉ የተለየ
ነው፡፡ ሌሎች ጥናቶች ጉድለት አለበት በሚሉት ጉዳይ ላይ ተነስተው
የራሳቸውን ጥረት ካደረጉ በኋላ በደረሱት ግኝት ወይም የዳሰሳ ውጤት
መሠረት የራሳቸውን አስተያየት (Recommendation) ወይም
መላምት (Hypothesis) ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
• የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንል ግን መጽሐፍ ቅዱስን መርምረን ይህ
እውነት ነው፣ ይህ ስህተት ነው አለያም ይህን እንቀበለው ይህን
አንቀበለው ይህ ደግሞ እንዲህ ቢሆን መልካም ነው የምንልበት ሂደት
አይደለም፡፡
• ይልቁንም እግዚአብሔር በገለጠልን መጠን ዝርዝር ዕውቀትና መረጃ
ለማግኘት ነው፡፡
1 - የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ምንነት፣ ዓላማና ጥቅም
የመጽፍ ቅዱስ ጥናት ያስተማረን ወይም አብነታችን ምንድን ነው?
1. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያስተማረን ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡- ይኸውም
ለምሳሌ ያክል ጥቂት እንመልከት
- የኤማሁስ መንገደኞችን በመንገድ በሚሄዱበት ጊዜ ሲከራከሩ ሰምቶ ከጠየቃቸውና
ከመለሱለት በኋላ ወቅሶም እንዲህ መጽሐፍትን ተረጎመላቸው አስጠናቸው፡፡
• ሉቃ 24.27 ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን
ተረጐመላቸው---እርስ በርሳቸውም በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን
ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ።
- ለሐዋርያትም ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በመጻሕፍት እንዲህ ተጽፏል እያለ
የመጽሐፍትን ነገር እየጠቀሰ ያስጠናቸውና ያስተምራቸው ነበር፡፡ ደግሞም በስልጣኑ
አስተማራቸው ይላል፡፡ በተለይም ከትንሣኤው በኋላ ከማረጉ በፊት መጻሕፍትን
ተርጉሞላቸዋል፡፡
• ማቴ 5.1-2 ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ
እርሱ ቀረቡ፤አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው
• ማር 2.13 ደግሞም በባሕር አጠገብ ወጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡና
አስተማራቸው፡፡
• ማቴ 21.13 ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ
አደረጋችኋት አላቸው
2. ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
አብነቶቻችን ናቸው
• ከክርስቶስ የተማሩ ሐዋርያት በኋላም ሐዋርያነ አበው
ሊቃውነተ ቤተክርስቲያን እና መምህራን ብዙ መጻሕፍትን
አጥንተው እውነቱን ከሐሰቱ ስንዴውን ከእንክርዳዱ ለይተው
መጻሕፍትን ከመጻሕፍት ጠቅሰው አራቀው ተምረው
አስተምረው አብነት ትተውልን አልፈዋልና አብነቶቻችን
ናቸው፡፡ ዕብ 13:7
2. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዓለማ ምንድን ነው?
• መንፈሳዊ ሕይወት የምንማርበትን መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሆነ
መቼ እንዴትና በማን እንደተጻፈ፣ በውስጡ ምን እንደሚገኝና
ከሌሎቹ ትክክለኛነቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ፤
• መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበትን ቋንቋ፣ ቦታ፣ የአጻጻፍና
የአተረጓጎሙን ስልት ለመረዳት፤
• የመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛው ቀኖና እንዴትና መቼ እንደተወሰነና
ከእኛም እንዴት እንደደረሰ ለመረዳት፤
• ባገኘነው ግንዛቤ ከበፊቱ በተሻለ አንብበንና ተረድተን በበለጠ
ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ፤
• በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ
ለመስጠት የተዘጋጀን እንድንሆን (1ኛ ጴጥ 3:15)
3. የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ስልት
• መንፈስ ቅዱስ ካላገዘ በቀር መጽሐፍ ቅዱስን በራስ ሐሳብና
ፍልስፍና መረዳት በእጅጉ አዳጋች ነው፡፡ በመሆኑም መንፈስ
ቅዱስን አጋዥ አድርጎ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት
የሚከተሉትን የጥናት ስልቶች ልንከተል እንችላለን፡-
• 3.1. መጠይቃዊ ስልቶችን በመጠቀም መጽሐፉ የተጻፈበትን
አለያም ቃሉ የተነገረበትን ሁኔታ መረዳት፡-
• ማን/Who/? ምን/What/? መቼ/When/?
የት/Where/? ለምን/Whay/? እንዴት/How/?
የሚሉትን የአንድን መጽሐፍ አለያም ቃል የተጻፈበትን
አለያም የተነገረበትን ሁኔታ ሊያስረዱ የሚችሉ መሠረታዊ
ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልጋል፡፡
3.2. የምንባቡን ሥነ ጽሑፋዊ የአጻጻፍ ባሕርይ መረዳት
• መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈባቸውን ከዚህ ቀጥለው የቀረቡ 4
ሥነ ጽሑፋዊ የአጻጻፍ ስልቶች መገንዘብ የተሸለ አረዳድ ሊሰጠን ይችላል፡፡
3.2.1. ትረካዊ የአጻጻፍ ስልት/Narrative Writing System/
• የብሉይም ይሁን የሐዲስ ኪዳን ብዙ መጻሕፍት በትረካዊ የአጻጻፍ ስልት ተዘግበው
እናገኛለን፡፡ ታዲያ ይህን ትረካዊ ስልት ተከትለን ስናጠና እንደ ታሪክ ብቻ አንብበን
የምንተወው ሳይሆን ብዙ አምላካዊ ምሥጢር ያላቸው መሆኑን ልናስተውል
ይገባል፡፡ በዚህ ከተጻፉ መጻሕፍት ውስጥ ለምሳሌ፡- መጽሐፈ ሩታ፣ የሐዋርያት
ሥራ፣ ሉቃስ ወንጌል ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡
3.2.2. ሥነ ግጥማዊ የአጻጻፍ ስልት/Poietic Writing System/
• ልበ አምላክ የተባለው ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ከጻፈው የመዝሙርና የቅኔ
መጽሐፍ ብንነሳ የተጻፈው በግጥም መልክ ነው፡፡ ነገር ግን ሰው በሌለበት ጊዜ ሰው
ሆኖ የተገኘውን መዝሙረኛውን ዳዊት ቅድመ አምላክነቱን፣ ልደቱን፣ ስደቱን፣
መከራውን፣ ስቅለቱን፣ ትንሣኤውን፣ ዕርገቱን እንዲሁም ዳግም ምጽአቱን
ተናግሮበታል፡፡ ለዚህስ አይደል እንደልቤ ያለውስ፡፡ እንዲያውም እነዚህን መጽሐፍት
ስናጠና የተጻፉበትን ጥበባዊና ምሳሌያዊ፣ ቅኔያዊና መዝሙራዊ ምሥጢር ልንረዳ
ይገባል፡፡ በብሉይ ኪዳን በዚህ መልክ የተጻፉ መጽሐፍት 8 ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
3.2.3. ትምህርታዊ የአጻጻፍ ስልት/Didactic Writing System/
• በዚህ ስልት የተጻፉት ደግሞ አብዛኛው ትኩረታቸው መሠረታዊ ትምህርተ
ሃይማኖት/Dogmatic/፣ ሥርዓተ እምነት፣ ትውፊት/Tradition/ና
ትንቢታዊ መልእክት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የቅዱስ ማቴዎስና ዮሐንስ ወንጌል፣
የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት፣ ትንቢተ ኢሳይያስ ወዘተ
3.2.4. ራእያዊና ሕልማዊ የአጻጻፍ ስልት/Apocalyptic Writing System/
• መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈባቸው ስልቶች መካከል ጠንከር ያለውና ጥልቅ
አረዳድን የሚጠይቀው ይኸው የአጻጻፍ ስልት ነው፡፡ ይህ ስልት በቀጥታ
ከሚናገሩትና ከሚያስረዱት በላይ ምሥጢር አዘል ስለሆኑና አንዳንዶቹ ደግሞ
ለወደፊት የሚፈጸሙ ጭምር ያለባቸው መሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ ያክል ራእየ
ዮሐንስን ብንወስድ ሊቃውንተ ቤተክርስቲን ይህን መጽሐፍ ለመተርጎም ወደ
ሰባት የሚደርሱ የትርጓሜ መንገዶችን እንደተከተሉ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ራእየ ዮሐንስን በተረጎመበት መጽሐፉ ገልጦልናል፡፡
• በራእያዊና ሕልማዊ የአጻጻፍ ስልት ተጽፈው ከምናገኛቸው መጻሕፍት ውስጥ
ትንቢተ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል፣ ኢዩኤልና ራአየ ዮሐንስ ይጠቀሳሉ፡፡
3.3. የመጽሐ ቅዱስን የአጻጻፍ ይዘትና የቋንቋ ጠባይዓት መረዳት
3.3.1. ሕዝባዊ ነው/Popular/
• ይህም ማለት መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ቀድመው የነበሩትን፣ አሁን ያሉትንና
ለወደፊትም የሚኖሩትን የህብረተሰብ ክፍሎች(ሕዝብ) በሚያጠቃልልና ሁሉን ዓቀፍ
በሆነ ቋንቋና ይዘት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ክፍል እኔን አይመለከትም ማለት አይቻልም፡፡
3.3.2. ክስተታዊ ነው
• እግዚአብሔር ነገሮችን የሚገልጥበት ክስተታዊ ሁኔታ አለው፡፡ ይህም ቋንቋው በቀጥታም
ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚገልጠው ነገር ጋር ይዛመዳል፡፡ ይህ ክስተታዊ አገላለጽ ግን
በማስተዋል ካልተረዳነው ትርጉም ላይሰጠን ይችላል፡፡
• ለማሳሌ፡- ማቴ 10:42 ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ
መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም። ይህንን
ለመረዳት ጽዋ ውኃ ምንድን ነው፣ ለምንስ በጽዋ ውኃ አለ ብለን ካልተገነዘብነው እንደ
ቀላልና ተራ ነገር ልንመለከተው እንችላለን፡፡
3.3.3. ኢ-ሳይንሳዊና ኢ-ንድፈ ሐሳባዊ ነው/Non-scintific and Non-theoretical/
• መጽሐፍ ቅዱስ የአንድን ነገር እውነተኛ ባሕርይ በንድፈ ሐሳብ/Theory/ ደረጃ ብቻ
አያስቀምጥም በሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ ጥበብ ብቻም አይገልጥም ከዚህም በላይ
የመለኮታዊ ባሕርይ መገለጥን ይከተላል እንጅ፡፡ ስለሆነም አጻጻፉ ኢ-ሳይንሳዊና ኢ-ንድፈ
ሐሳባዊ ነው፡፡
3.4. መጽሐፍ ቅዱስን በዐውደ እይታ የማጥናት ስልት
• ዐውደ እይታ ወይም ዐውደ ምንባብ ማለት አንድን የተጻፈ ቃል ወይም ዐረፍተ ነገር
ከመድረሱ በፊትና በኋላ በዙሪያው ያሉ ዐረፍተ ነገሮች ወይም አንቀጾች ናቸው፡፡ ይህ ዘዴ
መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ የሚቃረን አድርገን እንዳንወስድና ትክክለኛውን ትርጉም
ለማወቅ የሚረዳን የአጠናን ስልት ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-
3.4.1. ሥነ-ጽሑፋዊ ዐውደ እይታ ያጠናን ስልት፡-
• በምንባቡ ክፍል ዙሪያ የተገለፁትን አጠቃላይ ሥነጽሑፋዊ ሁኔታዎች ወይም ድርጊቶች
ወይም ሐሳቦች ማለት ነው፡፡ የቃል ዐውደ እይታ ዐረፍተ ነገር፣ የዐረፍተ ነገር ዐውደ እይታ
አንቀጽ፣ የአንቀጽ ዐውደ እይታ ምዕራፍ ፣ የምዕራፍ ዐውደ እይታ መጽሐፍ፣ የመጽሐፍ
ዐውደ እይታ መላው መጽሐፍ ቅዱስ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሉቃ 10:30 አንድ ሰው
ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ የሚለውን ለመረዳት የኢየሩሳሌምንና የኢያሪኮን ምንነት
መረዳት ያስፈልጋል፡፡
3.4.2. ሥነ መለኮታዊ ዐውደ እይታ
• የመጽሐ ቅዱስን ሥነ መለኮታዊ እይታ ካልተረዳን ምሥጢሩን ላንረዳ ብሎም ምሥጢርን
ልናፋልስ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ የዮሐንስ ወንጌልን ለመረዳት የመለኮታዊ ባሕርይን መረዳት
ተገቢ ነው፡፡ በመጀመሪያ ቃል ነበር የሚለውን ለመረዳት የቃልን ቅድምና ካላወቅን ቃል
በሚለው ብቻ ከሄድን አአትሪኮን፣ በርፎሪኮን እና አተርግዋን የሚባሉ ዝርዋን ቃላት አሉና
ገደል ይከተናል፡፡
• በማቴዎስ ወንጌል የተገለጸውን በግራና በቀኝ መቆም፣ ፍየልና በግ ወዘተ የመለኮታዊ
ባሕርይን ካልተረዳን ወደተሳሳተና ትርጉም ወደሌለው አረዳድ ይወስደናል፡፡
3.5. በአገላለጽ ወይም አባባል የሚታዩ የትርጉም ልዩነቶችን
የማጥናት ስልት
• መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ የሆነ አገላለጽና አባባል ያለው የራሱ
የሆነ የቃላት አጠቃቀምና የቋንቋ ሥርዓት አለው፡፡
3.6. የሐሳብ አንድነትንና የምሥጢር መስማማትን በጥንቃቄ
የማጥናት ስልት
• በመጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ጉዳይ ላይ በተለያየ አገላለጽና
ሊጋጩ በሚመስሉ ሁኔታ የቀረቡ በምሥጢርና በሐሳብ ግን
የማይለያዩ ብዙ አገላለጾች አሉትና ይህንም በጥንቃቄ
ማጥናት ተገቢ ነው፡፡
ምዕራፍ 2 - የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉምና ቅዱስነት
2.1. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ?
• መጽሐፍ ቅዱስ “መጽሐፍ” እና “ቅዱስ” ከሚሉ ሁለት
ቃላት የተገኘ ጥምር ቃል ሲሆን “መጽሐፍ” በአንድ ጥራዝ
ሥር የተሰበሰበ ጽሑፍ ሲሆን “ቅዱስ” የሚለው ደግሞ
በዕብራይስጥ ክዳሽ፣ በሱርስት ካዲሽ፣ በግዕዝና ዐረብኛ
ቅዱስ፣ የሚል ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ በጠቅላላው ደግሞ
በግሪክኛ ቢብሎስ(Byblos)፣ በላቲን
ስክሪፕቸር(Scripture) የሚል ስም ይሰጡታል፡፡
• በአጠቃላይ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ደግሞ የተለየ፣ የከበረ፣
የተቀደሰ መጽሐፍ ወይም ጽሑፍ ጥራዝ ማለት ነው፡፡
2.2. መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ዓላማ
1. የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም የፈጠረ እግዚአብሔር መሆኑንና ዓለምን ከመፍጠሩ
በፊትም በክብር በአንድነት በሦስትነት መኖሩን እንድናውቅ
• ዘፍ 1:1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
• ዘፍ 1:26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር
• ዮሐ 1:1-4 በመጀመሪያ ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም
እግዚአብሔር ነበረ ይህም በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥
ከሆነውም ሁሉ ያለ እርሱ ምንምን የሆነ የለም።
• መዝ 134:6 በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን
ሁሉ አደረገ።
• ዳን 4:35 በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ በሰማይም ሠራዊት
በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል እጁንም የሚከለክላት ወይም።
ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም።
• ዮሐ 10:17-18 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ
በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም
ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።
2. እግዚአብሔር እርሱ ብቻ አምላክ እንደሆነና እርሱን ብቻ እንድናመልከው
• ዘጸ 10:2 እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ
• ዘጸ 20:2-3፣ ዘዳ 5:6-7 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ
እኔ ነኝ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
3. የእግዚአብሔርን ባሕርይና ዘላለማዊ ፈቃድ አውቀን በፈቃዱ እንድንመራ
• ሮሜ 15:4 የተጻፈው ሁሉ በመታገሳችንና መጻሕፍትን በመታመናችን ተስፋችን እናገኝ
ዘንድ እኛ ልንማርበት ተጻፈ
• ሮሜ 8:24-25 የሚታየውን ተስፋ ማድረግ ተስፋ አይደለም የማይታየውን ተስፋ ብናደርግ
ግን እርሱን ተስፋ አድርገን በእርሱ እንደጸናን መጠን ትዕግስታችን ይታወቃል
• ሮሜ 8: 12-14 ወንድሞቻችን ሆይ አሁንም በሥጋችን ሳለን እንደሥጋ ፈቃድ እንኖር ዘንድ
አይገባም እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞታላችሁ ነገር ግን በመንፈሳዊ ሥራ የሥጋችሁን
ፈቃድ ብትገድሉ ለዘላለም ሕይዎት ትኖራላችሁ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚሠሩ ሁሉ
የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡
• ማቴ 22:37-39 ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም
ውደድ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥
እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት
• ዮሐ3:16-17 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ
እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ዓለም በልጁ
እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
4. ሥጋን ለብሶ የተገለጠው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምነን
በስሙም ዘላለማዊ ሕይዎት እንድናገኝ
• ዮሐ 20:31 ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ
ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ
ተጽፎአል።
5. እግዚአብሔር ኃጢአትን እንጂ ኃጢአተኞችን እንደማይጠላ በንስሐ ወደ
እርሱ ከተመለስን ከኃጢአታችን ሁሉ እንደሚያነጻን እንድናውቅ
• ማቴ 11:28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ፤ ሉቃ 15:7
ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ
በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል
6.በተዋሕዶ ዓለምን የማዳኑን ድንቅ ሥራ ለማሳወቅና ለማስገንዘብ
• ዮሐ 1:14 ቃልም ሥጋ ሆነ
• ገላ 4:4 ቀጠሮው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴቲቱም
ተወለደ
7. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ማረጉን ማስረዳትና ዳግም
ለፍርድ የሚመጣ መሆኑን ማሳወቅ
• መዝ 46:5-6 እግዚአብሔር በእልልታ ጌታችንም በመለከት
ድምፅ ዐረገ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ ዘምሩ ለንጉሣችን
ዘምሩ
• ሉቃ 24:51 እየባረካቸውም ራቃቸውም ወደሰማይም ዐረገ
• ሐዋ 1:9-11 እነርሱም ወደ እርሱ እያዩ ወደ ሰማይ ዐረገ፤
ከዓይናቸውም ተሠወረ እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ለምን
ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ወደ
ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል
• ማቴ 24ና 25 ስለዳግም ምጽአትና ፍርዱ በስፋት ይናገራል
2.3. የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርያት
• መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሕልውናውንና ፈቃዱን
ረቂቅ ባሕርይውን በመጠኑ የምንረዳበት፣ አምላክ ቅዱስ
ፈቃዱን የገለጸበት መጽሐፍ ነው፡፡
• መጽሐፍ ቅዱስ በባሕርይው ቅዱስ ነው፡፡ ቅዱስ የሚል
ባሕርይ ስንሰጠውም ያለምክንያት አይደለም፡፡
• ስለሆነም፡-
1. አስገኝው እግዚአብሔር ስለሆነ፤ የእግዚአብሔር የሆነ ደግሞ ቅዱስ ነው
• ኢሳ 34:16 በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም
• ዘጸ 17:14 ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው
• ራእ 1:11 የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ --- በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት
ላክ አለኝ
• ዘሌ 19:2 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ
2. በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሣሱ ቅዱሳን ሰዎች የጻፉት በመሆኑ ቅዱስ ነው
• 2ኛ ጴጥ 1:20-21 ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ
ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን
በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ
• ራእ 1:11 የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ --- በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት
ላክ አለኝ
• ራእ 22:8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ
• ነቢያት ሲጽፉ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል
መጣ፣ እንዲህ በል አለኝ እያሉ ይጽፉ ነበር (ኢሳ ምዕ 30 - 66፤ ኤር ምዕ 1 - 14)
• ጸሐፍቱ ከተለያየ የኑሮ ሁኔታና እውቀት ደረጃ የተጠሩ መሆኑም
ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡
• ይኸውም፡- ነቢዩ ሙሴ በምድያም የአማቱን(የኢትዮጵያዊውን
ዮቶር) በጎች ሲጠብቅ የተጠራ ነው፣ ነቢዩ ዳዊት የአባቱን በጎች
ሲጠብቅ፣ እንደነ ነቢዩ ሳሙኤል፣ ጠቢቡ ሰሎሞን፣ ካህኑ ዕዝራ
ያሉ ጥበበኞችና ተመራማሪዎች፣ እንደነ ነህምያ ያሉ ጠጅ
አሳላፊዎች፣ እንደነ ሉቃስ ያሉ ሐኪሞች እንደነ ቅዱስ ጳውሎስ
ያሉ ምሁረ ኦሪት ግን አሳዳጆች፣ እንደነ ጴጥሮስ፣ እንድርያስ፣
ዮሐንስና ያዕቆብ ያሉ ዓሣ አጥማጆች ወዘተ ተነስተው የጻፉት
በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጅ በሰው ሐሳብና ፈቃድ አይደለም፡፡
• - ከዚህም በተጨማሪ መጻሕፍቱ በተለያየ ቦታና ዘመን
መጻፋቸው ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መግለጻቸው
የመጽሐፍ ቅዱስን ቅድስና ያስረዳሉ ያረጋግጣሉም፡፡
3. የሰውል ልጅ ከመፈጠሩ በፊት ስላለው ነገር በእርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ
• ዘፍ 1:1 “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን
ፈጠረ” አለ እንጂ ፈጥሮ ይሆናል፣ የፈጠረ ይመስለኛል
አላለም፤ ነቢዩ ሙሴ ይህን የጻፈው 3800 ዓ.ዓ (ቅ:ል:ክ
1700/1300 የሚሉም አሉ/ በፊት ነው) ይህም ዓለም
ከተፈጠረ ከብዙ ዘመን በኋላ ጻፈው፡፡
• ዘፍ 12:1 እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ
ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ
ምድር ውጣ፤ አብርሃም ከሙሴ በፊት ብዙ ዘመናት
ይቀድማል ሙሴ ግን በዚያ ዘመን እግዚእብሔር ስለተናገረው
ነገር በወቅቱ እንደነበረ አድርጎ አስረግጦ ተናገረ፡፡
4. ወደፊት ስለሚሆነው በእርግጠኝነት በመናገሩ
• ኢሳ 7:14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል
ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ
ትጠራዋለች
• ራእ 1:7 እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል
• ራእ 22:7 እነሆም፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል
የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ
5. ሰውን ወደ ቅድስና የሚመራ በመሆኑ
• ራእ 22:7 የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ
• ሉቃ 11:28 ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት
ናቸው
• ሮሜ 10:17 እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል
ነው
6. የሚያነቡትንና የሚሰሙትን ስለሚባርክ
• መዝ 118:103 ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ
• ራእ 1:3 ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን
የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው
• 2ኛ ጢሞ 3:16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥
የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት
በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
7. ክብረ ቅዱሳንን የሚዘክር(የሚናገር) በመሆኑ
• መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ስለቅዱሳን መላእክት፣ ጻድቃን
ሰማዕታት፣ ስለ ቅዱሳት ንዋያት ወዘተ ይናገራል፡፡
• ሉቃ 1:19 እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ
• ሉቃ 1:26-27 በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ
ከተማ፥ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል
ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ
• መዝ 33:7 የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል
• መዝ 33:17 ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው
8. ዘመን የማይሽረው በመሆኑ
• መጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ መጻሕፍት ብሉየ መዋዕል ሲሆን ዘመን የማይሽረው ብቸኛ መጽሐፍ ነው፡፡
• ኢሳ 40:8 የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች
• ማቴ 24:35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም
• 1ኛ ጴጥ 1:25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል
2.4. የቅዱሳት መጽሐፍት የእግዚአብሔር እስትንፋስነት
• መጻሕፍተ አምላካውያት የእግዚአብሔር እስትንፋስ ናቸው፡፡
እንዲሁም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉን የፈጠረ የእግዚአብሔር
ቃል ነውና እርሱም ክቡርና ከፍጡር ሐሳብም ከፍ ያለ ነው፡፡
ሳዊሮስ ዘእስሙናይ
• ራእ 1:11 የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ --- በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ
አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ
• ራእ 22:8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ
• ነቢያት ሲጽፉ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ
እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ እንዲህ በል አለኝ እያሉ ይጽፉ ነበር (ኢሳ ምዕ
30 - 66፤ ኤር ምዕ 1 - 14)
• ኢሳ 3፡15 የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና---
• ኢሳ 38፡4 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ ---
• ኤር 1፡4 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ ----
2.5. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥቅም
1. እግዚአብሔርን የበለጠ ለማወቅና ለመቀደስ
• ዮሐ 5:39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን
ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤
• ዮሐ 17:17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።
• ኤፌ 5:26 በውኃ ጥምቀትና በቃሉ ይቀድሳት ዘንድ
2. ክፉንና በጎን ለመለየት
• መዝ 118:100 አስተዋይ ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ
• መዝ 118: 105 ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው
• መዝ 118:11 አንተን እንዳልበድል ቃልህን ሰወርሁ
• 2ኛ ጢሞ 3:16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን
ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም
ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።
3. በሥራ መከናወንን ለማግኘት
• ኢያሱ 1:8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና
ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል
ይከናወንልሃልም።
4. እውነትን ለማወቅ
• ምሳ 22:19-20 እምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ለአንተ ዛሬ እነሆ
አስታወቅሁህ። የእውነትን ቃል እርግጥነት አስታውቅህ ዘንድ፥ ለሚጠይቅህም
እውነትን ቃል መመለስ ይቻልህ ዘንድ፥ በምክርና በእውቀት የከበረን ነገር
አልጻፍሁልህምን?
5. እግዚአብሔር የገባልንን ርስት ለመቀበል
• ሐዋ 20:32 አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ
መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።
• ያዕ 1:25 ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥
ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ
ይሆናል።
6. መንፈሳዊ ውጊያ ለመዋጋት
• ኤፌ 6:10-18 በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ
የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር
ሁሉ ልበሱ።…የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም
የእግዚአብሔር ቃል ነው።
7. የጥበብ ሥጋዊና ጥበብ መንፈሳዊ(የሁሉ) ምንጭ መሆኑን ለመረዳት
• የሃይማኖት(ይሁ ቁ: 20፣ 2ኛ ጢሞ 4:7፣ 1ኛ ቆሮ 16:13)፣ የሥነምግባር(ዘጸ
20:7-17፣ ማቴ 5:20፣ ያዕ 2:17)፣ የሥርዓት(መዝ 118:118፣ 1ኛ ተሰ 5:14፣
2ኛ ተሰ3:6)፣ የሕግ(ዘጸ 20:12-17፣ ማቴ 22:34)፣ የሥራ አመራር(ዘጸ 18:13-
27)፣ የሥራ(ዘፍ 2:15፣ 2ኛ ተሰ 3:8-10)፣ የሕክምና(ዘፍ 50:2፣ ኤር 8:22፣ 2ኛ
ዜና 16:12፣ 2ኛ ነገ 20:7፣ ኢሳ 38:21፣ ማር 5:26፣ ቆላ 4:14 )፣ የግብርና(ዘፍ
42፣ 9:20፣ 21:33፣ 1ኛ ነገ 19:19)፣ የከብት እርባታ(ዘፍ 4:2፣ 12:5፣ 13:5-
8፣ 30:29፣ 46:31-32፣ 1ኛ ሳሙ 16:11)፣ የንግድ(ዘፍ 37:30፣ 33:19፣ 1ኛነገ
10:14፣ ሕዝ 27:1-25፣ ሐዋ 16:13-15)፣ የምህንድስና(ዘፍ 6:13-18፣ ዘጸ
25:21፣ ዘጸ 31:1-11)፣ የአናጺነት(ሕዝ 40:3፣ ራእ 21:15፣ 1ኛ ቆሮ 3:10፣
2ኛ ዜና 1:3-14፣ 7:11፣ 34:11)፣ የግንበኝነት (ዘፍ 11:1-9)፣ የአንጥረኛና
ቀጥቃጭነት (ዘኁ 31:21-23፣ ዘጸ 31:1፣ 36:1)፣ የልብስ ሠሪ(ዘጸ 35:25-35)፣
የሸክላ ሠሪ(ዘጸ 1:14፣ ኢሳ 41:25፣ ማቴ 27:7፣ ኤር 18:3፣ ሮሜ 9:21)፣
የቁርበት ፋቂ(ሐዋ 9:43)፣ የገድላት(ማቴ 23:35፣ ዕብ 11:4፣ ዳን 3:1፣ ሐዋ
7:54-60)፣ የተአምራት(2ኛ ነገ 6፡17፣ ዮሐ 2፡1-11፣ ሐዋ 14፡8-13፣ ሐዋ
5፡15-16)፣ የድርሳናት(ሉቃ 1:3፣ ሐዋ 1:1) ሁሉ መሠረት ነው፡፡
3.1. የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ዳሰሳና አከፋፈል
መጽሐፍ ቅዱስ
ብሉይ ኪዳን
/46/
የሕግ /5/
የታሪክ/17/
የመዝሙርና የጥበብ/8/
የትንቢት/16/
ሐዲስ ኪዳን
/35/
የወንጌል/የምሥራች/
/4/
የታሪክ /1/
መልዕክታት
/21/
የሥርዓት /8/
የትንቢት/የራእይ/
/1/
ምዕራፍ 3 - የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት
3.2. ሁለቱ ኪዳናት
3.2.1. የኪዳንና የቃል ኪዳን ትርጉም
• ኪዳን ማለት፡- “በተለያዩ ወገኖች መካከል የሚደረግ ውል፣ ቁም ነገር፣
የፍቅርና የአንድነት፣ ማሓላ፣ ሰላማዊ ሕግ፣ ሁለቱን ወገን አንድ
የሚያደርግ፣ ስለረብና ስለጥቅም በተስፋ የቆመ የተጻፈ ሥርዓት፣
ቢያፈርሱት ጉዳትና ጠብ የሚያመጣ ጥቅም የሚያሳጣ” ማለት ነው፡፡
/አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ /
• ኪዳን ስምምነት ሲሆን ቃል ኪዳን በቃል የተገባ ስምምነት ማለት ነው፤
• ቃል ኪዳን በብሉይ ኪዳን ወደ 280 ጊዜ በሐዲስ ኪዳን 33 ጊዜ ተጠቅሷል፤
• ቃል ኪዳን በሁለት ወይም ከሁለት በላይ በሆኑ ወገኞች መካከል የሚደረግ ስምምነት
ነው፤
• ይህ ውል/ስምምነት/ ሁለቱ ወገኖች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስረዳ ነው፤
• ለኪዳን የሚያስፈልጉ አካላት፡-
• ውል ሰጭ(መሐላውን የማለ) ቃል ኪዳን የገባ
• ውል ተቀባይ(የተማለለት) ባለ ቃልኪዳን
• ውሉ(መሐላው)
• ምልክት
በስምምነቱ ወቅት የቃል ኪዳንን የማጽደቅ ሒደት ያስፈለገው
1. ቃል ኪዳኑን የሚቀበሉት ተስፋው ተጨባጭ እንዲሆንላቸው፤
• 2ኛ ቆሮ 5፡5 የመንፈሱን መያዣ ሰጠን
2. ቃል ኪዳን እንዳያፈርሱ ለመጠበቅ
• መዝ 88፡34-35 ኪዳኔንም አላረክስም፥ ከከንፈሬም የወጣውን አልለውጥም፤
ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ።
3. ሁለቱም ወገን ማድረግ የሚገባቸውን ለማሳየትና
በፍቅርና በሰላም እንዲኖሩ፤
4. አንዱ ለሌላው ሊያደርገው ያሰበውን መልካም ነገር
ለመግለጥ፤
የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን ቃል ኪዳንን ንጽጽር
• የብሉይ ኪዳን ቃል ኪዳን
• የመጀመሪያውነ ቃል ኪዳን ከአዳም ጋር አደረገ፤
• ይህም ቃል ኪዳን የጸጋው ሥጦታ ነው፤
• መለኪያው የእግዚአብሔርን ትእዛዛዘ መጠበቅ ነው፤
• የቃልኪዳኑ ምልክት/ማኅተም/ የእውቀት ዛፍ ነበረች፤
• ፍጻሜ/ግብ/ በትንሽ ጊዜ/ጊዜያዊ/ መታዘዝ ዓለማዊ ሕይወት
ማግኘት፤
• የታተመው በእንስሳት ደም ነው፤
• ቃል ኪዳኑ ከሞት የማያድን ነበር፤
• የሐዲስ ኪዳን ቃል ኪዳን
• የተመሠረተው የአበውን ተስፋ ለመፈጸም ነው፤
• መነሻው የእግዚአብሔር ቸርነትና ለሰው ያለው የማይለወጥ ፍቅር
ነው፤
• መሥራቹ ራሱ ክርስቶስ ነው፤
• ቃል ኪዳኑ የጸናው በክርስቶስ ደም/መስዋዕትነት/ ነው፤
• ቃል ኪዳኑ የዘላለም ሕይወትን የሚያስገኝ ነው፤
• የቃል ኪዳኑ ፍጻሜ/ግብ/ ከእግዚአብሔር ጋር ተዋሕዶ ዘላለማዊ
ሕይወትን አግኝቶ ከክርስቶስ ጋር ሕያው ሆኖ መኖር፤
ብሉይ ኪዳን ሐዲስ ኪዳን
ጥንታዊ ፣ ቀዳማዊ ውል/ስምምነት/ አዲስ ውል/ስምምነት/
ውጫዊ/አፍአዊ/ ውስጣዊ ነው
የሰውን ኅሊና ፍጹም ሊያደርግ
ያጣውንም ነጻነት ሊመልስ አልቻለም
ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አዋሕዷል፣
ነጻነታችን ተመል ሷል
ፍጹም ይቅርታን አላስገኘም ፍጹም ይቅርታን ያስገኘ ነው
በፍርሃት የሚከበር ነበር በፍቅር የሚከበር ነው
ሁለቱ ኪዳናትን ስናጠቃልል በብሉይ ኪዳን አትብላ
የሚልና ይህንም አፍርሶ የበላው አዳም ቢሞት
በፈለገው ለማካስ በሐዲስ ኪዳን ብላ የሚልና ፍጹም
የድኅነት መንገድ ነው፡፡
ታዲያ በልተን መዳን እንዴት አንችልም?
ኢሳ 55፡1 እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም
የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን
ጠጅና ወተት ግዙ ---ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች፡፡
ዮሐ 6፡54-56 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም
ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፤ሥጋዬ
እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና፤ ሥጋዬን
የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ
እኖራለሁ።
3.2.2 ብሉይ ኪዳንና ኦሪት
• ምንነቱና አመሠራረቱ
ብሉይ ኪዳን
ሕገ ልቡና
/ከአዳም-ሙሴ/
3856 ዘመን
ሕገ ኦሪት
/ከሙሴ-ክርስቶስ/
1644 ዘመን
• ሀ. ሕገ ልቡና ምንነቱና አመሠራረቱ፡- ከእግዚአብሔር ለሰው በጥንተ
ተፈጥሮ በልቡናው ተቀርጾ ከሰውነቱ ጋር ተዋሕዶ የሚኖር ነው፤
• ሕገ ልቡና ጠባያቸው ባላደፈባቸው ቅዱሳን መላእክት ተጠብቆ ይኖራል፤ ለእነሱ
የተጻፈ ሕግ አያስፈልጋቸውም በንጽሕና ይኖራሉና፤
• ዓላማ - ሕገልቡና ለሰው የተሰጠው እንደዚሁ በንጽሕና እና በቅድስና በመኖር
ሃይማኖቱን አውቆ ፈጣሪውን በመፍራት እንዲኖር ነበር፤
• ሄኖ 19፡22 እንደ መላእክት ንጹሐን ጻድቃን ሁነው ይኖሩ ዘንድ ነው እንጂ ሰው
በእንዲህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም በጥቁር ቀለምና በቀይ ቀለም ጽፈው
ሃይማኖታቸውን ሊያጸኑ ሰው እንግዲህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም ነበርና
• ሰው በአእምሮ ጠባይዕ ዐውቆ እግዚአብሔርን በማምለክ የፈጣሪውንም ፈቃድ
በመፈጸም የኖረበትና የሚኖርበት ሕግ ነው፤
• ሮሜ 2፡12-15 ያለሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለሕግ ይጠፋሉና... እነርሱም
ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም
ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ
• ለ. ሕገ ኦሪት ምንነቱና አመሠራረቱ፡- ከእግዚአብሔር
በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለሕዝበ እሥራኤል የተሰጠ ነው፤
• ዓላማ -ሕገ ኦሪት ሰወች በተጻፈ ሕግ መመራት የጀመሩበት ጊዜ
ነው፤ ይህም በሕገ ልቡና ሁሉም ወደ ድኅነት መድረስ ስላልቻሉ በሕግ
እየተመሩ ወደ መዳን ይደርሱ ዘንድ አጋዥ ሆኖ የተሰጠ ሕግ ነው፤
• ሕገ ኦሪት በቃል በመናገርና በጽሑፍ በመቅረጽ እግዚአብሔር
በነቢያቱ አማካኝነት ለሕዝቡ የተሰጣቸውን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡
• የአምልኮት ሥርዓታቸውን ሁሉ የሚፈጽሙት በተጻፈ ሕግ ነው፤
• በአጠቃላይ ከሙሴ እስከ ክርስቶስ ያለውን ዘመን ይይዛል፤
መጻሕፍቱ እንዴት ይጠናሉ?
• የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጥናት
1. የሕግ መጽሐፍት ጥናት፤
• በመጀመሪያ በአጠቃላይ ስለ እነዚህ የመጽሐፈት ክፍልና ብዛት፤
• የመጽሐፉ ጸሐፊ ስምና እንደ አስፈላጊነቱ የጸሐፊው ታሪክ በአጭሩ፤
• የመጽሐፉ ስያሜ፣ የተጻፈበት ቦታና ዘመን፤
• የተጻፈበት ዓላማ፤
• የመጽሐፉ አጠቃላይ የምዕራፍ ብዛት፤
• የመጽሐፉ ዋና ዋና ይዘትና ታሪክ፤ ከሌሎች መጻሕፍት ጋር ያለው
ግንኙነት ካለ(በተለይ ለሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)፤
2. የብሉይ ኪዳን የታሪክ መጻሕፍት
3. የመዝሙርና የጥበብ መጻሕፍት
4. የትንቢት መጻሕፍት
ከሕግ መጻሕፍት አጠናን ምሳሌ
• የሕግ መጻሕፍት ከአራቱ የብሉይ ኪዳን ክፍሎች አንዱ ነው፤
• የሕግ መጻሕፍት የሚባሉተተ ነቢዩ ሙሴ የጻፋቸው አምስቱ መጻሕት ናቸው /ዘፍ፣ ዘጸ፣
ዘሌ፣ ዘኁ፣ ዘዳ/ በዚህም አምስቱ የሙሴ መጻህፍት ይባላሉ፤
• ብሔረ ኦሪት እየተባሉም ይጠራሉ፤
• ኦሪት የሚለው ቃል የሱርስት ሲሆን ትርጉሙም ሕግ ማለት ነው፤
• እንዲሁም በዕብራይስጥ ቶራ፣ በግሪክ/ፅርዕ/ ኖሞስ = ሕግ ማለት ነው፤
• አምስቱም መጻሕፍት እንደይዘታቸው የተለያየ ስያሜ አላቸው፤
• አምስቱ የሙሴ መጻሕፈት ስያሜና ዋና ዋና ይዘት አጠናን፡-
• 1. ኦሪት ዘፍጥረት፡- ኦሪት ዘልደትም ይባላል፤
• መጽሐፉ የሥነፍጥረትን አፈጣጠር፣ አጀማመር፣ አመጣትና ልደት የሚያስረዳ በመሆኑ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፣
• ከሕግ መጽሐፍት የመጀመሪያው ነው፤
• ዓላማው፡- ከፍጥረት አንስቶ እሥራኤላውያን ወደ ግብጽ እስከወረዱበት ጊዜ ድረስ
ያለውን የመለኮታዊ መገለጥ ታሪክ በጭሩ ማቅረብ ነው፤
• ስለዓለም አፈጣጠር፣ ስለሰው አፈጣጠር፣ እግዚአብሔር ከሰው ጋር ስለመሰረተው ቃል
ኪዳን፣ ሰው በኃጢአቱ ስለመውደቁ፣ ስለ ቃል ኪዳንና ስለ ቀደሙት አባቶች አኗኗር
ማሳየት ነው፤
• ኦሪት ዘፍጥረት $ ምዕራፎች ሲኖሩት ዋና ዋና ይዘቱ እንደሚከተለው
ይቀርባል፡
• 1. ምዕ 1-2 ስለ ሥነፍጥረት
• 2. ምዕ 3-4 ስለ ሰው ፈተናና ውድቀት
• 3. ምዕ 5-9 የጥፋት ውኃና የኖኅ ቤተሰቦች ድኅነት
• 4. ምዕ 10-11 የዓለም ሕዝብ ትውልድ ዝርዝርና የቋንቋ መለያየት
• 5. ምዕ 12-23 የአብርሃም ታሪክ
• 6. ምዕ 24-26 የይስሐቅ ታሪክ
• 7. ምዕ 27-36 የያዕቆብ ታሪክ
• 8. ምዕ 37-50 የዮሴፍ ታሪክ
• ሌሎችንም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በዚሁ መልኩ
ማጥናት ይቻላል
3.2.3. ሐዲስ ኪዳንና ወንጌል
• አዲስ ኪዳን ምንድን ነው?
• ሐዲስ የግእዝ ቃል ሲሆን በአማርኛ ደግሞ አዲስ ይላል
• አዲስ ውል ስምምነት መሓላ ማለት ነው፤
• የብሉይ ኪዳን ፍጻሜ ነው፤ የተመሠረተውም በክርስቶስ ደም ነው፤
• ሐዲስ ኪዳን ስንልም ከክርስቶስ መወለድ እስከ ዳግም ምጽአት ያለውን ያሳያል፤
• የሐዲስ ኪዳን ክፍል በጠቅላላ በተለያየ ይዘትና አቀራረብ ይጻፉ እንጂ ስለጌታችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናሩ በመሆኑ ወንጌል ተብሎ ይጠራል፤ ወንጌል
ማለትም የምሥራች ማለት ነው፤
• አስቀድሞ ነቢያት የተነበዩት የትንቢት ቃል አማናዊ ሆኖ የተሠጠበት ክፍል ነው፤
• አዲስ ኪዳን አካል፣ አማናዊና ፍጻሜ ነው፤
• የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ክፍፍልና አጠናን፡-
• አንዳለፈው ይቀጥላል
የቤት ሥራ
• ቡድን 1 - የሕግ መጽሐፍትና ራእይ ዮሐንስ
• ቡድን 2 - የመዝሙርና የጥበብ እና የታሪክ መጽሐፍትን
አጠቃላይ ዳሰሳና አከፋፈል አቆጣጠር
• ቡድን 3 - የትንቢት- በመጀመሪያ አጠቃላይ ስለመጽሐፍቱ
አቆጣጠርና አከፋፈል በመቀጠል ዐበይት ነቢያትን በዝርዝር
• ቡድን 4 - የምሥራች/የወንጌል/
• ቡድን 5 - የሐዋርያት ሥራና የሥርዓት መጻሕፍት
• ቡድን 6 - መልእክታት - አጠቃላይ ስለመልእክታቱ ከዚያም
14ቱን መልእክታት ዋና ዋና ይዘትና ጠባዕያት
2.3. የቅዱሳት መጻሕፍት አከፋፈል
• 2.3.1 የብሉይ ኪዳን አከፋፈል
• 2.3.2 የሐዲስ ኪዳን አከፋፈል
• (በምዕራፍ 3 በ3.1 የቀረበ ሲሆን በቀጣይ ባለው ምዕራፍ
የበለጠ ይዳሰሳል)
ምዕራፍ 4 - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክና አመጣጥ
• መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጻፈ
ብሉየ መዋዕል መጻሕፍተ ርዕስ ነው፡፡
• ለዓለም ሥነጽሑፍን ያስተማረ ዓለምን በቋንቋ ያናገረ
ብቸኛ መጽሐፍ ነው፡፡
4.1. የቅዱሳት መጻሕፍት አጻጻፍ ታሪክ
• 1. የተጻፉበት ዘመን
• መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ዘመንና ቦታ የተጻፈ እንጂ በአንድ ጊዜ የተገኘ
አይደለም፤
• የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ1400-400 ቅ.ል.ክ የተጻፉ ሲሆን ጸሐፍቱም
40 ያክል ቅዱሳን ሲሆኑ በጠቅላላው 46 መጻሕፍትን ይይዛል፡፡
• የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ ከ45-96 ዓ.ም በ8 ጸሐፍት የተጻፉ ሲሆኑ
በቁጥርም 35 ያክል ናቸው፡፡
• ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በመጀመሪያ የተጻፈው መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን ይኸውም
በ 1ሺ 486 ዓ.ዓ ነው(ቅ.ል.ክ 4ሺ 14 ዘመን ያስቆጠረ መጽሐፍ)፡፡
• በመጨረሻ የተጻፈው ደግሞ ራእየ ዮሐንስ ሲሆን ዘመኑም ከ96-98 ዓ.ም ነው፡፡
ይህን እንኳ 100 ዓ.ም ብለን ብንቆጥር መጽሐፍ ቅዱስ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ
4ሺ 114 ዓመታትን የፈጀ የእግዚአብሔር ፈቃድና የቅዱሳን ሥራ የተገለጠበት
ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡
• የሁለቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች(ብሉይና ሐዲስ) በተለያዩ ዘመን በተነሱ
ቅዱሳን ይጻፉ የቱንም ያክል የተራራቀ ዘመን ይኑራቸው እንጂ አንድ ዓላማ ይዘው
ያለምንም የሐሳብ ተፋልሶና ግጭት የተጻፉ ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው፡፡
• ይህም የሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ
የተገለጠባቸው መሆኑን ያስረዳል
• ከመጽሐፈ ሄኖክ ቀጥሎ ከብሉይ ኪዳን ቀድሞ የተጻፈው
መጽሐፈ ኢዮብ ሲሆን የተጻፈውም እሥራኤላውያን ከግብፅ
ባርነት ሳይወጡ ነው፡፡
• እሥራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ከወጡ በኋላ በ3ሺ 843 ዓ.ዓ
ኦሪት ተጻፈ
• በ4ሺ 407 ዓ.ዓ ሳኦል ነገሠ በዚህ ጊዜ መጽሐፈ ነገሥት ተጀመረ
• በ4ሺ 447 ዓ.ዓ ሳኦል ሞቶ ዳዊት ነገሠ በዚህ ጊዜ መዝሙረ
ዳዊት ተጻፈ
• በ4ሺ 481 ዓ.ዓ ዳዊት ሞቶ ሰሎሞን ነገሠ በ4ኛው ዓመት
ኢትዮጵያዊቱ ንግሥት ሳባ ወደ ጠቢቡ ሰሎሞን ሄደች፡፡
2. መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታና ቋንቋ ስለመጻፉ ማሳያ ሰንጠረዥ
ተ.ቁ የመጽሐፉ ስም የተጻፈበት ቦታ ቋንቋ
1 የኦሪት መጻሕፍት በሲና ምድር ዕብራይስጥ
2 መጽሐፈ ኢያሱ ምድረ ከነዓን(እሥራኤል) ዕብራይስጥ
3 መጽሐፈ አስቴር ፋርስ ዕብራይስጥ
4 ትንቢተ ዳንኤል ባቢሎን አረማይካ
5 ማቴዎስ ወንጌል በሶሪያ ውስጥ ባለች አንጾኪያ ከተማ ዕብራይስጥ/አረማይክ/
6 ማርቆስ ወንጌል ሮም ሮማይስጥ(ላቲን)
7 ሉቃስ ወንጌል አካይያ ጽርዕ(ግሪክ) - ዮናኒ(ዲያሌክት)
8 ዮሐንስ ወንጌል፣ የዮሐንስ መልእክታትና
ራእይ ዮሐንስ
ፍጥሞ ደሴት ጽርዕ(ግሪክ)
9 1ኛ ተሰሎንቄ አቴና
10 2ኛ ተሰሎንቄ በቆሮንቶስ ሳለ
11 ኤፌሶን፣ ፊልጵስዩስ፣ ቆላስይስና ወደ
ፊልሞና
በሮም/1ኛ እሥራቱ /
12 1ኛ ጢሞቴዎስ በሎዶቂያ/ከሮም እሥር ቤት እንደወጣ/
13 2ኛ ጢሞቴዎስ በሮም ወኅኒ ቤት/2ኛ እሥራቱ/
14 ዕብራውያን በመጀመሪያው የሮም እሥራቱ/ኢጣልያ
15 የሥርዓት መጻሕፍት ሱርስት/የሶርያ ቋንቋ/፣ ግሪክ የሚሊ አሉ
2. መጻሕፍቱ ወደ ኢትዮጵያ እንዴት መጡ፡-
ሀ. የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አመጣጥ
• ንግሥተ ሳባ ወደ ጠቢቡ ሰሎሞን መሄድና ቀዳማዊ ምኒልክን(በአረብኛ እብነ
እልኪም/እብነ ሐኪም/ በማለት ይጠሩታል ይህም የጥበበኛ ልጅ ማለት ነው፡፡)
ፀንሳ መመለሷ ከዚያም 22 ዓመት ሲሞላው ወደ አባቱ ሄዶ ለሦስት ዓመት
ከተቀመጠ በኋላ እሥራኤላውያን ለሁለት ንጉሥ መገዛት አይቻለንም( የበኵር
ልጅ ክቡር ስለሆነ) አንግሥና ወደ እናቱ ሀገር ላከው ባሉት ጊዜ አንግሦ
ከመጽሐፈ ሄኖክ አንስቶ ጠቢቡ ሰሎሞን እሰከጻፋቸው ያሉ ቅዱሳት
መጻሕፍትንና ይህን ተርጉመው የሚያስተምሩ 318 ሊቃውንትን ጨምሮ
ላከው፡፡ በዚያን ጊዜ በፈቃደ እግዚአብሔር ታቦተ ጽዮንም መጥታለች፡፡
ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር የመጡ ሊቃውንትም ቅዱሳት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ
ወደ ግእዝ በመተርጎም የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራ
ሠርተዋል፡፡ ይህም ቅ:ል:ክ 980 ዓመት ነው፡፡ ለዚህ ምሥክሩም ሲተረጉሙ
በቁሙ የዕብራይስጥ ቃላትን መተዋቸው ነው፡፡ የኸውም ኤሎሄ፣ አዶናይ፣
ጸባኦት የመሳሰሉትን ማለት ነው፡፡ (ሰሎሞን ወሲራክ ትርጓሜ መግቢያና
መጽሐፈ ምሥጢር አበጊዮርጊስ ዘጋስጫ) ይህች ንግስት መሄዷ ሌላ
የሚያስተምረን ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና አምልኮ ሥርዓት የነበረች
መሆኑን ነው ይኸውም የተናገረችው የእመነት ንግግርና በኋላም ክርስቶስ ስለ
እሷ የተናገረው ንግግር ነው፡፡
• 1ኛ ነገ 10:9፣ 2ኛ ዜና 9:8 አንተን የወደደ፥ በእሥራኤልም ዙፋን ያስቀመጠህ አምላክህ
እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን፡፡
• ማቴ 12:42 ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን
ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።
• ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና አምልኮ ሥርዓት ታመልክ እንደነበር ሌሎች መረጃዎችን እንጥቀስ፡-
• ኢትዮጵያ በኖኅ የልጅ ልጆች በሆኑት የካም ልጆች ኩሽ/ኢትዮጲስ/፣ ሳባ እና አቢስ መሰየሟ
• ይኸውም በኩሽ የኩሽ ምድር፣ በኢትዮጲስ(የኩሽ ሁለተኛ ስሙ) ኢትዮጵያውያን፤ በሳባ የሳባ
ምድር፣ በአቢስ አቢሲኒያውያን መባሏ ይህም የእነሱን እምነት መቀበሏን የሚያስረዳ ነው፡፡
• ኢትዮጵያዊው መልከ ጼዴቅ አበብዙሃን አብርሃምን መባረክ (ዘፍ 14:17-19: ዕብ 7:1-2)፤
መልከ ጼዴቅ - ትውልዱ ከአብርሃም ወገን የማይቆጠር፣ ክህነቱ ከሌዋዊ ያልሆነ፣ ጥንቱ ፍጻሜው
ለሌዋውያን ያልተገለጠ፣
• የስሙ ትርጓሜ በግእዝ መልከጼዴቅ ማለት ፤ለከ ገዛ፣ ጻድቅ- እውነተኛ ማለት ሲሆን ይህም
የጽድቅ ንጉሥ የእውነት ንጉሥ ማለት ነው፡፡ ይህን ካልን ግእዝ ደግሞ የኢትዮጵያ ቋንቋ እንጅ
የማንም አይደለም፡፡
• (የዕሥራ ምዕት በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ(VCD)-ማኅበረ ቅዱሳን)
ስለመልከ ጼዴቅ
• ከሰሎሞን በኋላ የተጻፉ መጻሕፍት -
• ከቀውስጦስ ታሪክ መጻሕፍ ምስክር እናመጣለን በ4ሺ 905 ዓ.ዓ እሥራኤል
ተማርከው ፋርስ ባቢሎን ወረዱ፡፡ በዚያን ጊዜም በኢትዮትዮጵያ ያሉ
ሊቃውንት ከንጉሡ ጋር ተማክረው እንዲህ ሲሉ የጥያቄ መለዕክት ላኩ
“የኛም የእናንተም አባቶች ነቢያት የጻፏቸው መጻሕፍት ተቃጠሉን ወይስ
ድነዋል? እናንተስ እንደምን አላችሁ? ለጣዖት ትሰግዳላችሁን? ሰንበትንስ
ሻራችሁን?” የሚል ነበር፡፡
• እነዚያም ይህን መልዕክት በሰሙ ጊዜ እዲህ ብለው መልሰዋል “እኛ በእነ
ዳንኤል ጸሎት የአብርሃም ፈጣሪ ጠብቆን ደህና ነን፡፡ መጻሕፍቱን ግን እኛ
እንዳንፈልጋቸው በምርኮ በመከራ ነው ያለን፡፡ እናንተ ግን በጸጥታ በደስታ
ነውና ያላችሁት ኢየሩሳሌም ወጥታችሁ ፈልጓቸው፡፡ ነገር ግን ከተማረክነ
በኋላ ዳንኤል ከእግዚአብሔር አግኝቶ የጻፈውን መጻሕፍ ጽፈን
ልከንላችኋልና ተቀበሉ” ብለው መጻሕፈ ዳንኤልን ልከውላቸዋል፡፡
• ይህም መጻሕፍ የመጣ አይሹር/አይዙር/ የሚባል የኢትዮጵያ ንጉሥ ስለ
ዘመዶቹ ስለ እሥራኤል ወደ ፋርስ ንጉሥ ወደ ዳርዮስ አማላጅነት በላከው
ሰው እጅ ነው፡፡ ይህንንም መጻሕፈ ዳንኤልን ተቀብለው በሰሎሞን ጊዜ
ከአባቶቻቻን ጋራ ከመጡ መጻሕፍት ደርበውታል፡፡
• በ4ሺ 975 ዓ.ዓ እሥራኤል ከባቢሎን ምርኮ ተመልሰው ዘሩባቤል
ነገሠ፡፡ ንጉሥ ዘሩባቤልም ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥ እንዲህ ሲል መልዕክት
ላከ “ሰላም ላንተ ይሁንና ስለ እግዚአብሔር ብለህ የለመንኩህን ስማኝ
ከኢየሩሳሌም ጥፋት አስቀድሞ ነቢያት የጻፏቸው መጻሕፍት በአያትህ
በሰሎሞን ልጅ በምኒልክ መንግሥት መጥተው ባገርህ አሉና ጽፈህ
ላክልኝ ብዬ ባባቶቻችን ፈጣሪ በከበረ ስሙ እማልድሃለሁ እኔም ወደ
እናተ ያልመጡትን ከኛ ዘንድ ያሉትን መጻሕፍት እልክልሃለሁ ይህ
ላንተም ለእኔም ደግ ነው” ብሎ ላከ፡፡
• የኢትዮጵያ ንጉሥም የዘሩባቤልን መልዕክት በሰማ ጊዜ ካህናቱን ጠርቶ
“በሀገራችን ያሉ መጻሕፍተ ነቢያትን ጽፋችሁ አምጡ” ብሎ ሁለት ሽህ
ወቄት ወርቅ ለስንቃቸው ሁለት መቶ ወቄት ወርቅ ለንጉሡ እጅ መንሻ
ሰጥቶ ሰደዳቸው፡፡ እነሱም መጻሕፍቱንም እጅ መንሻውንም ይዘው
ሄደው ለንጉሡ ሰጥተው በዘመኑ ካሉ ከደቂቀ ነቢያት ተገናኝተው ወደ
እኛ ያልመጡትን መጻሕፍት ጽፈው ይዘው ተመልሰዋል፡፡ ይገርማል
ኢትዮጵያውያን ከደቂቀ ነቢያት ተባርከው ሲመጡ የተመረጠ እድል
ይሉሀል እንዲህ ነው፡፡
• ኢትዮጵያ በሕገ ኦሪት አምልኮ ሥርዓትን ትፈጽም የነበረ መሆኑ ደግሞ
መጻሕፍቱ በሐገራችን ከመኖራቸውም ባሻገር ተተርጉመው ለአገልግሎት
የዋሉ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ይህ በመሆኑም ኢትዮጵያውያን በኦሪቱ ሥርዓት
እጅ ሊነሡ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር፡፡ ለዚህም 1. ነቢዩ ሶፎኒያስ
ትንቢት ተናግሯል፡፡ ይኸውም ከኢትዮጵያ ወንዝ ማዶ የሚሰግዱልኝ
የተበተኑት ልጆቼ መባዬን ይዘው ይመጣሉ፡፡ ሶፎ 3:10
• 2. ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ(ባኮስ/አቤላክ) ወደ ኢየሩሳሌም ሊሰግድ ሄዶ
ሰግዶ በሚመለስበት ጊዜ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ እያነበበ መገኘቱ በራሱ
ሁለት ጭብጥ ያስረዳል፡፡ ይህም የነቢያት መጻሕፍት ወደ ኢትዮጵያ
ቋንቋ(ግእዝ) መተርጎማቸውን በሌላ መልኩ ደግሞ ኢትዮጵያ በሕገ ኦሪት
አምልኮ ሥርዓት የነበረች መሆኑን፡፡ ሐዋ 8:26-ፍጻ
• ልብ በሉ! በምኒልክ ዘመን የመጡ ሌዋውያን መጻሕፍትን ወደ ግእዝ
ባይተረጉሙልን ኖሮ ይህ የኢትዮጵያ ሰው ወደ ኢየሩሳሌም ሊሰግድ እንዴት
ይሄድ ነበር? በአይሹር(አይዙር) ዘመንስ የነቢያት መጻሕፍት ባይመጡልን
ኑሮ ይህ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የነቢዩ ኢሳይያስን መጻሐፍ የት ያገኘው
ነበር?
• ኢትዮጵያ በሕገ ኦሪት ትመራ እንደነበር ሌሎች ማስረጃዎች፡-
• ቀዳማዊ ምኒልክ ከኢየሩሳሌም ሲመለስ ታቦተ ጽዮንን፣ ካህናተ ኦሪትንና
ቅዱሳት መጻሕፍትን ማምጣቱ
• በኢትዮጵያ የሕገ ኦሪት መስዋዕት ታዘጋጅ እንደነበር ሕያው የሆኑ አሻራዎች
አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- አክሱም ጽዮን(ትግራይ)፣ ጣና ቂርቆስ፣
መርጡለማርያም(ምሥ/ጎጃም)፣ ተድባበ ማርያም(ደ/ወሎ)ና ብርብር
ማርያም(ደቡብ ሕዝቦች) ይጠቀሳሉ፡፡
• የኢትዮጵያውያን ሕዝብ ሥርዓት ከእሥራኤላውያን ጋር መመሳሰሉ(ሕያው
አሻራዎች)
• ለምሳሌ፡- የወንድ ልጅ የግዝረት ሥርዓት፣ የሠርግ ሥርዓት፣ የማይበሉ
እንስሳት፣ የቀዳሚት ሰንበት አከባበር፣ የበዓላት ሥርዓት፣ የአለባበስ
ሥርዓትና ሌሎችም
• ኢየሩሳሌም ያለን የዴር ሱልጣን ገዳም
• 1ኛ ነገ 10:13 ንጉሡም ሰሎሞን፥ በገዛ እጁ ከሰጣት ሌላ፥ የወደደችውን
ሁሉ ከእርሱም የለመነችውን ሁሉ ለሳባ ንግሥት ሰጣት እርስዋም ተመልሳ
ከባሪያዎችዋ ጋር ወደ ምድርዋ ሄደች።
• ኢትዮጵያ በሕገ ኦሪት ትመራ እንደነበር ሌሎች ማስረጃዎች፡-
• ቀዳማዊ ምኒልክ ከኢየሩሳሌም ሲመለስ ታቦተ ጽዮንን፣ ካህናተ ኦሪትንና
ቅዱሳት መጻሕፍትን ማምጣቱ
• በኢትዮጵያ የሕገ ኦሪት መስዋዕት ታዘጋጅ እንደነበር ሕያው የሆኑ አሻራዎች
አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- አክሱም ጽዮን(ትግራይ)፣ ጣና ቂርቆስ፣
መርጡለማርያም(ምሥ/ጎጃም)፣ ተድባበ ማርያም(ደ/ወሎ)ና ብርብር
ማርያም(ደቡብ ሕዝቦች) ይጠቀሳሉ፡፡
• የኢትዮጵያውያን ሕዝብ ሥርዓት ከእሥራኤላውያን ጋር መመሳሰሉ(ሕያው
አሻራዎች)
• ለምሳሌ፡- የወንድ ልጅ የግዝረት ሥርዓት፣ የሠርግ ሥርዓት፣ የማይበሉ
እንስሳት፣ የቀዳሚት ሰንበት አከባበር፣ የበዓላት ሥርዓት፣ የአለባበስ
ሥርዓትና ሌሎችም
• ኢየሩሳሌም ያለን የዴር ሱልጣን ገዳም
• 1ኛ ነገ 10:13 ንጉሡም ሰሎሞን፥ በገዛ እጁ ከሰጣት ሌላ፥ የወደደችውን
ሁሉ ከእርሱም የለመነችውን ሁሉ ለሳባ ንግሥት ሰጣት እርስዋም ተመልሳ
ከባሪያዎችዋ ጋር ወደ ምድርዋ ሄደች።
• የቅዱሳት መጻሕፍት ማሰረጃዎች ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ከ40 ጊዜ በላይ
የተጠቀሰች ቅድስት ሀገር ናት፡፡ መዝ 67:31፣ አሞጽ 9:7፣ ሐዋ 8:26 ደግሞ
በሕገ አምልኮ እንደምትኖር ያስረዳሉ፡፡
• (የዕሥራ ምዕት በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ(VCD)-
ማኅበረ ቅዱሳን)
• ነቢዩ ሙሴ ኢትዮጵያዊቱን ሲፓራን ማግባቱ (ዘኁ 12:1-16)
ኢትዮጵያውያን በሕገ አምልኮ ስለሚመስሉት ነው፡፡ እህቱ ማርያምና
ወንድሙ አሮን በተቃወሙት ጊዜ እግዚአብሔር መቆጣቱም ለዚህ ነው፡፡
• ዘኁ 12:8-9 በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አልፈራችሁም?
አለ እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ።
• ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ለነቢዩ ኤርምያስ ደቀ መዝሙር ለመሆን የበቃው
በእምነቱ ነው፡፡
• ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋት ትንቢት በመናገሩ ወገኖቹ ወደ መጸዳጃ ጉድጓድ
የጣሉትን ኢትዮጵያዊው አቤሜልክ ግን ንጉሡን ማልዶ ከጉድጓድ እንዲወጣ
አደረገው፡፡ (ኤር 38:2-13)
• እንግዲህ እነዚህ ሁሉ የሚያስረዱን መጻሕፍቱ ተተርጉመው ለአገልግሎት
የዋሉ መሆኑን ነው፡፡
• በ5ሺ 242 ዓ.ዓ በጥሊሞስ ነገሠ(ግብፅ - እስክንድሪያ)
እርሱም ዓለምን አንደ ገል ቀጥቅጦ እንደሰም አቅልጦ ገዝቷት
ነበርና አሁንስ ምን ቀረኝ ባለ ጊዜ አማካሪዎቹ መጽሐፍተ
ብሉያትን አላስተረጎምክም አሉት፡፡ ንጉሱም ወደ ኢየሩሳሌም
ልኮ 72 መተርጉማንና መጻሕፍተ ብሉያት ተልከውለት
በ284 ቅ.ል.ክ ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ አስተርጉሟል፡፡
ይህም ሁለተኛው ትርጉም መሆኑ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች
የግዕዙን የኢትዮጵያን ትርጉም ሁለተኛው እንደሆነ አድርገው
የሚናገሩ ቢኖሩም ይህን ታሪክ ለማፋለስ ጥረዋልና እንደገና
እንዲያጠኑት እንጋብዛቸዋለን፡፡
ለ. የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አመጣጥ
• በሦስቱ ሕግጋት ማለትም በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪትና በሕገ
ወንጌል ጸንታ የኖረች ከዓለም ብቸኛ ሀገር ሀገረ እግዚአብሔር
ኢትዮጵያ ናት፡፡ የብሉያት መጻሕፍት ወደ ኢትዮጵያ እንዴት
እንደመጡ ቀደም ብለን አይተናል፡፡ ከዚህም አልፎ ኢትዮጵያ
ክርስትናን የተቀበለችው በራሷ ልጅ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ
በ34 ዓ.ም ነው፡፡ በዚህም በሐዲስ ኪዳን ከኢየሩሳሌም ውጭ
ክርስትናን በመጀመሪያ የተቀበለች ኢትዮጵያ ናት፡፡ ለዚህም ነው
ነቢዩ አሞጽ እሥራኤላውያንን ወቅሶ ኢትዮጵያውያንን
ያመሰገነው፡፡
• አሞጽ 9:7 የእሥራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ
ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?
ኢትዮጵያ በሕገ ወንጌል
• በክርስቶስ ልደት ወርቅ እጣን ከርቤ ካመጡት ሦስት ነገስታት አንዱ ኢትዮጵያዊው ንጉሥ
ባዜን መሆኑ
• መዝ 71:10 የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ
መንሻን ያቀርባሉ።
• ማቴ 2:10 ወድቀውም ሰገዱለት …እጅ መንሻ ወርቅ እጣን ከርቤም አቀረቡለት
• ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ መጠመቁ ሐዋ 8:26
• የቤተክርስቲያን ጸሐፍትም ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ ወንጌልን ሰበከላቸው ሲሉ ምስክርነታቸውን
ሰጥተዋል፡፡
• አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት(መሠረተ እምነት) ጠብቃ መኖሯ
(የዕሥራ ምዕት በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ(VCD)-ማኅበረ ቅዱሳን)
• ይሁን እንጂ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ግን በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን
በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አማካኝነት ወደግእዝ ተተርጉመው ነው፡፡
• ሁለተኛም በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአልአ ሜዳ ዘመነ መንግሥት ወደ ሀገራችን በመጡ
ተሰዓቱ ቅዱሳን(ዘጠኙ ቅዱሳን) የሐዲስ ኪዳንን መጻሕፍት በሙሉ ወደ ግእዝ ተርጉመዋል፡፡
• በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት መተርጉመ መጻሕፍት አባ ሰላማ ሐዲስ ኪዳንን ከተለዩ
ቋንቋዎች ወደ ግእዝ ተርጉመዋል፡፡
3. መጽሐቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ የተተረጎመበት ሁኔታ(በኢትዮጵያ -
ተጨማሪ)
• አባ አብርሃም(አባ ሮሜ) የተባሉ መነኩሴ ከጎንደር ተነስተው ወደ
ግብፅ በመሄድ የተለያዩ ቋንቋዎችን ካጠኑ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን
ወደ አማርኛ መልሰዋል፡፡ በመሆኑም የእርሳቸው የትርጉም ሥራ
በ1816 ዓ.ም ዐርባዕቱ ወንጌላት(አራቱ ወንጌል)፣ በ1821 ዓ.ም
ሐዲስ ኪዳን እና በ1832 ዓ.ም ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ
ጊዜ ታትሟል፡፡
• በ1878 ዓ.ም ደግሞ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ዕብራይስጥንና
ግሪክን ከሚያውቁ እንደ ማርቲን ፍላድ ካሉ የውጭሀገር ዜጎች ጋር
በመሆን እንደገና እንዲታተም አደረጉ፡፡
• አለቃ ተወልደ መድኅን ወደ ትግረኛ አናሲሞስ ነሲቡ ወደ ኦሮምኛ
ተርጉመውታል፡፡ በሌሎች ደግሞ በተለያዩ ቋንቋዎች(ወላይተኛ፣
ሲዳሞኛ፣ ጉራጊኛ፣ አኙዋክኛ ወዘተ) ተተርጉሟል፡፡
• በ1930 ዓ.ም(በ1938 እ:ኤ:አ:) ዩናይትድ ስቴትስ ፊላድልፊያ
በአማርኛ ታትሟል፡፡
• በ1953 ዓ.ም ከኢጣሊያን ወረራ በኋላ አሁን በአብዛኛው እጅ
የሚገኘው ባለ 66ቱ መጽሐፍ ቅዱስ ታተተመ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ
በደንብ መታረም እንዳለበት ይታመናል፡፡ ይህ አልበቃ ብሎ ግን በዘመኑ
በተነሱ የመናፍቃን ቅሰጣ “ጉድ ኒውስ ባይብል፣ ተሻሽሎ የወጣ፣ በቀላል
አማርኛ፣ አዲሲቷ ትርጉም፣ ለሕጻናተ፣ ሕያው ቃል” እያሉ ልዩ ልዩ
ስያሜ እየሰጡ ብሉይንና ሐዲስን ሲፈልጉም ሐዲስን ብቻ እያሳተሙ
እንካችሁ ካሉ ውለው አድረዋል፡፡ የእነዚህ መጽሐፍት የትርጉም ሁኔታ
የፈጠረውን ችግር መጽሐፍ ቅዱስና ትርጉም በሚለው ርዕሳችን
አናየዋለን፡፡
• በ1980 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ተክለሃይማት ፈቃድ ሙሉው መጽሐፍ
ቅዱስ ታተመ፤
• በ2000 ዓ.ም ደግሞ በብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ፈቃድ ሙሉው መጽሐፍ
ቅዱስ ተተርጉሟል፡፡ ይሁን እንጅ አሁንም ድረስ እንደገና መታረም
እንዳለበት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡
• 4. መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ የተተረጎመበት ሁኔታ(በውጭው ክፍለ ዓለም- በዚህ
ንዑስ ክፍል የተጠቀሱት ዓመቶች ሁሉም እ.ኤ.አ ናቸው)
• በ4ኛው መ/ክ/ዘመን(366 እ:ኤ:አ) አባጀሮም ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ዕብራይስጥንና
ግሪክን ቋንቋ በሚገባ ካጠና በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ቩልጌት ቋንቋ(በሮም ይኖሩ የነበሩ
የቩልገስ ህዝብ ቋንቋ) ተርጉሟል፤ ከዚያም ቩልገስን ወደ ላቲን ሲተረጉም እንዳለ በማረፉ
የእርሱን ጅምር ሌሎች እንዳጠናቀቁት ይነገራል፡፡ ከዚያ በመቀጠልም ከላቲን ወደ ጀርመኖች
ቋንቋ ጎቲክ ተተረጎመ፡፡ ይሁን እንጂ በ16ኛው መ/ክ/ዘ የተነሳው ማርቲን ሉተር ይህን የአባ
ጀሮምን የጎቲክ ትርጓሜ አልቀበልም በማለት ወደ ጀርመን ብሎም ከ50 በላይ ቋንቋዎች
እንዲተረጎም አድርጓል፡፡
• ሶርያም በሱርስት ቋንቋ የተተረጎሙ በርካታ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደነበሯት ይነገራል፡፡
በ5ኛው መ/ክ/ዘ የሮሐ ኤጲስ ቆጶስ የሆነው ራቡላ እና የመንበግ ኤጲስ ቆጶስ ፊልክስዮስ፤
በ7ኛው መ/ክ/ዘ ቶማስ ዘሄራክሊያ ትርጉሞችን በሱርስት ቋንቋ በማቅናት ይታወቃሉ፡፡
• ከ3-4ኛው መ/ከ/ዘ ቅዱስ ሚስሮችና ቅዱስ ሳሃክ ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን ወደ
አርማንያ(የአርመን ቋንቋ) ተርጉመዋል፡፡
• በ1525(26) ቴንዳሌ የተባለ እንግሊዛዊ ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጉም እያላ ካቶሊኮች የማርቲን
ሉተርን አተረጓጎም ስልት ተከትሏል በማለት በ1536 አስገደሉት፡፡ ይሁን እንጂ የእርሱ
ተከታይ የነበረው ኮቨርዳሌ በ1539 አጠናቆ በቅዱስ ማቴዎስ ስም The Mattew
Bible(እንግሊዞች ቅ/ማቴዎስ መጥቶ አስተምሯል ብለው ስለሚያምኑ) በማለት አሳተመው፡፡
• በ1553 የእንግሊዝ ፕሮቴስታንቶችመጽሐፍ ቅዱስን ምዕራፍና ቁጥር ሰጥተው
The Geneva Bible ብለው አሳተሙት፡፡ (በ1228 ዓ.ም በምዕራፍ በ1551
ዓ.ም በቁጥር እንደተለየ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ያስረዳል፡፡)
• በ1568 The Bishops Bible ብለው በንግስት ኤልሳቤጥ ዘመን አሳተሙት፤
• በ1601 The Douay Rheims Bible በካቶሊኮች ታተመ፤
• 1611 The King Jems Version(የንጉሥ ጀምስ ትርጉም ታተመ)፤
• በ18ኛውና 19ኛው መ/ክ/ዘ ግን በየግለሰቦች እየታተሙ በርካታ መጻሕፍት
መውጣት ጀመሩ አንዳንዶቹም ወዲያው ጠፍተዋል፡፡
• በ1881 ሐዲስ ኪዳን፣ በ1885 ብሉይ ኪዳን The Revised
Version(የተሸሻለው ትርጉም) በሚል ታተመ፤
• በ1901 The American Standard Version(የአሜሪካውያን ስታንዳርድ
ትርጉም)፤
• በ1952 The Revised American Standard Version(የተከለሰው
የአሜሪካውያን ስታንዳርድ ትርጉም) ታተመ፤
• በ1970 ደግሞ የእንግሊዝ ካቶሊኮችና የአየርላንድ ፕሮቴስታንቶች The New
English Bible(አዲሱ የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ) በሚል አሳተሙ፤
• በ1970 በዚሁ ዓመት አሜሪካ ደግሞ The New American Bible(አዲሱ
የአሜሪካ መጽሐፍ ቅዱስ) በማለት አሳተሙ፤
• በ1971 The New American Standared Bible(አዲሱ
የአሜሪካውያን ስታንዳርድ መጽሐፍ ቅዱስ)፤
• በ1976 Todays English Version(የዛሬው የእንግሊዝ ትርጉም)፤
• በ1978 The New International Version(አዲሱ ዓለም አቀፋዊ
ትርጉም)፤
• በ1985 የቀድሞውን የፈረንሳይኛ እና የኢየሩሳሌም መጽሐፍ
ቅዱስ(Jerusalem Bible) እንዲሁም ከዕብራይስጥና ከግሪክ መጻሕፍት ጋር
በማስተያየት ካቶሊኮች አዲሱ የኢየሩሳሌም መጽሐፍ ቅዱስ(The New
Jerusalem Bible)፤
• በ1985 በዚሁ ዓመት የአይሁድ ሊቃውንት አዘጋጅተውታል ተብሎ
የሚነገረው ታናክህ(Tanakh) መጽሐፍ ቅዱስ በዕብራይስጥ፤
• በ1989 በአሜሪካውያን The New Revised Standards
Version(አዲሱ የተከለሰው ስታንዳርድ ትርጉም)
• በ989 በእንግሊዝ The New Revised English Bible(አዲሱ የተከለሰው
የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ) በማለት አሳትመውታል፡፡
የመጻሕፍተ አምላካውያት ቁጥር ቀኖና
[የ'1ዱ ቅዱሳት መጻሕፍት የት መጣ]
• ቀኖና የሚለው ቃል የተገኘው ካኖን ከሚለው የጽርዕ [የግሪክ
ቋንቋ] ሲሆን ትርጉሙም ሕግ ወይም የመሥፈሪያ[የመለኪያ]
ደረጃ ማለት ነው::
• ስለዚህ ቀኖና ስንል ስለ አንድ መንፈሳዊ ጉዳይ በቤተክርስቲያን
አባቶች[በተለይም በሲኖዶስ] የተመሠረተ ድንጋጌ ወይም
ሥርዓት ማለታችን ነው:: ከእነዚህም የቤተክርስቲያን ቀኖናት
መካከል ስለቅዱሳት መጻሕፍት የተደነገገው ቀኖና ይጠቀሳል::
መጽሐፍ ቅዱስ የብዙ ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል ዉጤት
መሆኑ ይታወቃል:: በዉስጡ የተካተቱት እነዚህ መጻሕፍተ
ቅዱሳት [ቅዱሳት መጻሕፍት] በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ መጠሪያዎች አሏቸው:: እነዚህም ፦
፠ ቅዱሳት መጻሕፍት ወይም መጻሕፍተ ቅዱሳት፣
፠ አሥራው መጻሕፍት፣
፠ መጻሕፍተ አምላካውያት የሚሉት ናቸው::
• ቅዱሳት መጻሕፍት ወይም መጻሕፍተ ቅዱሳት የሚለው አጠራር
የሚያመለክተው መጻሕፍቱ የተለዩ የከበሩ የተቀደሱ መሆናቸውን፤
እንዲሁም ለልዕልናቸው አምሳያ፣ ወደረተኛ፣ አቻ ፣ምትክ
የማይገኝላቸው እጅግ በጣም ከፍ ያሉ መሆናቸውን ነው::
• አሥራው መጻሕፍት ማለትም በቀጥታ የመጻሕፍት ሥሮች ማለት ሲሆን
የቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ መገኛቸው ምንጮቻቸው ሥረ መሠረታት
መሆናቸውን የሚያጠይቅ ነው:: ከእነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ያልተቀዳ
ወይም እነርሱን ሥርና መሠረት አድርጎ ያልበቀለ ከመጀመሪያው እስከ
ፍጻሜው ተሠፍረው [ተለክተው] ተቆጥረው ተለይተው ታውቀው
በቀኖና ተደንግገው ተወሥነው የተቀበልናቸው መጻሕፍተ ቅዱሳት
ተባብረውና ተስማምተው ከሚያስተላልፉት ውጪ አዲስ መልእክት
የሚያመጣ ሌላ መጽሐፍ እንዳይኖር ድንበር አበጅተው ፍኖት ቀይሰው
አቅጣጫ መሪ ወሰን አስከባሪ በመሆናቸው የተሰጣቸው መጠሪያ ነው::
ከአሥራው መጻሕፍት ምንጭነት የሚቀዱት የሚፈልቁት ደግሞ አዋልድ
ይባላሉ::
• መጻሕፍተ አምላካውያት የተባሉበትም ምክንያት እነዚህ ቅዱሳት
መጻሕፍት የተገኙት በፈቃደ አምላክ እንጂ በሌላ በማንም
አይደለምና ነው:: የመጻሕፍቱ ባለቤት ራሱ እግዚአበሔር
መሆኑን ለማጠየቅ ሲባል ቅድስት ቤተክርስቲያን በዚህ መጠሪያ
ሰይማቸዋለች:: ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ "በእግዚአብሔር መጽሐፍ
ፈልጉ አንብቡም" ብሎ እንደተናገረ:: ኢሳ ፴፬፥፲፮።
በእግዚአብሔር መጽሐፍ ሲል በአምላክ መጽሐፍ ማለቱ ነውና::
የአምላክ መጽሐፍ ወይም መጽሐፈ አምላክ የሚለው ነጠላ
ሲሆን ሲበዛ መጻሕፍተ አምላካውያት ይሆናል::
• በተለምዶ መጽሐፍ ቅዱስ እያልን በነጠላ ቁጥር እንደ አንድ
መጽሐፍ የምንጠራው የእነዚህን ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል
ወይም ጥራዝ ሲሆን በኅፅኑ [በማኅፀኑ ወይም በዉስጡ] ክትት
አድርጎ የሰበሰባቸው ፹፩ መጻሕፍት ደግሞ በእነዚህ ሦስት እርስ
በእርሳቸው ተተካኪ በሆኑ አቻ ስሞች ይጠራሉ:: በመሆኑም
በዚህ ጽሑፍ በተቀያያሪነት እንጠቀምባቸዋለን::
• የአሥራው መጻሕፍት አልፋ እና ዖሜጋ
• የአሥራው መጻሕፍት ሁሉ በኵር የሆነው መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን
እርሱም የተጻፈው በ፩ሺ፬፻፹፮ ዓዓ ነው:: [መጻሕፍተ ሰሎሞን
ወሲራክ ትርጓሜ መቅድም እንዲሁም መጽሔተ አሚንን
ተመልከት] ይኽም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ፬ሺ፲፬ [አራት ሺህ
አሥራ አራት]ዓመታትን ያስቆጥራል:: የእነዚህ መጻሕፍተ
አምላካውያት መደምደሚያ የሆነው የሀዲስ ኪዳን መጽሐፍ
ደግሞ የዮሐንስ ራእይ ሲሆን እርሱም ከ፺፰ እሰከ ፻ ዓም ባለው
ጊዜ ውስጥ እንደተጻፈ ይታመናል:: ስለዚህ የመጻሕፍተ ቅዱሳት
አልፋቸው ማለትም መጀመሪያቸው መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን
ዖሜጋቸው ማለትም መጨረሻቸው ደግሞ የዮሐንስ ራእይ ነው::
ከዚህ በመነሣትም መጻሕፍተ አምላካውያት ተወጥነው
እስኪጠናቀቁ ፬ሺ፻፲፬ [አራት ሺህ አንድ መቶ አሥራ አራት]
ዓመታት ተቆጥረዋል ማለት ነው::
• መጽሐፍ ቅዱስ የአንድ ድንገታዊ ጊዜ ስጦታ ሳይሆን የእነዚህ
በርካታ ዘመናት ድምር ዉጤት መሆኑ እጅግ በጣም
የሚያስደንቀው አንደኛው ገጽታው መሆኑን መካድ
አይቻልም:: በዘመናት ዑደት ተጀምሮ እስኪያበቃ ይህን
ያህል ዘመን የጠየቀ መጽሐፍ አለ ከተባለ ብቸኛው መጽሐፍ
ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው:: ምናልባት በሆነ ወቅት
ተጀምረው ሳይጠናቀቁ የቀሩ ሌሎች መጻሕፍት ሊኖሩ
ይችላሉ:: [ለአብነትም እንደ ኢንሳይክሎፒድያ ያሉትን በብዙ
ጸሐፊዎች የሚቀናበሩትን መጻሕፍት መጥቀስ ይቻላል]
መጽሐፍ ቅዱስ ከእነዚህ መጻሕፍት ቢያንስ በሁለት
ምክንያቶች ይለያል፦
• ፩ መጽሐፍ ቅዱስ በውጥን የቀረ ሳይሆን ተጀምሮ በአግባቡ የተጠናቀቀ
በመሆኑ አልፋ እና ዖሜጋው ይታወቃል:: ከሌሎች መጻሕፍት ምናልባትም
አንዳንዶቹ ፍጻሜያቸው የማይታወቅ ሲኖሩ፣ ምንጊዜም ለእርማት እና
ለመሻሻል ክፍት ከመሆናቸውም ባሻገር ገና አዳዲስ ሀሳቦችንም [ከበፊቱ
የሚጋጩ ቢሆኑ እንኳ] ለማስተናገድ ያልተዘጉ ናቸው:: መጽሐፍ ቅዱስ
የበርካታ ዘመናት እና የተለያዩ ቅዱሳን ውጤት ይሁን እንጂ የዘመናት
መፈራረቅ አሉታዊ ተጽዕኖ ያላሳደሩበት በውስጡ ያሉት መጻሕፍትም ከዚህ
የተነሳ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚገመተው የሀሳብ ተቃርኖ ወይም ግጭት
ያልደረሰበት ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው::
• ፪ የእነዚያ መጻሕፍት ጸሐፊዎች ሰዎች በመሆናቸው ዐረፍተ ዘመን
እየገደባቸው መጻሕፍቱ በሂደት ላይ ወይም በጅምር ላይ መሆናቸውን እንጂ
መጠናቀቃቸውን ሳያውቁ የሚቀሩበት ሁኔታ ሲኖር፤ የቅዱሳት መጻሕፍት
ባለቤት ግን በባሕርዪው ኅልፈት በመንግሥቱ ሽረት የሌለበት ልዑል
እግዚአብሔር ነውና የጀመረውን ፈጽሞታል:: እግዚአብሔር በባሕርዪው
ሁሉን ቻይ ሁሉን ዐዋቂ እንደመሆኑ ይህ ቀረብኝ ያ ጎደለብኝ ብሎ የሚጸጸት
አይደለምና:: ሊያስተላልፍ የፈለገውን ሁሉ በወሰነው ጊዜ ያለማስተሀቀር
አስተላልፏል::
• ቅዱሳት መጻሕፍቱ ሁሉ የተቀዱት ከአንድ ባሕር ነውና ምንም እንኳ ፬ሺ፻፲፬ ዓመታትን
ያኽል ረጅም ዘመን የፈጀ ጊዜ ከባለቤታቸው ከእግዚአብሔር ቢመደብላቸውም
ያለመዘበራረቅ እና ያለ ቅራኔ በልዩ እና ፍጹም ስምምነት የተከናወኑ ናቸው:: እየታዘዙ
የጻፏቸው ሰዎች ብዙ አና በተለያየ ዘመን የኖሩ ቢሆኑም ቅሉ ምንጩ አንዱ እግዚአብሔር
የማይለወጥ ፤ ዘመናት ሲሻሻሉ መሻሻል፥ ሁኔታዎች ሲጎሳቆሉ መጎሳቆል የሌለበት ጽኑዐ
ባሕርዪ ስለሆነ የጊዜው መርዘም በእርሱ ዘንድ አሉታዊ ውጤት አያመጣም:: ሰው ግን
ዛሬ ያሰበውን ነገ የሚለውጥ፥ አሁን የጻፈውን መልሶ የማይደግም ስለሆነ የዘመናት
መፈራረቅ መሠረታዊ ለውጥ ያሳድሩበታል:: ከልምዱ [ከሚያየው ከሚሰማው ከኖረው
ከተማረው] በመነሳት በብዙ የሀሳብ ውጣ ውረድ ውስጥ ይጓዛል:: ስለሆነም የአስተሳሰብ
ተለዋዋጭነት ይከሰትበታል:: በአንድ ወቅት የሠራውን ወይም የጻፈውን በሌላ ጊዜ
ሊለውጠው ከዚህም በላይ በተቃራኒው ሊጓዝ ይችላል:: የዘመናት ባለቤት
እግዚአብሔር ግን ዘመናትን ይሠለጥንባቸዋል የወደደውንም ይሠራባቸዋል እንጂ
አይሠለጥኑበትም::
• ጥንት መጽሐፈ ሄኖክን ሲያጽፍ የነበረው እግዚአብሔር ኋላም አቡቀለምሲስን ያጻፈው
መለወጥ ሳይኖርበት ነው:: ዘመናትን አስረጃቸው እንጂ እርሱ ያው ነው:: በዘመናት
በለጸገ እንጂ ለውጥ የለበትም:: ቅዱስ ዳዊት ̋አንተ ግን ያው አንተ ነህ ዓመቶችህም ከቶ
አያልቁም ̋ ሲል እንደተናገረ:: መዝ ፻፩፥፳፯:: ደግሞም በነቢዩ ላይ አድሮ «እኔ
እግዚአብሔር አልለወጥም» ብሎ እንዳናገረ:: ሚል ፫፥፮። ቅዱስ ጳውሎስም ̋ኢየሱስ
ክርስቶስ ትናንትና ዛሬም እስከ ለዘላለምም ያው ነው ̋ እንዳለ።ዕብ፲፫፥፰።
አሥራው መጻሕፍትን በሚመለከት የተደረጉ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤያት
• አሥራው መጻሕፍትን በሚመለከት የተደረጉ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤያት
• ቅዱሳት መጻሕፍት ወደ አንድ ሙሉ ጥራዝ ከመጠቃለላቸው በፊት በርካታ ጉባኤያት
ተካሂደዋል:: ከቤተክርስቲያን ታሪክ እንደምንገነዘበው በታላላቆች ቅዱሳን አበው
አማካይነት ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሌሎች ሰርጎ ገብ ድርሳናት ለመጠበቅ ሲባል ተደጋጋሚ
ዓለም አቀፍ ጉባኤያት ተደርገዋል::
• የቅዱሳት መጻሕፍትን ቀኖና ለመወሰን በርካታ ጉባኤያት እንደተካሄዱ መረጃዎች
ያመለክታሉ:: ይሁን እንጂ ተቀባይነት ያላቸው ጉባኤያት ቤተ ክርስቲያን ሳትከፋፈል
ማለትም ከጉባኤ ኬልቄዶን በፊት የተካሄዱት ብቻ በመሆናቸው እኛም ትኩረታችን
በዚሁ መሠረት ይሆናል:: ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚመለከት ፮ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና
ያላቸው ጉባኤያት ተካሂደዋል::
• እንደ ሰባተኛ ሊቆጠር ይገባዋል ተብሎ በብዙ ጥንታዊ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት
የሚታመንበት ደግሞ ጉባኤ ኒቅያ ነው:: በዚህ ጉባኤ ላይ በሰፊው ወይይት
ባይደረግበትም አጀንዳው ተነሥቶ ፹፭ኛውን የሐዋርያት ቀኖና[ከዘህ በታች በዝርዝር
የምንመለከተውን] አጽንቶ እንደተጠናቀቀ ይታመናል:: ይህም የሆነው የጉባኤው
ተቀዳሚ እና ዐቢይ አጀንዳ የርእሰ መናፍቃን የአርዮስን ትምህርት ማውገዝ በመሆኑ እና
ረዥም ጊዜ በመፍጀቱ እንደሆነ ታውቋል::
• ከዚህ በታች የቀሩትን ፮ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና ያላቸው ጉባኤያት
እንመለከታለን::
፩᎐ ጉባኤ ሐዋርያት
• ጉባኤ የተካሄደበትን በ$ ዓ.ም ነው፤ የመጀመሪያው ሲኖዶስ
በመባል ይታወቃል፤ የተካሔደው በኢየሩሳሌም ሲሆን
የጉባኤው መሪም ሐዋርያው ያዕቆብ ነው፡፡(የጌታ ወንድም፣
የወንጌላዊው ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ ወንድም፣ መልእክቱን የጻፈው)
• ጉባኤ ሐዋርያት የዓለም አቀፍ ጉባኤያት መሠረት በመሆኑ
ለተከታዮቹ የኋለኞች ጉባኤያት አረአያነቱ የሚጠቀስ ነው::
• ይህ ጉባኤ '5 አንቀጾች ሲኖሩት '5ኛው አንቀጽም ስለ
መጻሕፍተ አምላካውያት የተደነገገ ነው::
• እነዚህ ቀኖናት በቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም አማከይነት
ተዘጋጅተው ወደ ተለያዩ አብያተክርስቲያናት እንደተላኩ
በ'5ኛው ቀኖና ላይ ተዘግቧል::
• Canon 85, Let the following books be esteemed venerable and holy by
you, both of the clergy and laity. Of the Old Covenant: the five books of
Moses—Genesis, Exodus, Leviticus, Numbers, and Deuteronomy; one of
Joshua(ኢያ) the son of Nun(ወልደ ነዌ), one of the Judges(መሳ), one of Ruth,
four of the Kings(ሳሙና ነገሥት), two of the Chronicles, two of Ezra, one of
Esther, one of Judith(ዮዲት), three of the Maccabees, one of Job, one
hundred and fifty psalms; three books of Solomon—Proverbs, Ecclesiastes,
and the Song of Songs; sixteen prophets. And besides these, take care that
your young persons learn the Wisdom of the very learned Sirach. (43
Books)
• But our sacred books, that is, those of the New Covenant, are these: the
four Gospels of Matthew, Mark, Luke, and John; the fourteen Epistles of
Paul; two Epistles of Peter, three of John, one of James, one of Jude; two
Epistles of Clement; and the Constitutions dedicated to you the bishops by
me Clement, in eight books; which it is not fit to publish before all,
because of the mysteries contained in them; and the Acts of us the
Apostles.
Philip Schaff, Ante-Nicene Fathers (ANF) Vol. 07, Constitutions of the Holy Apostles. Christian Classics
Ethereal Library, Grand Rapids, MI, 2004. p. 759, ANKE WANGER: The Biblical Canon of
the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church: p13-14
Not listed Prayer of Mianasseh, Jubilees, Enoch, Tobit, Wisdom,
• ይኽም ውሣኔ ከስምንቱ የሐዲስ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍት በግጽው
ሲኖዶስ [ረስጠጅ] 56ኛው ቀኖና 81
• እንዲሁም አብጥሊስ ሲኖዶስ [ረስጠአ ወይም ረስጣ] 80ኛው ቀኖና 81
• ትእዛዝ ሲኖዶስ [ረስጠብ] 55 የመጻሕፍት ቁጥራቸው ከ'1ዱ
ቅዱሳትእንደሆኑ አስረግጠው ነግረውናል
• እነዚህ ውሣኔዎች ቅድስት ቤተክርስቲያን በኋላ ለምትወሥናቸው
መጻሕፍትን የሚመለከቱ ማናቸውም ድንጋጌዎች አብነቶች ናቸው::
ምክንያቱም
• በቀኖና ቤተክርስቲያን የመደንገግ ሥልጣን ከጉባኤ ሐዋርያት የሚልቅ
የለም:: አነርሱ የወሠኑት ሁሉ የድንጋጌዎች ወይም የቀኖናዎች ሁሉ
ላዕለይ ለመሆኑ ተከራካሪ አይገኝም:: ስለሆነም ከእነርሱ በኋላ አነርሱን
ተከትለው የሚከናወኑ ጉባኤያት በሙሉ የቅዱሳን ሐዋርያትን አሠረ
ፍኖት የተከተሉ እንዲሆኑ ይጠበቃል:: ውሣኔዎች ሁሉ በእነርሱ
መስፈርት የሚለኩ በመሆናቸው የሐዋርያት ተከታዮች የሆኑት ሐዋርያነ
አበው የተቀበሉትን ባለማዛነፍ ሲከተሏቸው ታይተዋል::
• ስምንቱን የሐዲሰ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍት ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከሐዋርያት ተቀብሎ
ያሠራጨው የቅ/ጴጥሮስ ደቀመዝሙር የሆነው ቅዱስ ቀሌምንጦስ እጅ መላኩ የመልዕክቱን
ተቀባይነት አያጠራጥርም::
• በሐዋርያት ቀኖና የአሥራው መጻሕፍት ቁጥር '1 መሆኑ ከመገለጹም በላይ በአነዚህ ቅዱሳት
መጻሕፍት መካከል ምንም ዓይነት የደረጃ ልዩነት የሌለ መሆኑን ያረጋግጣል::
• በኋላ ዘመን አይሁድ በ፺ ዓም ባደረጉት የጃሚና ጉባኤ ፕሮቶካኖኒካል(የመጀመሪያ የቀኖና) እና
ዲዮትሮካኖኒካል(ሁለተኛ የቀኖና) መጻሕፍት በማለት ከፈለዋቸዋል:: የዚህ ጉባኤ ዋና ዓላማውም
ክርስትናን ለመቃወም እንዲመቻቸው የራሳቸውን የመጻሕፍት ቀኖና መደንገግ ነው::
• የአነርሱን ድርጊት በውል ከተመለከትነው ዘመነ ክርስትና ከታወጀ በኋላ ምንም ዓይነት ውሣኔ
ቢወሥኑ ምንም ዓይነት ተቀባይነት እንደሌለው ያለማመንታት እንረዳበታለን:: አይሁድ ያገለሏቸውን
በእግራቸው ገብቶ እነርሱን ተከትሎ ማግለል በምንም ዓይነት መለኪያ አሳማኝ ሊሆን አይችልም::
እንኳን መጻሕፍቱን ፈጣሪያቸውን የሰቀሉ ናቸውና::
• “There is currently no distinction at all between the book that are referred
to as protocanoncial and deuterocanonical. Whereas the Ethiopian Orthodox
Church understand and uses these terms when referring to the respective
books, it does not differentiate in its own Bible between proto and deutero
canon. All books accepted into the Bible are considered equally inspired,
equally the Word of God, and equally instructive (albeit for different
situations and circumstances.”
ANKE WANGER: The Biblical Canon of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church: p .4
• ይህ የአይሁድ ድርጊት ለጊዜውም ቢሆን እንደ እነ አባ ጀሮም(አውሳብዮስ
ሄሮኒመስ፣ አባ ሄሮኒመስ) በመሰሉ አባቶች ላይ ተጽእኖ አሳድሮ ነበረ ለማለት
ይቻላል:: ምክንያቱም አባ ጀሮም ቅዱሳት መጻሕፍትን ወደ ቩልገስ ቋንቋ
ሲተረጉም የሥራው መጀመሪያ ያደረገው የዕብራይስጥን ቋንቋ መማር ነበር::
ይህንንም ለማሳካት ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዟል:: በዚያም ከአይሁድ ሊቃውንት
ባገኘው መረጃ ምክንያት የጃሚናውን ውሣኔ ተከትሎ እነርሱ ያገለሏቸውን
ቅዱሳት መጻሕፍት ላለመተው ሲል ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት የሚል መጠሪያ
በመስጠት ተርጉሟቸዋል::
• ይህንን የተረዱት ቅዱስ አውግስጢኖስና ታዋቂው ጸሐፊ ሩፊኖስ በጉዳዩ ላይ
ከአባ ጀሮም ጋር በጥልቀት ከመከሩ በኋላ አባ ጀሮምን አሳምነው ሁሉም
የቀኖና መጻሕፍት ማዕርግ አግኝተው እንዲሰየሙ አድርገዋል::
• ይሁን እንጂ ይህ ጉዳይ መፍትሔ ከተሰጠው ከ፲፩፻ [ከአንድ ሺህ አንድ መቶ]
ዓመታት በኋላ የተነሳው ማርቲን ሉተር የተባለ የፕሮቴስታንት እምነት
መሥራች ወደኋላ ተመልሶ የአይሁድን ውሣኔ በማጽደቅ ይከተላት
የነበረችውን የሮም ካቶሊክን ቀኖና በማፍረስ ዲዮትሮካኖኒካል ወይም ሁለተኛ
የቀኖና መጻሕፍት (አፖክሪፋ) ይዞ አዲስ የክህደት በር ከፈተ::
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final
Bibl study power point aragaw final

Weitere ähnliche Inhalte

Was ist angesagt?

የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptxየመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptxGetachewEndale
 
Rick Warren, Purpose Driven Life: Section 24
Rick Warren, Purpose Driven Life: Section 24Rick Warren, Purpose Driven Life: Section 24
Rick Warren, Purpose Driven Life: Section 24Richard Chamberlain
 
Be Useful Vessels
Be Useful VesselsBe Useful Vessels
Be Useful VesselsOrFenn
 
The Romans Road of Salvation
The Romans Road of SalvationThe Romans Road of Salvation
The Romans Road of SalvationMichael Smith
 
Lifelines Sermon 1 (Tagalog)
Lifelines Sermon 1 (Tagalog)Lifelines Sermon 1 (Tagalog)
Lifelines Sermon 1 (Tagalog)Bong Baylon
 
Meditating on the word
Meditating on the wordMeditating on the word
Meditating on the wordGary Vought
 
The Power of God's Word
The Power of God's WordThe Power of God's Word
The Power of God's WordDon McClain
 
Session 05 Old Testament Overview - Exodus 20-40
Session 05 Old Testament Overview - Exodus 20-40Session 05 Old Testament Overview - Exodus 20-40
Session 05 Old Testament Overview - Exodus 20-40John Brooks
 
13 cost of discipleship
13 cost of discipleship13 cost of discipleship
13 cost of discipleshipchucho1943
 
Who Am I in CHRIST?
Who Am I in CHRIST?Who Am I in CHRIST?
Who Am I in CHRIST?Stanley Tan
 
presentation on christian discipleship
presentation on christian discipleshippresentation on christian discipleship
presentation on christian discipleshipRoshan Lobo
 
Barumsa Sanbataa_Barnoota2ffaa_nuusa3ffaa_2022.pptx
Barumsa Sanbataa_Barnoota2ffaa_nuusa3ffaa_2022.pptxBarumsa Sanbataa_Barnoota2ffaa_nuusa3ffaa_2022.pptx
Barumsa Sanbataa_Barnoota2ffaa_nuusa3ffaa_2022.pptxTakele Dufera
 
The ministry discovery process
The ministry discovery processThe ministry discovery process
The ministry discovery processMeki Carolino
 

Was ist angesagt? (20)

የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptxየመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
የመካኒሳ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን.pptx
 
Rick Warren, Purpose Driven Life: Section 24
Rick Warren, Purpose Driven Life: Section 24Rick Warren, Purpose Driven Life: Section 24
Rick Warren, Purpose Driven Life: Section 24
 
The New Me!
The New Me!The New Me!
The New Me!
 
Be Useful Vessels
Be Useful VesselsBe Useful Vessels
Be Useful Vessels
 
The Romans Road of Salvation
The Romans Road of SalvationThe Romans Road of Salvation
The Romans Road of Salvation
 
Lifelines Sermon 1 (Tagalog)
Lifelines Sermon 1 (Tagalog)Lifelines Sermon 1 (Tagalog)
Lifelines Sermon 1 (Tagalog)
 
Chapter 22 Peter
Chapter 22 PeterChapter 22 Peter
Chapter 22 Peter
 
Meditating on the word
Meditating on the wordMeditating on the word
Meditating on the word
 
God is calling you
God is calling youGod is calling you
God is calling you
 
HOLY TRINITY
HOLY TRINITYHOLY TRINITY
HOLY TRINITY
 
The Power of God's Word
The Power of God's WordThe Power of God's Word
The Power of God's Word
 
Chosen
ChosenChosen
Chosen
 
Power in the blood
Power in the bloodPower in the blood
Power in the blood
 
Session 05 Old Testament Overview - Exodus 20-40
Session 05 Old Testament Overview - Exodus 20-40Session 05 Old Testament Overview - Exodus 20-40
Session 05 Old Testament Overview - Exodus 20-40
 
13 cost of discipleship
13 cost of discipleship13 cost of discipleship
13 cost of discipleship
 
Who Am I in CHRIST?
Who Am I in CHRIST?Who Am I in CHRIST?
Who Am I in CHRIST?
 
presentation on christian discipleship
presentation on christian discipleshippresentation on christian discipleship
presentation on christian discipleship
 
Barumsa Sanbataa_Barnoota2ffaa_nuusa3ffaa_2022.pptx
Barumsa Sanbataa_Barnoota2ffaa_nuusa3ffaa_2022.pptxBarumsa Sanbataa_Barnoota2ffaa_nuusa3ffaa_2022.pptx
Barumsa Sanbataa_Barnoota2ffaa_nuusa3ffaa_2022.pptx
 
Fear not
Fear notFear not
Fear not
 
The ministry discovery process
The ministry discovery processThe ministry discovery process
The ministry discovery process
 

Ähnlich wie Bibl study power point aragaw final

ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdfከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdfssuser0a3463
 
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptxKEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptxarmoniumtvkiw
 
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdfየፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdfHabibBeshir
 
Pastoral caring and counseling in the church
Pastoral caring and counseling in the churchPastoral caring and counseling in the church
Pastoral caring and counseling in the churchPetrosGeset
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ሳልሳይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ሳልሳይ ሕታምጋዜጣ ቃል መስቀል ሳልሳይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ሳልሳይ ሕታምGabani Computer Company
 
ተግበራዊ ክርስትና.pdf
ተግበራዊ ክርስትና.pdfተግበራዊ ክርስትና.pdf
ተግበራዊ ክርስትና.pdfzelalem13
 
Come holy spirit (amaric ethiopia)
Come holy spirit (amaric ethiopia)Come holy spirit (amaric ethiopia)
Come holy spirit (amaric ethiopia)Martin M Flynn
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም Gabani Computer Company
 
ሥነ-ፍጥረት.pdf
ሥነ-ፍጥረት.pdfሥነ-ፍጥረት.pdf
ሥነ-ፍጥረት.pdfeshetu42
 
Tigrinya - The Epistles of Paul the Apostle to Seneca, with Seneca's to Paul.pdf
Tigrinya - The Epistles of Paul the Apostle to Seneca, with Seneca's to Paul.pdfTigrinya - The Epistles of Paul the Apostle to Seneca, with Seneca's to Paul.pdf
Tigrinya - The Epistles of Paul the Apostle to Seneca, with Seneca's to Paul.pdfFilipino Tracts and Literature Society Inc.
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታምጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታምGabani Computer Company
 

Ähnlich wie Bibl study power point aragaw final (20)

ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdfከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያፈነገጡ አስተሳሰቦችና መልሶቻቸው.pdf
 
Is issa jesus f
Is issa jesus fIs issa jesus f
Is issa jesus f
 
Tigrinya - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdf
Tigrinya - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdfTigrinya - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdf
Tigrinya - The Epistle of Paul the Apostle to the Laodiceans.pdf
 
Orthodox christianfamilylesson12
Orthodox christianfamilylesson12Orthodox christianfamilylesson12
Orthodox christianfamilylesson12
 
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptxKEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
KEEPING SPRITUAL PURITY in diffcult situationpptx
 
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdfየፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
 
Homiletic.pptx
Homiletic.pptxHomiletic.pptx
Homiletic.pptx
 
Pastoral caring and counseling in the church
Pastoral caring and counseling in the churchPastoral caring and counseling in the church
Pastoral caring and counseling in the church
 
Orthodox tewahedomarriage7wb
Orthodox tewahedomarriage7wbOrthodox tewahedomarriage7wb
Orthodox tewahedomarriage7wb
 
TIGRINYA - JUDE.pdf
TIGRINYA - JUDE.pdfTIGRINYA - JUDE.pdf
TIGRINYA - JUDE.pdf
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ሳልሳይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ሳልሳይ ሕታምጋዜጣ ቃል መስቀል ሳልሳይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ሳልሳይ ሕታም
 
ተግበራዊ ክርስትና.pdf
ተግበራዊ ክርስትና.pdfተግበራዊ ክርስትና.pdf
ተግበራዊ ክርስትና.pdf
 
Orthodox christianfamilylesson05
Orthodox christianfamilylesson05Orthodox christianfamilylesson05
Orthodox christianfamilylesson05
 
Orthodox tewahedo marriage 3 wb
Orthodox tewahedo marriage  3 wbOrthodox tewahedo marriage  3 wb
Orthodox tewahedo marriage 3 wb
 
Come holy spirit (amaric ethiopia)
Come holy spirit (amaric ethiopia)Come holy spirit (amaric ethiopia)
Come holy spirit (amaric ethiopia)
 
TIGRINYA - The Book of the Prophet Nahum.pdf
TIGRINYA - The Book of the Prophet Nahum.pdfTIGRINYA - The Book of the Prophet Nahum.pdf
TIGRINYA - The Book of the Prophet Nahum.pdf
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ራብዓይ ሕታም
 
ሥነ-ፍጥረት.pdf
ሥነ-ፍጥረት.pdfሥነ-ፍጥረት.pdf
ሥነ-ፍጥረት.pdf
 
Tigrinya - The Epistles of Paul the Apostle to Seneca, with Seneca's to Paul.pdf
Tigrinya - The Epistles of Paul the Apostle to Seneca, with Seneca's to Paul.pdfTigrinya - The Epistles of Paul the Apostle to Seneca, with Seneca's to Paul.pdf
Tigrinya - The Epistles of Paul the Apostle to Seneca, with Seneca's to Paul.pdf
 
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታምጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
ጋዜጣ ቃል መስቀል ቀዳማይ ሕታም
 

Mehr von Engidaw Ambelu

pop andurinary incontinence
pop andurinary incontinencepop andurinary incontinence
pop andurinary incontinenceEngidaw Ambelu
 
Congenital heart disease
Congenital heart diseaseCongenital heart disease
Congenital heart diseaseEngidaw Ambelu
 
Hypertensive disorder of pregnancy
Hypertensive disorder of pregnancyHypertensive disorder of pregnancy
Hypertensive disorder of pregnancyEngidaw Ambelu
 
acquired heart disease
acquired heart diseaseacquired heart disease
acquired heart diseaseEngidaw Ambelu
 
congenital heart disease_january2011_final
congenital heart disease_january2011_finalcongenital heart disease_january2011_final
congenital heart disease_january2011_finalEngidaw Ambelu
 
urinary tract infection
urinary tract infectionurinary tract infection
urinary tract infectionEngidaw Ambelu
 
Approach to the child with anemia
Approach to the child with anemiaApproach to the child with anemia
Approach to the child with anemiaEngidaw Ambelu
 
Diarrheal diseases in children
Diarrheal diseases in childrenDiarrheal diseases in children
Diarrheal diseases in childrenEngidaw Ambelu
 
Acute respiratory tract infections
Acute respiratory tract infectionsAcute respiratory tract infections
Acute respiratory tract infectionsEngidaw Ambelu
 
Approach to childhood poisoning.tmp 12
Approach to childhood poisoning.tmp 12Approach to childhood poisoning.tmp 12
Approach to childhood poisoning.tmp 12Engidaw Ambelu
 

Mehr von Engidaw Ambelu (20)

pop andurinary incontinence
pop andurinary incontinencepop andurinary incontinence
pop andurinary incontinence
 
Congenital heart disease
Congenital heart diseaseCongenital heart disease
Congenital heart disease
 
Hypertensive disorder of pregnancy
Hypertensive disorder of pregnancyHypertensive disorder of pregnancy
Hypertensive disorder of pregnancy
 
PROM
PROMPROM
PROM
 
preterm labor
preterm laborpreterm labor
preterm labor
 
postpartum hemorrhage
postpartum hemorrhagepostpartum hemorrhage
postpartum hemorrhage
 
antepartal hemorrhage
antepartal hemorrhageantepartal hemorrhage
antepartal hemorrhage
 
acquired heart disease
acquired heart diseaseacquired heart disease
acquired heart disease
 
congenital heart disease_january2011_final
congenital heart disease_january2011_finalcongenital heart disease_january2011_final
congenital heart disease_january2011_final
 
CNS infections
CNS infectionsCNS infections
CNS infections
 
Seizure disorders
Seizure disordersSeizure disorders
Seizure disorders
 
urinary tract infection
urinary tract infectionurinary tract infection
urinary tract infection
 
Approach to the child with anemia
Approach to the child with anemiaApproach to the child with anemia
Approach to the child with anemia
 
Childhood asthma & TB
Childhood asthma & TBChildhood asthma & TB
Childhood asthma & TB
 
Seminar on poisoning
Seminar on poisoningSeminar on poisoning
Seminar on poisoning
 
Diarrheal diseases in children
Diarrheal diseases in childrenDiarrheal diseases in children
Diarrheal diseases in children
 
Abnormal labor
Abnormal laborAbnormal labor
Abnormal labor
 
Acute respiratory tract infections
Acute respiratory tract infectionsAcute respiratory tract infections
Acute respiratory tract infections
 
Approach to childhood poisoning.tmp 12
Approach to childhood poisoning.tmp 12Approach to childhood poisoning.tmp 12
Approach to childhood poisoning.tmp 12
 
Labor
LaborLabor
Labor
 

Bibl study power point aragaw final

 • 1. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ የመጽሐ ቅዱስ ጥናት ለተተኪ መምህራን ደረጃ 2 ሥልጠና የተዘጋጀ አራጋው ብርሃኑ ሐምሌ 23/2009 ዓ.ም ባሕር ዳር • ሐምሌ 02ና ግንቦት 15 ስንክሳር የቱ
 • 2. • የእግዚአብሔርን ድምፅ ከምንሰማባቸው ነገሮች ቀዳሚውና ዋነኛው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ • ይህን የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት ደግሞ ፈቃደኛ ልብ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ • በሌላ መልኩ ደግሞ “ጠርጥር ከገንፎም አለ ስንጥር” እንዲሉ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ፈቃደኛ ልቡናችንን ከፍተን (ሰጥተን) ስንሰማ ሌሎቹ ደግሞ በውስጥ ለውስጥ የላኩብንን ስንጥር መለየት ይገባናል፡፡ • ይህ ካልሆነ ግን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉን እንደሚችሉ የማንክደው ሀቅ ነው፡፡ መግቢያ
 • 3. • አባቶቻችን የመጽሐፍትን ምንነትና ጠቀሜታ ተረድተው ቅዱስ እግዚአብሔር በቅዱሳት መጽሐፍት የነገራቸውን ተግብረው እንዲያውም ከዚያ በላይ (በትሩፋት፣ በገድል) ፈጽመው እግዚአብሔርን አገልግለውና አስደስተው አልፈዋል፡፡ • ለእነርሱ ብቻ አይደለም ለእኛም እንዲደርሰን ብራና ፍቀው በቀለም ብቻ ያይደለ በደማቸው ጽፈው፣ በዋሻ በፍሩክታ እየተሰደዱ በእሳት እየነደዱ አቆይተውልናል፡፡ • በመሆኑም የእሳት ልጅ አመድ እንዳንባል ቅዱሳን በኖሩበት ሕይወት መኖር፣ የእነርሱንም ቅርስ መጠበቅ ኃላፊነት ሳይሆን ግዴታችን ነው፡፡ • ለዚህ ደግሞ አባቶቻችን የተማሩበትን፣ የኖሩበትን፣ እነርሱ ያገኙትን አምላካዊ ስጦታ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን ልናውቀው፣ ልንረዳው፣ ልንጠብቀውና ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ • በመሆኑም በዚህ ሥልጠና የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም፣ ታሪክና ምንነት፣ ቀኖና፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ምንነት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ባህል፣ አባባል፣ ትውፊትና አዋልድ መጻሕፍትና ሌሎች ጉዳዮችን እንዳስስበታለን፡፡ • የጥበብና የእውቀት ሁሉ ባለቤት የጠመመውን አቅንቶ የጎደለውን ሞልቶ ቅዱስ ቃሉን እንድንሰማ ፈቃዱ ይሁንልን የድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት አይለየን፡፡
 • 4. ምዕራፍ 1 - የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ምንነት፣ ዓላማና ጥቅም • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከሌሎቹ ጥናቶች /Research/ ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ሌሎች ጥናቶች ጉድለት አለበት በሚሉት ጉዳይ ላይ ተነስተው የራሳቸውን ጥረት ካደረጉ በኋላ በደረሱት ግኝት ወይም የዳሰሳ ውጤት መሠረት የራሳቸውን አስተያየት (Recommendation) ወይም መላምት (Hypothesis) ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንል ግን መጽሐፍ ቅዱስን መርምረን ይህ እውነት ነው፣ ይህ ስህተት ነው አለያም ይህን እንቀበለው ይህን አንቀበለው ይህ ደግሞ እንዲህ ቢሆን መልካም ነው የምንልበት ሂደት አይደለም፡፡ • ይልቁንም እግዚአብሔር በገለጠልን መጠን ዝርዝር ዕውቀትና መረጃ ለማግኘት ነው፡፡ 1 - የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ምንነት፣ ዓላማና ጥቅም
 • 5. የመጽፍ ቅዱስ ጥናት ያስተማረን ወይም አብነታችን ምንድን ነው? 1. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያስተማረን ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡- ይኸውም ለምሳሌ ያክል ጥቂት እንመልከት - የኤማሁስ መንገደኞችን በመንገድ በሚሄዱበት ጊዜ ሲከራከሩ ሰምቶ ከጠየቃቸውና ከመለሱለት በኋላ ወቅሶም እንዲህ መጽሐፍትን ተረጎመላቸው አስጠናቸው፡፡ • ሉቃ 24.27 ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው---እርስ በርሳቸውም በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ። - ለሐዋርያትም ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በመጻሕፍት እንዲህ ተጽፏል እያለ የመጽሐፍትን ነገር እየጠቀሰ ያስጠናቸውና ያስተምራቸው ነበር፡፡ ደግሞም በስልጣኑ አስተማራቸው ይላል፡፡ በተለይም ከትንሣኤው በኋላ ከማረጉ በፊት መጻሕፍትን ተርጉሞላቸዋል፡፡ • ማቴ 5.1-2 ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው • ማር 2.13 ደግሞም በባሕር አጠገብ ወጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡና አስተማራቸው፡፡ • ማቴ 21.13 ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው
 • 6. 2. ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አብነቶቻችን ናቸው • ከክርስቶስ የተማሩ ሐዋርያት በኋላም ሐዋርያነ አበው ሊቃውነተ ቤተክርስቲያን እና መምህራን ብዙ መጻሕፍትን አጥንተው እውነቱን ከሐሰቱ ስንዴውን ከእንክርዳዱ ለይተው መጻሕፍትን ከመጻሕፍት ጠቅሰው አራቀው ተምረው አስተምረው አብነት ትተውልን አልፈዋልና አብነቶቻችን ናቸው፡፡ ዕብ 13:7
 • 7. 2. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዓለማ ምንድን ነው? • መንፈሳዊ ሕይወት የምንማርበትን መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሆነ መቼ እንዴትና በማን እንደተጻፈ፣ በውስጡ ምን እንደሚገኝና ከሌሎቹ ትክክለኛነቱ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ፤ • መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበትን ቋንቋ፣ ቦታ፣ የአጻጻፍና የአተረጓጎሙን ስልት ለመረዳት፤ • የመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛው ቀኖና እንዴትና መቼ እንደተወሰነና ከእኛም እንዴት እንደደረሰ ለመረዳት፤ • ባገኘነው ግንዛቤ ከበፊቱ በተሻለ አንብበንና ተረድተን በበለጠ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ፤ • በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የተዘጋጀን እንድንሆን (1ኛ ጴጥ 3:15)
 • 8. 3. የመጽሐፍ ቅዱስ አጠናን ስልት • መንፈስ ቅዱስ ካላገዘ በቀር መጽሐፍ ቅዱስን በራስ ሐሳብና ፍልስፍና መረዳት በእጅጉ አዳጋች ነው፡፡ በመሆኑም መንፈስ ቅዱስን አጋዥ አድርጎ መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የሚከተሉትን የጥናት ስልቶች ልንከተል እንችላለን፡- • 3.1. መጠይቃዊ ስልቶችን በመጠቀም መጽሐፉ የተጻፈበትን አለያም ቃሉ የተነገረበትን ሁኔታ መረዳት፡- • ማን/Who/? ምን/What/? መቼ/When/? የት/Where/? ለምን/Whay/? እንዴት/How/? የሚሉትን የአንድን መጽሐፍ አለያም ቃል የተጻፈበትን አለያም የተነገረበትን ሁኔታ ሊያስረዱ የሚችሉ መሠረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልጋል፡፡
 • 9. 3.2. የምንባቡን ሥነ ጽሑፋዊ የአጻጻፍ ባሕርይ መረዳት • መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈባቸውን ከዚህ ቀጥለው የቀረቡ 4 ሥነ ጽሑፋዊ የአጻጻፍ ስልቶች መገንዘብ የተሸለ አረዳድ ሊሰጠን ይችላል፡፡ 3.2.1. ትረካዊ የአጻጻፍ ስልት/Narrative Writing System/ • የብሉይም ይሁን የሐዲስ ኪዳን ብዙ መጻሕፍት በትረካዊ የአጻጻፍ ስልት ተዘግበው እናገኛለን፡፡ ታዲያ ይህን ትረካዊ ስልት ተከትለን ስናጠና እንደ ታሪክ ብቻ አንብበን የምንተወው ሳይሆን ብዙ አምላካዊ ምሥጢር ያላቸው መሆኑን ልናስተውል ይገባል፡፡ በዚህ ከተጻፉ መጻሕፍት ውስጥ ለምሳሌ፡- መጽሐፈ ሩታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ ሉቃስ ወንጌል ወዘተ ይጠቀሳሉ፡፡ 3.2.2. ሥነ ግጥማዊ የአጻጻፍ ስልት/Poietic Writing System/ • ልበ አምላክ የተባለው ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ከጻፈው የመዝሙርና የቅኔ መጽሐፍ ብንነሳ የተጻፈው በግጥም መልክ ነው፡፡ ነገር ግን ሰው በሌለበት ጊዜ ሰው ሆኖ የተገኘውን መዝሙረኛውን ዳዊት ቅድመ አምላክነቱን፣ ልደቱን፣ ስደቱን፣ መከራውን፣ ስቅለቱን፣ ትንሣኤውን፣ ዕርገቱን እንዲሁም ዳግም ምጽአቱን ተናግሮበታል፡፡ ለዚህስ አይደል እንደልቤ ያለውስ፡፡ እንዲያውም እነዚህን መጽሐፍት ስናጠና የተጻፉበትን ጥበባዊና ምሳሌያዊ፣ ቅኔያዊና መዝሙራዊ ምሥጢር ልንረዳ ይገባል፡፡ በብሉይ ኪዳን በዚህ መልክ የተጻፉ መጽሐፍት 8 ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡
 • 10. 3.2.3. ትምህርታዊ የአጻጻፍ ስልት/Didactic Writing System/ • በዚህ ስልት የተጻፉት ደግሞ አብዛኛው ትኩረታቸው መሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት/Dogmatic/፣ ሥርዓተ እምነት፣ ትውፊት/Tradition/ና ትንቢታዊ መልእክት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የቅዱስ ማቴዎስና ዮሐንስ ወንጌል፣ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታት፣ ትንቢተ ኢሳይያስ ወዘተ 3.2.4. ራእያዊና ሕልማዊ የአጻጻፍ ስልት/Apocalyptic Writing System/ • መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈባቸው ስልቶች መካከል ጠንከር ያለውና ጥልቅ አረዳድን የሚጠይቀው ይኸው የአጻጻፍ ስልት ነው፡፡ ይህ ስልት በቀጥታ ከሚናገሩትና ከሚያስረዱት በላይ ምሥጢር አዘል ስለሆኑና አንዳንዶቹ ደግሞ ለወደፊት የሚፈጸሙ ጭምር ያለባቸው መሆኑ ነው፡፡ ለምሳሌ ያክል ራእየ ዮሐንስን ብንወስድ ሊቃውንተ ቤተክርስቲን ይህን መጽሐፍ ለመተርጎም ወደ ሰባት የሚደርሱ የትርጓሜ መንገዶችን እንደተከተሉ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ራእየ ዮሐንስን በተረጎመበት መጽሐፉ ገልጦልናል፡፡ • በራእያዊና ሕልማዊ የአጻጻፍ ስልት ተጽፈው ከምናገኛቸው መጻሕፍት ውስጥ ትንቢተ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል፣ ኢዩኤልና ራአየ ዮሐንስ ይጠቀሳሉ፡፡
 • 11. 3.3. የመጽሐ ቅዱስን የአጻጻፍ ይዘትና የቋንቋ ጠባይዓት መረዳት 3.3.1. ሕዝባዊ ነው/Popular/ • ይህም ማለት መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው ቀድመው የነበሩትን፣ አሁን ያሉትንና ለወደፊትም የሚኖሩትን የህብረተሰብ ክፍሎች(ሕዝብ) በሚያጠቃልልና ሁሉን ዓቀፍ በሆነ ቋንቋና ይዘት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ክፍል እኔን አይመለከትም ማለት አይቻልም፡፡ 3.3.2. ክስተታዊ ነው • እግዚአብሔር ነገሮችን የሚገልጥበት ክስተታዊ ሁኔታ አለው፡፡ ይህም ቋንቋው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚገልጠው ነገር ጋር ይዛመዳል፡፡ ይህ ክስተታዊ አገላለጽ ግን በማስተዋል ካልተረዳነው ትርጉም ላይሰጠን ይችላል፡፡ • ለማሳሌ፡- ማቴ 10:42 ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም። ይህንን ለመረዳት ጽዋ ውኃ ምንድን ነው፣ ለምንስ በጽዋ ውኃ አለ ብለን ካልተገነዘብነው እንደ ቀላልና ተራ ነገር ልንመለከተው እንችላለን፡፡ 3.3.3. ኢ-ሳይንሳዊና ኢ-ንድፈ ሐሳባዊ ነው/Non-scintific and Non-theoretical/ • መጽሐፍ ቅዱስ የአንድን ነገር እውነተኛ ባሕርይ በንድፈ ሐሳብ/Theory/ ደረጃ ብቻ አያስቀምጥም በሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ ጥበብ ብቻም አይገልጥም ከዚህም በላይ የመለኮታዊ ባሕርይ መገለጥን ይከተላል እንጅ፡፡ ስለሆነም አጻጻፉ ኢ-ሳይንሳዊና ኢ-ንድፈ ሐሳባዊ ነው፡፡
 • 12. 3.4. መጽሐፍ ቅዱስን በዐውደ እይታ የማጥናት ስልት • ዐውደ እይታ ወይም ዐውደ ምንባብ ማለት አንድን የተጻፈ ቃል ወይም ዐረፍተ ነገር ከመድረሱ በፊትና በኋላ በዙሪያው ያሉ ዐረፍተ ነገሮች ወይም አንቀጾች ናቸው፡፡ ይህ ዘዴ መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ የሚቃረን አድርገን እንዳንወስድና ትክክለኛውን ትርጉም ለማወቅ የሚረዳን የአጠናን ስልት ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡- 3.4.1. ሥነ-ጽሑፋዊ ዐውደ እይታ ያጠናን ስልት፡- • በምንባቡ ክፍል ዙሪያ የተገለፁትን አጠቃላይ ሥነጽሑፋዊ ሁኔታዎች ወይም ድርጊቶች ወይም ሐሳቦች ማለት ነው፡፡ የቃል ዐውደ እይታ ዐረፍተ ነገር፣ የዐረፍተ ነገር ዐውደ እይታ አንቀጽ፣ የአንቀጽ ዐውደ እይታ ምዕራፍ ፣ የምዕራፍ ዐውደ እይታ መጽሐፍ፣ የመጽሐፍ ዐውደ እይታ መላው መጽሐፍ ቅዱስ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሉቃ 10:30 አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ የሚለውን ለመረዳት የኢየሩሳሌምንና የኢያሪኮን ምንነት መረዳት ያስፈልጋል፡፡ 3.4.2. ሥነ መለኮታዊ ዐውደ እይታ • የመጽሐ ቅዱስን ሥነ መለኮታዊ እይታ ካልተረዳን ምሥጢሩን ላንረዳ ብሎም ምሥጢርን ልናፋልስ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ የዮሐንስ ወንጌልን ለመረዳት የመለኮታዊ ባሕርይን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ በመጀመሪያ ቃል ነበር የሚለውን ለመረዳት የቃልን ቅድምና ካላወቅን ቃል በሚለው ብቻ ከሄድን አአትሪኮን፣ በርፎሪኮን እና አተርግዋን የሚባሉ ዝርዋን ቃላት አሉና ገደል ይከተናል፡፡ • በማቴዎስ ወንጌል የተገለጸውን በግራና በቀኝ መቆም፣ ፍየልና በግ ወዘተ የመለኮታዊ ባሕርይን ካልተረዳን ወደተሳሳተና ትርጉም ወደሌለው አረዳድ ይወስደናል፡፡
 • 13. 3.5. በአገላለጽ ወይም አባባል የሚታዩ የትርጉም ልዩነቶችን የማጥናት ስልት • መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ የሆነ አገላለጽና አባባል ያለው የራሱ የሆነ የቃላት አጠቃቀምና የቋንቋ ሥርዓት አለው፡፡ 3.6. የሐሳብ አንድነትንና የምሥጢር መስማማትን በጥንቃቄ የማጥናት ስልት • በመጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ጉዳይ ላይ በተለያየ አገላለጽና ሊጋጩ በሚመስሉ ሁኔታ የቀረቡ በምሥጢርና በሐሳብ ግን የማይለያዩ ብዙ አገላለጾች አሉትና ይህንም በጥንቃቄ ማጥናት ተገቢ ነው፡፡
 • 14. ምዕራፍ 2 - የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉምና ቅዱስነት 2.1. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ? • መጽሐፍ ቅዱስ “መጽሐፍ” እና “ቅዱስ” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ጥምር ቃል ሲሆን “መጽሐፍ” በአንድ ጥራዝ ሥር የተሰበሰበ ጽሑፍ ሲሆን “ቅዱስ” የሚለው ደግሞ በዕብራይስጥ ክዳሽ፣ በሱርስት ካዲሽ፣ በግዕዝና ዐረብኛ ቅዱስ፣ የሚል ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ በጠቅላላው ደግሞ በግሪክኛ ቢብሎስ(Byblos)፣ በላቲን ስክሪፕቸር(Scripture) የሚል ስም ይሰጡታል፡፡ • በአጠቃላይ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ደግሞ የተለየ፣ የከበረ፣ የተቀደሰ መጽሐፍ ወይም ጽሑፍ ጥራዝ ማለት ነው፡፡
 • 15. 2.2. መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት ዓላማ 1. የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም የፈጠረ እግዚአብሔር መሆኑንና ዓለምን ከመፍጠሩ በፊትም በክብር በአንድነት በሦስትነት መኖሩን እንድናውቅ • ዘፍ 1:1 በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። • ዘፍ 1:26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር • ዮሐ 1:1-4 በመጀመሪያ ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ይህም በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም ሁሉ ያለ እርሱ ምንምን የሆነ የለም። • መዝ 134:6 በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ። • ዳን 4:35 በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል እጁንም የሚከለክላት ወይም። ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም። • ዮሐ 10:17-18 ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።
 • 16. 2. እግዚአብሔር እርሱ ብቻ አምላክ እንደሆነና እርሱን ብቻ እንድናመልከው • ዘጸ 10:2 እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ • ዘጸ 20:2-3፣ ዘዳ 5:6-7 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። 3. የእግዚአብሔርን ባሕርይና ዘላለማዊ ፈቃድ አውቀን በፈቃዱ እንድንመራ • ሮሜ 15:4 የተጻፈው ሁሉ በመታገሳችንና መጻሕፍትን በመታመናችን ተስፋችን እናገኝ ዘንድ እኛ ልንማርበት ተጻፈ • ሮሜ 8:24-25 የሚታየውን ተስፋ ማድረግ ተስፋ አይደለም የማይታየውን ተስፋ ብናደርግ ግን እርሱን ተስፋ አድርገን በእርሱ እንደጸናን መጠን ትዕግስታችን ይታወቃል • ሮሜ 8: 12-14 ወንድሞቻችን ሆይ አሁንም በሥጋችን ሳለን እንደሥጋ ፈቃድ እንኖር ዘንድ አይገባም እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞታላችሁ ነገር ግን በመንፈሳዊ ሥራ የሥጋችሁን ፈቃድ ብትገድሉ ለዘላለም ሕይዎት ትኖራላችሁ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚሠሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡ • ማቴ 22:37-39 ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት • ዮሐ3:16-17 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።
 • 17. 4. ሥጋን ለብሶ የተገለጠው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምነን በስሙም ዘላለማዊ ሕይዎት እንድናገኝ • ዮሐ 20:31 ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል። 5. እግዚአብሔር ኃጢአትን እንጂ ኃጢአተኞችን እንደማይጠላ በንስሐ ወደ እርሱ ከተመለስን ከኃጢአታችን ሁሉ እንደሚያነጻን እንድናውቅ • ማቴ 11:28 እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ፤ ሉቃ 15:7 ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል 6.በተዋሕዶ ዓለምን የማዳኑን ድንቅ ሥራ ለማሳወቅና ለማስገንዘብ • ዮሐ 1:14 ቃልም ሥጋ ሆነ • ገላ 4:4 ቀጠሮው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴቲቱም ተወለደ
 • 18. 7. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ማረጉን ማስረዳትና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መሆኑን ማሳወቅ • መዝ 46:5-6 እግዚአብሔር በእልልታ ጌታችንም በመለከት ድምፅ ዐረገ ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ • ሉቃ 24:51 እየባረካቸውም ራቃቸውም ወደሰማይም ዐረገ • ሐዋ 1:9-11 እነርሱም ወደ እርሱ እያዩ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ከዓይናቸውም ተሠወረ እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል • ማቴ 24ና 25 ስለዳግም ምጽአትና ፍርዱ በስፋት ይናገራል
 • 19. 2.3. የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርያት • መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ሕልውናውንና ፈቃዱን ረቂቅ ባሕርይውን በመጠኑ የምንረዳበት፣ አምላክ ቅዱስ ፈቃዱን የገለጸበት መጽሐፍ ነው፡፡ • መጽሐፍ ቅዱስ በባሕርይው ቅዱስ ነው፡፡ ቅዱስ የሚል ባሕርይ ስንሰጠውም ያለምክንያት አይደለም፡፡ • ስለሆነም፡-
 • 20. 1. አስገኝው እግዚአብሔር ስለሆነ፤ የእግዚአብሔር የሆነ ደግሞ ቅዱስ ነው • ኢሳ 34:16 በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም • ዘጸ 17:14 ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው • ራእ 1:11 የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ --- በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ • ዘሌ 19:2 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ 2. በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሣሱ ቅዱሳን ሰዎች የጻፉት በመሆኑ ቅዱስ ነው • 2ኛ ጴጥ 1:20-21 ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ • ራእ 1:11 የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ --- በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ • ራእ 22:8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ • ነቢያት ሲጽፉ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ እንዲህ በል አለኝ እያሉ ይጽፉ ነበር (ኢሳ ምዕ 30 - 66፤ ኤር ምዕ 1 - 14)
 • 21. • ጸሐፍቱ ከተለያየ የኑሮ ሁኔታና እውቀት ደረጃ የተጠሩ መሆኑም ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡ • ይኸውም፡- ነቢዩ ሙሴ በምድያም የአማቱን(የኢትዮጵያዊውን ዮቶር) በጎች ሲጠብቅ የተጠራ ነው፣ ነቢዩ ዳዊት የአባቱን በጎች ሲጠብቅ፣ እንደነ ነቢዩ ሳሙኤል፣ ጠቢቡ ሰሎሞን፣ ካህኑ ዕዝራ ያሉ ጥበበኞችና ተመራማሪዎች፣ እንደነ ነህምያ ያሉ ጠጅ አሳላፊዎች፣ እንደነ ሉቃስ ያሉ ሐኪሞች እንደነ ቅዱስ ጳውሎስ ያሉ ምሁረ ኦሪት ግን አሳዳጆች፣ እንደነ ጴጥሮስ፣ እንድርያስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብ ያሉ ዓሣ አጥማጆች ወዘተ ተነስተው የጻፉት በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጅ በሰው ሐሳብና ፈቃድ አይደለም፡፡ • - ከዚህም በተጨማሪ መጻሕፍቱ በተለያየ ቦታና ዘመን መጻፋቸው ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መግለጻቸው የመጽሐፍ ቅዱስን ቅድስና ያስረዳሉ ያረጋግጣሉም፡፡
 • 22. 3. የሰውል ልጅ ከመፈጠሩ በፊት ስላለው ነገር በእርግጠኝነት የሚናገር በመሆኑ • ዘፍ 1:1 “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” አለ እንጂ ፈጥሮ ይሆናል፣ የፈጠረ ይመስለኛል አላለም፤ ነቢዩ ሙሴ ይህን የጻፈው 3800 ዓ.ዓ (ቅ:ል:ክ 1700/1300 የሚሉም አሉ/ በፊት ነው) ይህም ዓለም ከተፈጠረ ከብዙ ዘመን በኋላ ጻፈው፡፡ • ዘፍ 12:1 እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ፤ አብርሃም ከሙሴ በፊት ብዙ ዘመናት ይቀድማል ሙሴ ግን በዚያ ዘመን እግዚእብሔር ስለተናገረው ነገር በወቅቱ እንደነበረ አድርጎ አስረግጦ ተናገረ፡፡
 • 23. 4. ወደፊት ስለሚሆነው በእርግጠኝነት በመናገሩ • ኢሳ 7:14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች • ራእ 1:7 እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል • ራእ 22:7 እነሆም፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ 5. ሰውን ወደ ቅድስና የሚመራ በመሆኑ • ራእ 22:7 የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ • ሉቃ 11:28 ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው • ሮሜ 10:17 እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው
 • 24. 6. የሚያነቡትንና የሚሰሙትን ስለሚባርክ • መዝ 118:103 ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ • ራእ 1:3 ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው • 2ኛ ጢሞ 3:16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 7. ክብረ ቅዱሳንን የሚዘክር(የሚናገር) በመሆኑ • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ስለቅዱሳን መላእክት፣ ጻድቃን ሰማዕታት፣ ስለ ቅዱሳት ንዋያት ወዘተ ይናገራል፡፡ • ሉቃ 1:19 እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ • ሉቃ 1:26-27 በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ • መዝ 33:7 የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል • መዝ 33:17 ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው 8. ዘመን የማይሽረው በመሆኑ • መጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ መጻሕፍት ብሉየ መዋዕል ሲሆን ዘመን የማይሽረው ብቸኛ መጽሐፍ ነው፡፡ • ኢሳ 40:8 የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች • ማቴ 24:35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም • 1ኛ ጴጥ 1:25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል
 • 25. 2.4. የቅዱሳት መጽሐፍት የእግዚአብሔር እስትንፋስነት • መጻሕፍተ አምላካውያት የእግዚአብሔር እስትንፋስ ናቸው፡፡ እንዲሁም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉን የፈጠረ የእግዚአብሔር ቃል ነውና እርሱም ክቡርና ከፍጡር ሐሳብም ከፍ ያለ ነው፡፡ ሳዊሮስ ዘእስሙናይ
 • 26. • ራእ 1:11 የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ --- በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ • ራእ 22:8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ • ነቢያት ሲጽፉ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ እንዲህ በል አለኝ እያሉ ይጽፉ ነበር (ኢሳ ምዕ 30 - 66፤ ኤር ምዕ 1 - 14) • ኢሳ 3፡15 የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና--- • ኢሳ 38፡4 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ --- • ኤር 1፡4 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ ----
 • 27. 2.5. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥቅም 1. እግዚአብሔርን የበለጠ ለማወቅና ለመቀደስ • ዮሐ 5:39 እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ • ዮሐ 17:17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። • ኤፌ 5:26 በውኃ ጥምቀትና በቃሉ ይቀድሳት ዘንድ 2. ክፉንና በጎን ለመለየት • መዝ 118:100 አስተዋይ ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ • መዝ 118: 105 ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው • መዝ 118:11 አንተን እንዳልበድል ቃልህን ሰወርሁ • 2ኛ ጢሞ 3:16-17 የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 3. በሥራ መከናወንን ለማግኘት • ኢያሱ 1:8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።
 • 28. 4. እውነትን ለማወቅ • ምሳ 22:19-20 እምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ለአንተ ዛሬ እነሆ አስታወቅሁህ። የእውነትን ቃል እርግጥነት አስታውቅህ ዘንድ፥ ለሚጠይቅህም እውነትን ቃል መመለስ ይቻልህ ዘንድ፥ በምክርና በእውቀት የከበረን ነገር አልጻፍሁልህምን? 5. እግዚአብሔር የገባልንን ርስት ለመቀበል • ሐዋ 20:32 አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ። • ያዕ 1:25 ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል። 6. መንፈሳዊ ውጊያ ለመዋጋት • ኤፌ 6:10-18 በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።…የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
 • 29. 7. የጥበብ ሥጋዊና ጥበብ መንፈሳዊ(የሁሉ) ምንጭ መሆኑን ለመረዳት • የሃይማኖት(ይሁ ቁ: 20፣ 2ኛ ጢሞ 4:7፣ 1ኛ ቆሮ 16:13)፣ የሥነምግባር(ዘጸ 20:7-17፣ ማቴ 5:20፣ ያዕ 2:17)፣ የሥርዓት(መዝ 118:118፣ 1ኛ ተሰ 5:14፣ 2ኛ ተሰ3:6)፣ የሕግ(ዘጸ 20:12-17፣ ማቴ 22:34)፣ የሥራ አመራር(ዘጸ 18:13- 27)፣ የሥራ(ዘፍ 2:15፣ 2ኛ ተሰ 3:8-10)፣ የሕክምና(ዘፍ 50:2፣ ኤር 8:22፣ 2ኛ ዜና 16:12፣ 2ኛ ነገ 20:7፣ ኢሳ 38:21፣ ማር 5:26፣ ቆላ 4:14 )፣ የግብርና(ዘፍ 42፣ 9:20፣ 21:33፣ 1ኛ ነገ 19:19)፣ የከብት እርባታ(ዘፍ 4:2፣ 12:5፣ 13:5- 8፣ 30:29፣ 46:31-32፣ 1ኛ ሳሙ 16:11)፣ የንግድ(ዘፍ 37:30፣ 33:19፣ 1ኛነገ 10:14፣ ሕዝ 27:1-25፣ ሐዋ 16:13-15)፣ የምህንድስና(ዘፍ 6:13-18፣ ዘጸ 25:21፣ ዘጸ 31:1-11)፣ የአናጺነት(ሕዝ 40:3፣ ራእ 21:15፣ 1ኛ ቆሮ 3:10፣ 2ኛ ዜና 1:3-14፣ 7:11፣ 34:11)፣ የግንበኝነት (ዘፍ 11:1-9)፣ የአንጥረኛና ቀጥቃጭነት (ዘኁ 31:21-23፣ ዘጸ 31:1፣ 36:1)፣ የልብስ ሠሪ(ዘጸ 35:25-35)፣ የሸክላ ሠሪ(ዘጸ 1:14፣ ኢሳ 41:25፣ ማቴ 27:7፣ ኤር 18:3፣ ሮሜ 9:21)፣ የቁርበት ፋቂ(ሐዋ 9:43)፣ የገድላት(ማቴ 23:35፣ ዕብ 11:4፣ ዳን 3:1፣ ሐዋ 7:54-60)፣ የተአምራት(2ኛ ነገ 6፡17፣ ዮሐ 2፡1-11፣ ሐዋ 14፡8-13፣ ሐዋ 5፡15-16)፣ የድርሳናት(ሉቃ 1:3፣ ሐዋ 1:1) ሁሉ መሠረት ነው፡፡
 • 30. 3.1. የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ዳሰሳና አከፋፈል መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን /46/ የሕግ /5/ የታሪክ/17/ የመዝሙርና የጥበብ/8/ የትንቢት/16/ ሐዲስ ኪዳን /35/ የወንጌል/የምሥራች/ /4/ የታሪክ /1/ መልዕክታት /21/ የሥርዓት /8/ የትንቢት/የራእይ/ /1/ ምዕራፍ 3 - የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት
 • 31. 3.2. ሁለቱ ኪዳናት 3.2.1. የኪዳንና የቃል ኪዳን ትርጉም • ኪዳን ማለት፡- “በተለያዩ ወገኖች መካከል የሚደረግ ውል፣ ቁም ነገር፣ የፍቅርና የአንድነት፣ ማሓላ፣ ሰላማዊ ሕግ፣ ሁለቱን ወገን አንድ የሚያደርግ፣ ስለረብና ስለጥቅም በተስፋ የቆመ የተጻፈ ሥርዓት፣ ቢያፈርሱት ጉዳትና ጠብ የሚያመጣ ጥቅም የሚያሳጣ” ማለት ነው፡፡ /አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ / • ኪዳን ስምምነት ሲሆን ቃል ኪዳን በቃል የተገባ ስምምነት ማለት ነው፤ • ቃል ኪዳን በብሉይ ኪዳን ወደ 280 ጊዜ በሐዲስ ኪዳን 33 ጊዜ ተጠቅሷል፤ • ቃል ኪዳን በሁለት ወይም ከሁለት በላይ በሆኑ ወገኞች መካከል የሚደረግ ስምምነት ነው፤ • ይህ ውል/ስምምነት/ ሁለቱ ወገኖች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስረዳ ነው፤ • ለኪዳን የሚያስፈልጉ አካላት፡- • ውል ሰጭ(መሐላውን የማለ) ቃል ኪዳን የገባ • ውል ተቀባይ(የተማለለት) ባለ ቃልኪዳን • ውሉ(መሐላው) • ምልክት
 • 32. በስምምነቱ ወቅት የቃል ኪዳንን የማጽደቅ ሒደት ያስፈለገው 1. ቃል ኪዳኑን የሚቀበሉት ተስፋው ተጨባጭ እንዲሆንላቸው፤ • 2ኛ ቆሮ 5፡5 የመንፈሱን መያዣ ሰጠን 2. ቃል ኪዳን እንዳያፈርሱ ለመጠበቅ • መዝ 88፡34-35 ኪዳኔንም አላረክስም፥ ከከንፈሬም የወጣውን አልለውጥም፤ ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ። 3. ሁለቱም ወገን ማድረግ የሚገባቸውን ለማሳየትና በፍቅርና በሰላም እንዲኖሩ፤ 4. አንዱ ለሌላው ሊያደርገው ያሰበውን መልካም ነገር ለመግለጥ፤
 • 33. የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን ቃል ኪዳንን ንጽጽር • የብሉይ ኪዳን ቃል ኪዳን • የመጀመሪያውነ ቃል ኪዳን ከአዳም ጋር አደረገ፤ • ይህም ቃል ኪዳን የጸጋው ሥጦታ ነው፤ • መለኪያው የእግዚአብሔርን ትእዛዛዘ መጠበቅ ነው፤ • የቃልኪዳኑ ምልክት/ማኅተም/ የእውቀት ዛፍ ነበረች፤ • ፍጻሜ/ግብ/ በትንሽ ጊዜ/ጊዜያዊ/ መታዘዝ ዓለማዊ ሕይወት ማግኘት፤ • የታተመው በእንስሳት ደም ነው፤ • ቃል ኪዳኑ ከሞት የማያድን ነበር፤
 • 34. • የሐዲስ ኪዳን ቃል ኪዳን • የተመሠረተው የአበውን ተስፋ ለመፈጸም ነው፤ • መነሻው የእግዚአብሔር ቸርነትና ለሰው ያለው የማይለወጥ ፍቅር ነው፤ • መሥራቹ ራሱ ክርስቶስ ነው፤ • ቃል ኪዳኑ የጸናው በክርስቶስ ደም/መስዋዕትነት/ ነው፤ • ቃል ኪዳኑ የዘላለም ሕይወትን የሚያስገኝ ነው፤ • የቃል ኪዳኑ ፍጻሜ/ግብ/ ከእግዚአብሔር ጋር ተዋሕዶ ዘላለማዊ ሕይወትን አግኝቶ ከክርስቶስ ጋር ሕያው ሆኖ መኖር፤
 • 35. ብሉይ ኪዳን ሐዲስ ኪዳን ጥንታዊ ፣ ቀዳማዊ ውል/ስምምነት/ አዲስ ውል/ስምምነት/ ውጫዊ/አፍአዊ/ ውስጣዊ ነው የሰውን ኅሊና ፍጹም ሊያደርግ ያጣውንም ነጻነት ሊመልስ አልቻለም ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አዋሕዷል፣ ነጻነታችን ተመል ሷል ፍጹም ይቅርታን አላስገኘም ፍጹም ይቅርታን ያስገኘ ነው በፍርሃት የሚከበር ነበር በፍቅር የሚከበር ነው
 • 36. ሁለቱ ኪዳናትን ስናጠቃልል በብሉይ ኪዳን አትብላ የሚልና ይህንም አፍርሶ የበላው አዳም ቢሞት በፈለገው ለማካስ በሐዲስ ኪዳን ብላ የሚልና ፍጹም የድኅነት መንገድ ነው፡፡ ታዲያ በልተን መዳን እንዴት አንችልም? ኢሳ 55፡1 እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ ---ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች፡፡ ዮሐ 6፡54-56 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፤ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና፤ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።
 • 37. 3.2.2 ብሉይ ኪዳንና ኦሪት • ምንነቱና አመሠራረቱ ብሉይ ኪዳን ሕገ ልቡና /ከአዳም-ሙሴ/ 3856 ዘመን ሕገ ኦሪት /ከሙሴ-ክርስቶስ/ 1644 ዘመን
 • 38. • ሀ. ሕገ ልቡና ምንነቱና አመሠራረቱ፡- ከእግዚአብሔር ለሰው በጥንተ ተፈጥሮ በልቡናው ተቀርጾ ከሰውነቱ ጋር ተዋሕዶ የሚኖር ነው፤ • ሕገ ልቡና ጠባያቸው ባላደፈባቸው ቅዱሳን መላእክት ተጠብቆ ይኖራል፤ ለእነሱ የተጻፈ ሕግ አያስፈልጋቸውም በንጽሕና ይኖራሉና፤ • ዓላማ - ሕገልቡና ለሰው የተሰጠው እንደዚሁ በንጽሕና እና በቅድስና በመኖር ሃይማኖቱን አውቆ ፈጣሪውን በመፍራት እንዲኖር ነበር፤ • ሄኖ 19፡22 እንደ መላእክት ንጹሐን ጻድቃን ሁነው ይኖሩ ዘንድ ነው እንጂ ሰው በእንዲህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም በጥቁር ቀለምና በቀይ ቀለም ጽፈው ሃይማኖታቸውን ሊያጸኑ ሰው እንግዲህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም ነበርና • ሰው በአእምሮ ጠባይዕ ዐውቆ እግዚአብሔርን በማምለክ የፈጣሪውንም ፈቃድ በመፈጸም የኖረበትና የሚኖርበት ሕግ ነው፤ • ሮሜ 2፡12-15 ያለሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለሕግ ይጠፋሉና... እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ
 • 39. • ለ. ሕገ ኦሪት ምንነቱና አመሠራረቱ፡- ከእግዚአብሔር በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለሕዝበ እሥራኤል የተሰጠ ነው፤ • ዓላማ -ሕገ ኦሪት ሰወች በተጻፈ ሕግ መመራት የጀመሩበት ጊዜ ነው፤ ይህም በሕገ ልቡና ሁሉም ወደ ድኅነት መድረስ ስላልቻሉ በሕግ እየተመሩ ወደ መዳን ይደርሱ ዘንድ አጋዥ ሆኖ የተሰጠ ሕግ ነው፤ • ሕገ ኦሪት በቃል በመናገርና በጽሑፍ በመቅረጽ እግዚአብሔር በነቢያቱ አማካኝነት ለሕዝቡ የተሰጣቸውን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ • የአምልኮት ሥርዓታቸውን ሁሉ የሚፈጽሙት በተጻፈ ሕግ ነው፤ • በአጠቃላይ ከሙሴ እስከ ክርስቶስ ያለውን ዘመን ይይዛል፤
 • 40. መጻሕፍቱ እንዴት ይጠናሉ? • የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጥናት 1. የሕግ መጽሐፍት ጥናት፤ • በመጀመሪያ በአጠቃላይ ስለ እነዚህ የመጽሐፈት ክፍልና ብዛት፤ • የመጽሐፉ ጸሐፊ ስምና እንደ አስፈላጊነቱ የጸሐፊው ታሪክ በአጭሩ፤ • የመጽሐፉ ስያሜ፣ የተጻፈበት ቦታና ዘመን፤ • የተጻፈበት ዓላማ፤ • የመጽሐፉ አጠቃላይ የምዕራፍ ብዛት፤ • የመጽሐፉ ዋና ዋና ይዘትና ታሪክ፤ ከሌሎች መጻሕፍት ጋር ያለው ግንኙነት ካለ(በተለይ ለሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)፤ 2. የብሉይ ኪዳን የታሪክ መጻሕፍት 3. የመዝሙርና የጥበብ መጻሕፍት 4. የትንቢት መጻሕፍት
 • 41. ከሕግ መጻሕፍት አጠናን ምሳሌ • የሕግ መጻሕፍት ከአራቱ የብሉይ ኪዳን ክፍሎች አንዱ ነው፤ • የሕግ መጻሕፍት የሚባሉተተ ነቢዩ ሙሴ የጻፋቸው አምስቱ መጻሕት ናቸው /ዘፍ፣ ዘጸ፣ ዘሌ፣ ዘኁ፣ ዘዳ/ በዚህም አምስቱ የሙሴ መጻህፍት ይባላሉ፤ • ብሔረ ኦሪት እየተባሉም ይጠራሉ፤ • ኦሪት የሚለው ቃል የሱርስት ሲሆን ትርጉሙም ሕግ ማለት ነው፤ • እንዲሁም በዕብራይስጥ ቶራ፣ በግሪክ/ፅርዕ/ ኖሞስ = ሕግ ማለት ነው፤ • አምስቱም መጻሕፍት እንደይዘታቸው የተለያየ ስያሜ አላቸው፤ • አምስቱ የሙሴ መጻሕፈት ስያሜና ዋና ዋና ይዘት አጠናን፡- • 1. ኦሪት ዘፍጥረት፡- ኦሪት ዘልደትም ይባላል፤ • መጽሐፉ የሥነፍጥረትን አፈጣጠር፣ አጀማመር፣ አመጣትና ልደት የሚያስረዳ በመሆኑ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፣ • ከሕግ መጽሐፍት የመጀመሪያው ነው፤ • ዓላማው፡- ከፍጥረት አንስቶ እሥራኤላውያን ወደ ግብጽ እስከወረዱበት ጊዜ ድረስ ያለውን የመለኮታዊ መገለጥ ታሪክ በጭሩ ማቅረብ ነው፤ • ስለዓለም አፈጣጠር፣ ስለሰው አፈጣጠር፣ እግዚአብሔር ከሰው ጋር ስለመሰረተው ቃል ኪዳን፣ ሰው በኃጢአቱ ስለመውደቁ፣ ስለ ቃል ኪዳንና ስለ ቀደሙት አባቶች አኗኗር ማሳየት ነው፤
 • 42. • ኦሪት ዘፍጥረት $ ምዕራፎች ሲኖሩት ዋና ዋና ይዘቱ እንደሚከተለው ይቀርባል፡ • 1. ምዕ 1-2 ስለ ሥነፍጥረት • 2. ምዕ 3-4 ስለ ሰው ፈተናና ውድቀት • 3. ምዕ 5-9 የጥፋት ውኃና የኖኅ ቤተሰቦች ድኅነት • 4. ምዕ 10-11 የዓለም ሕዝብ ትውልድ ዝርዝርና የቋንቋ መለያየት • 5. ምዕ 12-23 የአብርሃም ታሪክ • 6. ምዕ 24-26 የይስሐቅ ታሪክ • 7. ምዕ 27-36 የያዕቆብ ታሪክ • 8. ምዕ 37-50 የዮሴፍ ታሪክ • ሌሎችንም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በዚሁ መልኩ ማጥናት ይቻላል
 • 43. 3.2.3. ሐዲስ ኪዳንና ወንጌል • አዲስ ኪዳን ምንድን ነው? • ሐዲስ የግእዝ ቃል ሲሆን በአማርኛ ደግሞ አዲስ ይላል • አዲስ ውል ስምምነት መሓላ ማለት ነው፤ • የብሉይ ኪዳን ፍጻሜ ነው፤ የተመሠረተውም በክርስቶስ ደም ነው፤ • ሐዲስ ኪዳን ስንልም ከክርስቶስ መወለድ እስከ ዳግም ምጽአት ያለውን ያሳያል፤ • የሐዲስ ኪዳን ክፍል በጠቅላላ በተለያየ ይዘትና አቀራረብ ይጻፉ እንጂ ስለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናሩ በመሆኑ ወንጌል ተብሎ ይጠራል፤ ወንጌል ማለትም የምሥራች ማለት ነው፤ • አስቀድሞ ነቢያት የተነበዩት የትንቢት ቃል አማናዊ ሆኖ የተሠጠበት ክፍል ነው፤ • አዲስ ኪዳን አካል፣ አማናዊና ፍጻሜ ነው፤ • የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ክፍፍልና አጠናን፡- • አንዳለፈው ይቀጥላል
 • 44. የቤት ሥራ • ቡድን 1 - የሕግ መጽሐፍትና ራእይ ዮሐንስ • ቡድን 2 - የመዝሙርና የጥበብ እና የታሪክ መጽሐፍትን አጠቃላይ ዳሰሳና አከፋፈል አቆጣጠር • ቡድን 3 - የትንቢት- በመጀመሪያ አጠቃላይ ስለመጽሐፍቱ አቆጣጠርና አከፋፈል በመቀጠል ዐበይት ነቢያትን በዝርዝር • ቡድን 4 - የምሥራች/የወንጌል/ • ቡድን 5 - የሐዋርያት ሥራና የሥርዓት መጻሕፍት • ቡድን 6 - መልእክታት - አጠቃላይ ስለመልእክታቱ ከዚያም 14ቱን መልእክታት ዋና ዋና ይዘትና ጠባዕያት
 • 45. 2.3. የቅዱሳት መጻሕፍት አከፋፈል • 2.3.1 የብሉይ ኪዳን አከፋፈል • 2.3.2 የሐዲስ ኪዳን አከፋፈል • (በምዕራፍ 3 በ3.1 የቀረበ ሲሆን በቀጣይ ባለው ምዕራፍ የበለጠ ይዳሰሳል)
 • 46. ምዕራፍ 4 - የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክና አመጣጥ • መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጻፈ ብሉየ መዋዕል መጻሕፍተ ርዕስ ነው፡፡ • ለዓለም ሥነጽሑፍን ያስተማረ ዓለምን በቋንቋ ያናገረ ብቸኛ መጽሐፍ ነው፡፡
 • 47. 4.1. የቅዱሳት መጻሕፍት አጻጻፍ ታሪክ • 1. የተጻፉበት ዘመን • መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ዘመንና ቦታ የተጻፈ እንጂ በአንድ ጊዜ የተገኘ አይደለም፤ • የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ1400-400 ቅ.ል.ክ የተጻፉ ሲሆን ጸሐፍቱም 40 ያክል ቅዱሳን ሲሆኑ በጠቅላላው 46 መጻሕፍትን ይይዛል፡፡ • የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ ከ45-96 ዓ.ም በ8 ጸሐፍት የተጻፉ ሲሆኑ በቁጥርም 35 ያክል ናቸው፡፡ • ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በመጀመሪያ የተጻፈው መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን ይኸውም በ 1ሺ 486 ዓ.ዓ ነው(ቅ.ል.ክ 4ሺ 14 ዘመን ያስቆጠረ መጽሐፍ)፡፡ • በመጨረሻ የተጻፈው ደግሞ ራእየ ዮሐንስ ሲሆን ዘመኑም ከ96-98 ዓ.ም ነው፡፡ ይህን እንኳ 100 ዓ.ም ብለን ብንቆጥር መጽሐፍ ቅዱስ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ 4ሺ 114 ዓመታትን የፈጀ የእግዚአብሔር ፈቃድና የቅዱሳን ሥራ የተገለጠበት ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡ • የሁለቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች(ብሉይና ሐዲስ) በተለያዩ ዘመን በተነሱ ቅዱሳን ይጻፉ የቱንም ያክል የተራራቀ ዘመን ይኑራቸው እንጂ አንድ ዓላማ ይዘው ያለምንም የሐሳብ ተፋልሶና ግጭት የተጻፉ ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው፡፡
 • 48. • ይህም የሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ የተገለጠባቸው መሆኑን ያስረዳል • ከመጽሐፈ ሄኖክ ቀጥሎ ከብሉይ ኪዳን ቀድሞ የተጻፈው መጽሐፈ ኢዮብ ሲሆን የተጻፈውም እሥራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ሳይወጡ ነው፡፡ • እሥራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ከወጡ በኋላ በ3ሺ 843 ዓ.ዓ ኦሪት ተጻፈ • በ4ሺ 407 ዓ.ዓ ሳኦል ነገሠ በዚህ ጊዜ መጽሐፈ ነገሥት ተጀመረ • በ4ሺ 447 ዓ.ዓ ሳኦል ሞቶ ዳዊት ነገሠ በዚህ ጊዜ መዝሙረ ዳዊት ተጻፈ • በ4ሺ 481 ዓ.ዓ ዳዊት ሞቶ ሰሎሞን ነገሠ በ4ኛው ዓመት ኢትዮጵያዊቱ ንግሥት ሳባ ወደ ጠቢቡ ሰሎሞን ሄደች፡፡
 • 49. 2. መጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቦታና ቋንቋ ስለመጻፉ ማሳያ ሰንጠረዥ ተ.ቁ የመጽሐፉ ስም የተጻፈበት ቦታ ቋንቋ 1 የኦሪት መጻሕፍት በሲና ምድር ዕብራይስጥ 2 መጽሐፈ ኢያሱ ምድረ ከነዓን(እሥራኤል) ዕብራይስጥ 3 መጽሐፈ አስቴር ፋርስ ዕብራይስጥ 4 ትንቢተ ዳንኤል ባቢሎን አረማይካ 5 ማቴዎስ ወንጌል በሶሪያ ውስጥ ባለች አንጾኪያ ከተማ ዕብራይስጥ/አረማይክ/ 6 ማርቆስ ወንጌል ሮም ሮማይስጥ(ላቲን) 7 ሉቃስ ወንጌል አካይያ ጽርዕ(ግሪክ) - ዮናኒ(ዲያሌክት) 8 ዮሐንስ ወንጌል፣ የዮሐንስ መልእክታትና ራእይ ዮሐንስ ፍጥሞ ደሴት ጽርዕ(ግሪክ) 9 1ኛ ተሰሎንቄ አቴና 10 2ኛ ተሰሎንቄ በቆሮንቶስ ሳለ 11 ኤፌሶን፣ ፊልጵስዩስ፣ ቆላስይስና ወደ ፊልሞና በሮም/1ኛ እሥራቱ / 12 1ኛ ጢሞቴዎስ በሎዶቂያ/ከሮም እሥር ቤት እንደወጣ/ 13 2ኛ ጢሞቴዎስ በሮም ወኅኒ ቤት/2ኛ እሥራቱ/ 14 ዕብራውያን በመጀመሪያው የሮም እሥራቱ/ኢጣልያ 15 የሥርዓት መጻሕፍት ሱርስት/የሶርያ ቋንቋ/፣ ግሪክ የሚሊ አሉ
 • 50. 2. መጻሕፍቱ ወደ ኢትዮጵያ እንዴት መጡ፡- ሀ. የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አመጣጥ • ንግሥተ ሳባ ወደ ጠቢቡ ሰሎሞን መሄድና ቀዳማዊ ምኒልክን(በአረብኛ እብነ እልኪም/እብነ ሐኪም/ በማለት ይጠሩታል ይህም የጥበበኛ ልጅ ማለት ነው፡፡) ፀንሳ መመለሷ ከዚያም 22 ዓመት ሲሞላው ወደ አባቱ ሄዶ ለሦስት ዓመት ከተቀመጠ በኋላ እሥራኤላውያን ለሁለት ንጉሥ መገዛት አይቻለንም( የበኵር ልጅ ክቡር ስለሆነ) አንግሥና ወደ እናቱ ሀገር ላከው ባሉት ጊዜ አንግሦ ከመጽሐፈ ሄኖክ አንስቶ ጠቢቡ ሰሎሞን እሰከጻፋቸው ያሉ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ይህን ተርጉመው የሚያስተምሩ 318 ሊቃውንትን ጨምሮ ላከው፡፡ በዚያን ጊዜ በፈቃደ እግዚአብሔር ታቦተ ጽዮንም መጥታለች፡፡ ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር የመጡ ሊቃውንትም ቅዱሳት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ በመተርጎም የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራ ሠርተዋል፡፡ ይህም ቅ:ል:ክ 980 ዓመት ነው፡፡ ለዚህ ምሥክሩም ሲተረጉሙ በቁሙ የዕብራይስጥ ቃላትን መተዋቸው ነው፡፡ የኸውም ኤሎሄ፣ አዶናይ፣ ጸባኦት የመሳሰሉትን ማለት ነው፡፡ (ሰሎሞን ወሲራክ ትርጓሜ መግቢያና መጽሐፈ ምሥጢር አበጊዮርጊስ ዘጋስጫ) ይህች ንግስት መሄዷ ሌላ የሚያስተምረን ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና አምልኮ ሥርዓት የነበረች መሆኑን ነው ይኸውም የተናገረችው የእመነት ንግግርና በኋላም ክርስቶስ ስለ እሷ የተናገረው ንግግር ነው፡፡
 • 51. • 1ኛ ነገ 10:9፣ 2ኛ ዜና 9:8 አንተን የወደደ፥ በእሥራኤልም ዙፋን ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን፡፡ • ማቴ 12:42 ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ። • ኢትዮጵያ በሕገ ልቡና አምልኮ ሥርዓት ታመልክ እንደነበር ሌሎች መረጃዎችን እንጥቀስ፡- • ኢትዮጵያ በኖኅ የልጅ ልጆች በሆኑት የካም ልጆች ኩሽ/ኢትዮጲስ/፣ ሳባ እና አቢስ መሰየሟ • ይኸውም በኩሽ የኩሽ ምድር፣ በኢትዮጲስ(የኩሽ ሁለተኛ ስሙ) ኢትዮጵያውያን፤ በሳባ የሳባ ምድር፣ በአቢስ አቢሲኒያውያን መባሏ ይህም የእነሱን እምነት መቀበሏን የሚያስረዳ ነው፡፡ • ኢትዮጵያዊው መልከ ጼዴቅ አበብዙሃን አብርሃምን መባረክ (ዘፍ 14:17-19: ዕብ 7:1-2)፤ መልከ ጼዴቅ - ትውልዱ ከአብርሃም ወገን የማይቆጠር፣ ክህነቱ ከሌዋዊ ያልሆነ፣ ጥንቱ ፍጻሜው ለሌዋውያን ያልተገለጠ፣ • የስሙ ትርጓሜ በግእዝ መልከጼዴቅ ማለት ፤ለከ ገዛ፣ ጻድቅ- እውነተኛ ማለት ሲሆን ይህም የጽድቅ ንጉሥ የእውነት ንጉሥ ማለት ነው፡፡ ይህን ካልን ግእዝ ደግሞ የኢትዮጵያ ቋንቋ እንጅ የማንም አይደለም፡፡ • (የዕሥራ ምዕት በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ(VCD)-ማኅበረ ቅዱሳን)
 • 53.
 • 54. • ከሰሎሞን በኋላ የተጻፉ መጻሕፍት - • ከቀውስጦስ ታሪክ መጻሕፍ ምስክር እናመጣለን በ4ሺ 905 ዓ.ዓ እሥራኤል ተማርከው ፋርስ ባቢሎን ወረዱ፡፡ በዚያን ጊዜም በኢትዮትዮጵያ ያሉ ሊቃውንት ከንጉሡ ጋር ተማክረው እንዲህ ሲሉ የጥያቄ መለዕክት ላኩ “የኛም የእናንተም አባቶች ነቢያት የጻፏቸው መጻሕፍት ተቃጠሉን ወይስ ድነዋል? እናንተስ እንደምን አላችሁ? ለጣዖት ትሰግዳላችሁን? ሰንበትንስ ሻራችሁን?” የሚል ነበር፡፡ • እነዚያም ይህን መልዕክት በሰሙ ጊዜ እዲህ ብለው መልሰዋል “እኛ በእነ ዳንኤል ጸሎት የአብርሃም ፈጣሪ ጠብቆን ደህና ነን፡፡ መጻሕፍቱን ግን እኛ እንዳንፈልጋቸው በምርኮ በመከራ ነው ያለን፡፡ እናንተ ግን በጸጥታ በደስታ ነውና ያላችሁት ኢየሩሳሌም ወጥታችሁ ፈልጓቸው፡፡ ነገር ግን ከተማረክነ በኋላ ዳንኤል ከእግዚአብሔር አግኝቶ የጻፈውን መጻሕፍ ጽፈን ልከንላችኋልና ተቀበሉ” ብለው መጻሕፈ ዳንኤልን ልከውላቸዋል፡፡ • ይህም መጻሕፍ የመጣ አይሹር/አይዙር/ የሚባል የኢትዮጵያ ንጉሥ ስለ ዘመዶቹ ስለ እሥራኤል ወደ ፋርስ ንጉሥ ወደ ዳርዮስ አማላጅነት በላከው ሰው እጅ ነው፡፡ ይህንንም መጻሕፈ ዳንኤልን ተቀብለው በሰሎሞን ጊዜ ከአባቶቻቻን ጋራ ከመጡ መጻሕፍት ደርበውታል፡፡
 • 55. • በ4ሺ 975 ዓ.ዓ እሥራኤል ከባቢሎን ምርኮ ተመልሰው ዘሩባቤል ነገሠ፡፡ ንጉሥ ዘሩባቤልም ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥ እንዲህ ሲል መልዕክት ላከ “ሰላም ላንተ ይሁንና ስለ እግዚአብሔር ብለህ የለመንኩህን ስማኝ ከኢየሩሳሌም ጥፋት አስቀድሞ ነቢያት የጻፏቸው መጻሕፍት በአያትህ በሰሎሞን ልጅ በምኒልክ መንግሥት መጥተው ባገርህ አሉና ጽፈህ ላክልኝ ብዬ ባባቶቻችን ፈጣሪ በከበረ ስሙ እማልድሃለሁ እኔም ወደ እናተ ያልመጡትን ከኛ ዘንድ ያሉትን መጻሕፍት እልክልሃለሁ ይህ ላንተም ለእኔም ደግ ነው” ብሎ ላከ፡፡ • የኢትዮጵያ ንጉሥም የዘሩባቤልን መልዕክት በሰማ ጊዜ ካህናቱን ጠርቶ “በሀገራችን ያሉ መጻሕፍተ ነቢያትን ጽፋችሁ አምጡ” ብሎ ሁለት ሽህ ወቄት ወርቅ ለስንቃቸው ሁለት መቶ ወቄት ወርቅ ለንጉሡ እጅ መንሻ ሰጥቶ ሰደዳቸው፡፡ እነሱም መጻሕፍቱንም እጅ መንሻውንም ይዘው ሄደው ለንጉሡ ሰጥተው በዘመኑ ካሉ ከደቂቀ ነቢያት ተገናኝተው ወደ እኛ ያልመጡትን መጻሕፍት ጽፈው ይዘው ተመልሰዋል፡፡ ይገርማል ኢትዮጵያውያን ከደቂቀ ነቢያት ተባርከው ሲመጡ የተመረጠ እድል ይሉሀል እንዲህ ነው፡፡
 • 56. • ኢትዮጵያ በሕገ ኦሪት አምልኮ ሥርዓትን ትፈጽም የነበረ መሆኑ ደግሞ መጻሕፍቱ በሐገራችን ከመኖራቸውም ባሻገር ተተርጉመው ለአገልግሎት የዋሉ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ይህ በመሆኑም ኢትዮጵያውያን በኦሪቱ ሥርዓት እጅ ሊነሡ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር፡፡ ለዚህም 1. ነቢዩ ሶፎኒያስ ትንቢት ተናግሯል፡፡ ይኸውም ከኢትዮጵያ ወንዝ ማዶ የሚሰግዱልኝ የተበተኑት ልጆቼ መባዬን ይዘው ይመጣሉ፡፡ ሶፎ 3:10 • 2. ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ(ባኮስ/አቤላክ) ወደ ኢየሩሳሌም ሊሰግድ ሄዶ ሰግዶ በሚመለስበት ጊዜ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ እያነበበ መገኘቱ በራሱ ሁለት ጭብጥ ያስረዳል፡፡ ይህም የነቢያት መጻሕፍት ወደ ኢትዮጵያ ቋንቋ(ግእዝ) መተርጎማቸውን በሌላ መልኩ ደግሞ ኢትዮጵያ በሕገ ኦሪት አምልኮ ሥርዓት የነበረች መሆኑን፡፡ ሐዋ 8:26-ፍጻ • ልብ በሉ! በምኒልክ ዘመን የመጡ ሌዋውያን መጻሕፍትን ወደ ግእዝ ባይተረጉሙልን ኖሮ ይህ የኢትዮጵያ ሰው ወደ ኢየሩሳሌም ሊሰግድ እንዴት ይሄድ ነበር? በአይሹር(አይዙር) ዘመንስ የነቢያት መጻሕፍት ባይመጡልን ኑሮ ይህ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የነቢዩ ኢሳይያስን መጻሐፍ የት ያገኘው ነበር?
 • 57. • ኢትዮጵያ በሕገ ኦሪት ትመራ እንደነበር ሌሎች ማስረጃዎች፡- • ቀዳማዊ ምኒልክ ከኢየሩሳሌም ሲመለስ ታቦተ ጽዮንን፣ ካህናተ ኦሪትንና ቅዱሳት መጻሕፍትን ማምጣቱ • በኢትዮጵያ የሕገ ኦሪት መስዋዕት ታዘጋጅ እንደነበር ሕያው የሆኑ አሻራዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- አክሱም ጽዮን(ትግራይ)፣ ጣና ቂርቆስ፣ መርጡለማርያም(ምሥ/ጎጃም)፣ ተድባበ ማርያም(ደ/ወሎ)ና ብርብር ማርያም(ደቡብ ሕዝቦች) ይጠቀሳሉ፡፡ • የኢትዮጵያውያን ሕዝብ ሥርዓት ከእሥራኤላውያን ጋር መመሳሰሉ(ሕያው አሻራዎች) • ለምሳሌ፡- የወንድ ልጅ የግዝረት ሥርዓት፣ የሠርግ ሥርዓት፣ የማይበሉ እንስሳት፣ የቀዳሚት ሰንበት አከባበር፣ የበዓላት ሥርዓት፣ የአለባበስ ሥርዓትና ሌሎችም • ኢየሩሳሌም ያለን የዴር ሱልጣን ገዳም • 1ኛ ነገ 10:13 ንጉሡም ሰሎሞን፥ በገዛ እጁ ከሰጣት ሌላ፥ የወደደችውን ሁሉ ከእርሱም የለመነችውን ሁሉ ለሳባ ንግሥት ሰጣት እርስዋም ተመልሳ ከባሪያዎችዋ ጋር ወደ ምድርዋ ሄደች።
 • 58. • ኢትዮጵያ በሕገ ኦሪት ትመራ እንደነበር ሌሎች ማስረጃዎች፡- • ቀዳማዊ ምኒልክ ከኢየሩሳሌም ሲመለስ ታቦተ ጽዮንን፣ ካህናተ ኦሪትንና ቅዱሳት መጻሕፍትን ማምጣቱ • በኢትዮጵያ የሕገ ኦሪት መስዋዕት ታዘጋጅ እንደነበር ሕያው የሆኑ አሻራዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- አክሱም ጽዮን(ትግራይ)፣ ጣና ቂርቆስ፣ መርጡለማርያም(ምሥ/ጎጃም)፣ ተድባበ ማርያም(ደ/ወሎ)ና ብርብር ማርያም(ደቡብ ሕዝቦች) ይጠቀሳሉ፡፡ • የኢትዮጵያውያን ሕዝብ ሥርዓት ከእሥራኤላውያን ጋር መመሳሰሉ(ሕያው አሻራዎች) • ለምሳሌ፡- የወንድ ልጅ የግዝረት ሥርዓት፣ የሠርግ ሥርዓት፣ የማይበሉ እንስሳት፣ የቀዳሚት ሰንበት አከባበር፣ የበዓላት ሥርዓት፣ የአለባበስ ሥርዓትና ሌሎችም • ኢየሩሳሌም ያለን የዴር ሱልጣን ገዳም • 1ኛ ነገ 10:13 ንጉሡም ሰሎሞን፥ በገዛ እጁ ከሰጣት ሌላ፥ የወደደችውን ሁሉ ከእርሱም የለመነችውን ሁሉ ለሳባ ንግሥት ሰጣት እርስዋም ተመልሳ ከባሪያዎችዋ ጋር ወደ ምድርዋ ሄደች።
 • 59. • የቅዱሳት መጻሕፍት ማሰረጃዎች ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ከ40 ጊዜ በላይ የተጠቀሰች ቅድስት ሀገር ናት፡፡ መዝ 67:31፣ አሞጽ 9:7፣ ሐዋ 8:26 ደግሞ በሕገ አምልኮ እንደምትኖር ያስረዳሉ፡፡ • (የዕሥራ ምዕት በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ(VCD)- ማኅበረ ቅዱሳን) • ነቢዩ ሙሴ ኢትዮጵያዊቱን ሲፓራን ማግባቱ (ዘኁ 12:1-16) ኢትዮጵያውያን በሕገ አምልኮ ስለሚመስሉት ነው፡፡ እህቱ ማርያምና ወንድሙ አሮን በተቃወሙት ጊዜ እግዚአብሔር መቆጣቱም ለዚህ ነው፡፡ • ዘኁ 12:8-9 በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አልፈራችሁም? አለ እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ። • ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ለነቢዩ ኤርምያስ ደቀ መዝሙር ለመሆን የበቃው በእምነቱ ነው፡፡ • ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋት ትንቢት በመናገሩ ወገኖቹ ወደ መጸዳጃ ጉድጓድ የጣሉትን ኢትዮጵያዊው አቤሜልክ ግን ንጉሡን ማልዶ ከጉድጓድ እንዲወጣ አደረገው፡፡ (ኤር 38:2-13) • እንግዲህ እነዚህ ሁሉ የሚያስረዱን መጻሕፍቱ ተተርጉመው ለአገልግሎት የዋሉ መሆኑን ነው፡፡
 • 60. • በ5ሺ 242 ዓ.ዓ በጥሊሞስ ነገሠ(ግብፅ - እስክንድሪያ) እርሱም ዓለምን አንደ ገል ቀጥቅጦ እንደሰም አቅልጦ ገዝቷት ነበርና አሁንስ ምን ቀረኝ ባለ ጊዜ አማካሪዎቹ መጽሐፍተ ብሉያትን አላስተረጎምክም አሉት፡፡ ንጉሱም ወደ ኢየሩሳሌም ልኮ 72 መተርጉማንና መጻሕፍተ ብሉያት ተልከውለት በ284 ቅ.ል.ክ ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ አስተርጉሟል፡፡ ይህም ሁለተኛው ትርጉም መሆኑ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የግዕዙን የኢትዮጵያን ትርጉም ሁለተኛው እንደሆነ አድርገው የሚናገሩ ቢኖሩም ይህን ታሪክ ለማፋለስ ጥረዋልና እንደገና እንዲያጠኑት እንጋብዛቸዋለን፡፡
 • 61. ለ. የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት አመጣጥ • በሦስቱ ሕግጋት ማለትም በሕገ ልቡና በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል ጸንታ የኖረች ከዓለም ብቸኛ ሀገር ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ናት፡፡ የብሉያት መጻሕፍት ወደ ኢትዮጵያ እንዴት እንደመጡ ቀደም ብለን አይተናል፡፡ ከዚህም አልፎ ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው በራሷ ልጅ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በ34 ዓ.ም ነው፡፡ በዚህም በሐዲስ ኪዳን ከኢየሩሳሌም ውጭ ክርስትናን በመጀመሪያ የተቀበለች ኢትዮጵያ ናት፡፡ ለዚህም ነው ነቢዩ አሞጽ እሥራኤላውያንን ወቅሶ ኢትዮጵያውያንን ያመሰገነው፡፡ • አሞጽ 9:7 የእሥራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?
 • 62. ኢትዮጵያ በሕገ ወንጌል • በክርስቶስ ልደት ወርቅ እጣን ከርቤ ካመጡት ሦስት ነገስታት አንዱ ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ባዜን መሆኑ • መዝ 71:10 የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ። • ማቴ 2:10 ወድቀውም ሰገዱለት …እጅ መንሻ ወርቅ እጣን ከርቤም አቀረቡለት • ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ መጠመቁ ሐዋ 8:26 • የቤተክርስቲያን ጸሐፍትም ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ ወንጌልን ሰበከላቸው ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ • አምስቱ አዕማደ ምሥጢራት(መሠረተ እምነት) ጠብቃ መኖሯ (የዕሥራ ምዕት በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀ ዐውደ ርእይ(VCD)-ማኅበረ ቅዱሳን) • ይሁን እንጂ የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ግን በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አማካኝነት ወደግእዝ ተተርጉመው ነው፡፡ • ሁለተኛም በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአልአ ሜዳ ዘመነ መንግሥት ወደ ሀገራችን በመጡ ተሰዓቱ ቅዱሳን(ዘጠኙ ቅዱሳን) የሐዲስ ኪዳንን መጻሕፍት በሙሉ ወደ ግእዝ ተርጉመዋል፡፡ • በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት መተርጉመ መጻሕፍት አባ ሰላማ ሐዲስ ኪዳንን ከተለዩ ቋንቋዎች ወደ ግእዝ ተርጉመዋል፡፡
 • 63. 3. መጽሐቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ የተተረጎመበት ሁኔታ(በኢትዮጵያ - ተጨማሪ) • አባ አብርሃም(አባ ሮሜ) የተባሉ መነኩሴ ከጎንደር ተነስተው ወደ ግብፅ በመሄድ የተለያዩ ቋንቋዎችን ካጠኑ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ አማርኛ መልሰዋል፡፡ በመሆኑም የእርሳቸው የትርጉም ሥራ በ1816 ዓ.ም ዐርባዕቱ ወንጌላት(አራቱ ወንጌል)፣ በ1821 ዓ.ም ሐዲስ ኪዳን እና በ1832 ዓ.ም ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሟል፡፡ • በ1878 ዓ.ም ደግሞ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ዕብራይስጥንና ግሪክን ከሚያውቁ እንደ ማርቲን ፍላድ ካሉ የውጭሀገር ዜጎች ጋር በመሆን እንደገና እንዲታተም አደረጉ፡፡ • አለቃ ተወልደ መድኅን ወደ ትግረኛ አናሲሞስ ነሲቡ ወደ ኦሮምኛ ተርጉመውታል፡፡ በሌሎች ደግሞ በተለያዩ ቋንቋዎች(ወላይተኛ፣ ሲዳሞኛ፣ ጉራጊኛ፣ አኙዋክኛ ወዘተ) ተተርጉሟል፡፡ • በ1930 ዓ.ም(በ1938 እ:ኤ:አ:) ዩናይትድ ስቴትስ ፊላድልፊያ በአማርኛ ታትሟል፡፡
 • 64. • በ1953 ዓ.ም ከኢጣሊያን ወረራ በኋላ አሁን በአብዛኛው እጅ የሚገኘው ባለ 66ቱ መጽሐፍ ቅዱስ ታተተመ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ በደንብ መታረም እንዳለበት ይታመናል፡፡ ይህ አልበቃ ብሎ ግን በዘመኑ በተነሱ የመናፍቃን ቅሰጣ “ጉድ ኒውስ ባይብል፣ ተሻሽሎ የወጣ፣ በቀላል አማርኛ፣ አዲሲቷ ትርጉም፣ ለሕጻናተ፣ ሕያው ቃል” እያሉ ልዩ ልዩ ስያሜ እየሰጡ ብሉይንና ሐዲስን ሲፈልጉም ሐዲስን ብቻ እያሳተሙ እንካችሁ ካሉ ውለው አድረዋል፡፡ የእነዚህ መጽሐፍት የትርጉም ሁኔታ የፈጠረውን ችግር መጽሐፍ ቅዱስና ትርጉም በሚለው ርዕሳችን አናየዋለን፡፡ • በ1980 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ተክለሃይማት ፈቃድ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ታተመ፤ • በ2000 ዓ.ም ደግሞ በብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ፈቃድ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ተተርጉሟል፡፡ ይሁን እንጅ አሁንም ድረስ እንደገና መታረም እንዳለበት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡
 • 65. • 4. መጽሐፍ ቅዱስ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ የተተረጎመበት ሁኔታ(በውጭው ክፍለ ዓለም- በዚህ ንዑስ ክፍል የተጠቀሱት ዓመቶች ሁሉም እ.ኤ.አ ናቸው) • በ4ኛው መ/ክ/ዘመን(366 እ:ኤ:አ) አባጀሮም ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ዕብራይስጥንና ግሪክን ቋንቋ በሚገባ ካጠና በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ቩልጌት ቋንቋ(በሮም ይኖሩ የነበሩ የቩልገስ ህዝብ ቋንቋ) ተርጉሟል፤ ከዚያም ቩልገስን ወደ ላቲን ሲተረጉም እንዳለ በማረፉ የእርሱን ጅምር ሌሎች እንዳጠናቀቁት ይነገራል፡፡ ከዚያ በመቀጠልም ከላቲን ወደ ጀርመኖች ቋንቋ ጎቲክ ተተረጎመ፡፡ ይሁን እንጂ በ16ኛው መ/ክ/ዘ የተነሳው ማርቲን ሉተር ይህን የአባ ጀሮምን የጎቲክ ትርጓሜ አልቀበልም በማለት ወደ ጀርመን ብሎም ከ50 በላይ ቋንቋዎች እንዲተረጎም አድርጓል፡፡ • ሶርያም በሱርስት ቋንቋ የተተረጎሙ በርካታ ቅዱሳት መጻሕፍት እንደነበሯት ይነገራል፡፡ በ5ኛው መ/ክ/ዘ የሮሐ ኤጲስ ቆጶስ የሆነው ራቡላ እና የመንበግ ኤጲስ ቆጶስ ፊልክስዮስ፤ በ7ኛው መ/ክ/ዘ ቶማስ ዘሄራክሊያ ትርጉሞችን በሱርስት ቋንቋ በማቅናት ይታወቃሉ፡፡ • ከ3-4ኛው መ/ከ/ዘ ቅዱስ ሚስሮችና ቅዱስ ሳሃክ ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን ወደ አርማንያ(የአርመን ቋንቋ) ተርጉመዋል፡፡ • በ1525(26) ቴንዳሌ የተባለ እንግሊዛዊ ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጉም እያላ ካቶሊኮች የማርቲን ሉተርን አተረጓጎም ስልት ተከትሏል በማለት በ1536 አስገደሉት፡፡ ይሁን እንጂ የእርሱ ተከታይ የነበረው ኮቨርዳሌ በ1539 አጠናቆ በቅዱስ ማቴዎስ ስም The Mattew Bible(እንግሊዞች ቅ/ማቴዎስ መጥቶ አስተምሯል ብለው ስለሚያምኑ) በማለት አሳተመው፡፡
 • 66. • በ1553 የእንግሊዝ ፕሮቴስታንቶችመጽሐፍ ቅዱስን ምዕራፍና ቁጥር ሰጥተው The Geneva Bible ብለው አሳተሙት፡፡ (በ1228 ዓ.ም በምዕራፍ በ1551 ዓ.ም በቁጥር እንደተለየ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ያስረዳል፡፡) • በ1568 The Bishops Bible ብለው በንግስት ኤልሳቤጥ ዘመን አሳተሙት፤ • በ1601 The Douay Rheims Bible በካቶሊኮች ታተመ፤ • 1611 The King Jems Version(የንጉሥ ጀምስ ትርጉም ታተመ)፤ • በ18ኛውና 19ኛው መ/ክ/ዘ ግን በየግለሰቦች እየታተሙ በርካታ መጻሕፍት መውጣት ጀመሩ አንዳንዶቹም ወዲያው ጠፍተዋል፡፡ • በ1881 ሐዲስ ኪዳን፣ በ1885 ብሉይ ኪዳን The Revised Version(የተሸሻለው ትርጉም) በሚል ታተመ፤ • በ1901 The American Standard Version(የአሜሪካውያን ስታንዳርድ ትርጉም)፤ • በ1952 The Revised American Standard Version(የተከለሰው የአሜሪካውያን ስታንዳርድ ትርጉም) ታተመ፤ • በ1970 ደግሞ የእንግሊዝ ካቶሊኮችና የአየርላንድ ፕሮቴስታንቶች The New English Bible(አዲሱ የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ) በሚል አሳተሙ፤
 • 67. • በ1970 በዚሁ ዓመት አሜሪካ ደግሞ The New American Bible(አዲሱ የአሜሪካ መጽሐፍ ቅዱስ) በማለት አሳተሙ፤ • በ1971 The New American Standared Bible(አዲሱ የአሜሪካውያን ስታንዳርድ መጽሐፍ ቅዱስ)፤ • በ1976 Todays English Version(የዛሬው የእንግሊዝ ትርጉም)፤ • በ1978 The New International Version(አዲሱ ዓለም አቀፋዊ ትርጉም)፤ • በ1985 የቀድሞውን የፈረንሳይኛ እና የኢየሩሳሌም መጽሐፍ ቅዱስ(Jerusalem Bible) እንዲሁም ከዕብራይስጥና ከግሪክ መጻሕፍት ጋር በማስተያየት ካቶሊኮች አዲሱ የኢየሩሳሌም መጽሐፍ ቅዱስ(The New Jerusalem Bible)፤ • በ1985 በዚሁ ዓመት የአይሁድ ሊቃውንት አዘጋጅተውታል ተብሎ የሚነገረው ታናክህ(Tanakh) መጽሐፍ ቅዱስ በዕብራይስጥ፤ • በ1989 በአሜሪካውያን The New Revised Standards Version(አዲሱ የተከለሰው ስታንዳርድ ትርጉም) • በ989 በእንግሊዝ The New Revised English Bible(አዲሱ የተከለሰው የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ) በማለት አሳትመውታል፡፡
 • 68. የመጻሕፍተ አምላካውያት ቁጥር ቀኖና [የ'1ዱ ቅዱሳት መጻሕፍት የት መጣ]
 • 69. • ቀኖና የሚለው ቃል የተገኘው ካኖን ከሚለው የጽርዕ [የግሪክ ቋንቋ] ሲሆን ትርጉሙም ሕግ ወይም የመሥፈሪያ[የመለኪያ] ደረጃ ማለት ነው:: • ስለዚህ ቀኖና ስንል ስለ አንድ መንፈሳዊ ጉዳይ በቤተክርስቲያን አባቶች[በተለይም በሲኖዶስ] የተመሠረተ ድንጋጌ ወይም ሥርዓት ማለታችን ነው:: ከእነዚህም የቤተክርስቲያን ቀኖናት መካከል ስለቅዱሳት መጻሕፍት የተደነገገው ቀኖና ይጠቀሳል:: መጽሐፍ ቅዱስ የብዙ ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል ዉጤት መሆኑ ይታወቃል:: በዉስጡ የተካተቱት እነዚህ መጻሕፍተ ቅዱሳት [ቅዱሳት መጻሕፍት] በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ መጠሪያዎች አሏቸው:: እነዚህም ፦ ፠ ቅዱሳት መጻሕፍት ወይም መጻሕፍተ ቅዱሳት፣ ፠ አሥራው መጻሕፍት፣ ፠ መጻሕፍተ አምላካውያት የሚሉት ናቸው::
 • 70. • ቅዱሳት መጻሕፍት ወይም መጻሕፍተ ቅዱሳት የሚለው አጠራር የሚያመለክተው መጻሕፍቱ የተለዩ የከበሩ የተቀደሱ መሆናቸውን፤ እንዲሁም ለልዕልናቸው አምሳያ፣ ወደረተኛ፣ አቻ ፣ምትክ የማይገኝላቸው እጅግ በጣም ከፍ ያሉ መሆናቸውን ነው:: • አሥራው መጻሕፍት ማለትም በቀጥታ የመጻሕፍት ሥሮች ማለት ሲሆን የቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ መገኛቸው ምንጮቻቸው ሥረ መሠረታት መሆናቸውን የሚያጠይቅ ነው:: ከእነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት ያልተቀዳ ወይም እነርሱን ሥርና መሠረት አድርጎ ያልበቀለ ከመጀመሪያው እስከ ፍጻሜው ተሠፍረው [ተለክተው] ተቆጥረው ተለይተው ታውቀው በቀኖና ተደንግገው ተወሥነው የተቀበልናቸው መጻሕፍተ ቅዱሳት ተባብረውና ተስማምተው ከሚያስተላልፉት ውጪ አዲስ መልእክት የሚያመጣ ሌላ መጽሐፍ እንዳይኖር ድንበር አበጅተው ፍኖት ቀይሰው አቅጣጫ መሪ ወሰን አስከባሪ በመሆናቸው የተሰጣቸው መጠሪያ ነው:: ከአሥራው መጻሕፍት ምንጭነት የሚቀዱት የሚፈልቁት ደግሞ አዋልድ ይባላሉ::
 • 71. • መጻሕፍተ አምላካውያት የተባሉበትም ምክንያት እነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት የተገኙት በፈቃደ አምላክ እንጂ በሌላ በማንም አይደለምና ነው:: የመጻሕፍቱ ባለቤት ራሱ እግዚአበሔር መሆኑን ለማጠየቅ ሲባል ቅድስት ቤተክርስቲያን በዚህ መጠሪያ ሰይማቸዋለች:: ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ "በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም" ብሎ እንደተናገረ:: ኢሳ ፴፬፥፲፮። በእግዚአብሔር መጽሐፍ ሲል በአምላክ መጽሐፍ ማለቱ ነውና:: የአምላክ መጽሐፍ ወይም መጽሐፈ አምላክ የሚለው ነጠላ ሲሆን ሲበዛ መጻሕፍተ አምላካውያት ይሆናል:: • በተለምዶ መጽሐፍ ቅዱስ እያልን በነጠላ ቁጥር እንደ አንድ መጽሐፍ የምንጠራው የእነዚህን ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል ወይም ጥራዝ ሲሆን በኅፅኑ [በማኅፀኑ ወይም በዉስጡ] ክትት አድርጎ የሰበሰባቸው ፹፩ መጻሕፍት ደግሞ በእነዚህ ሦስት እርስ በእርሳቸው ተተካኪ በሆኑ አቻ ስሞች ይጠራሉ:: በመሆኑም በዚህ ጽሑፍ በተቀያያሪነት እንጠቀምባቸዋለን::
 • 72. • የአሥራው መጻሕፍት አልፋ እና ዖሜጋ • የአሥራው መጻሕፍት ሁሉ በኵር የሆነው መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን እርሱም የተጻፈው በ፩ሺ፬፻፹፮ ዓዓ ነው:: [መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ ትርጓሜ መቅድም እንዲሁም መጽሔተ አሚንን ተመልከት] ይኽም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ፬ሺ፲፬ [አራት ሺህ አሥራ አራት]ዓመታትን ያስቆጥራል:: የእነዚህ መጻሕፍተ አምላካውያት መደምደሚያ የሆነው የሀዲስ ኪዳን መጽሐፍ ደግሞ የዮሐንስ ራእይ ሲሆን እርሱም ከ፺፰ እሰከ ፻ ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደተጻፈ ይታመናል:: ስለዚህ የመጻሕፍተ ቅዱሳት አልፋቸው ማለትም መጀመሪያቸው መጽሐፈ ሄኖክ ሲሆን ዖሜጋቸው ማለትም መጨረሻቸው ደግሞ የዮሐንስ ራእይ ነው:: ከዚህ በመነሣትም መጻሕፍተ አምላካውያት ተወጥነው እስኪጠናቀቁ ፬ሺ፻፲፬ [አራት ሺህ አንድ መቶ አሥራ አራት] ዓመታት ተቆጥረዋል ማለት ነው::
 • 73. • መጽሐፍ ቅዱስ የአንድ ድንገታዊ ጊዜ ስጦታ ሳይሆን የእነዚህ በርካታ ዘመናት ድምር ዉጤት መሆኑ እጅግ በጣም የሚያስደንቀው አንደኛው ገጽታው መሆኑን መካድ አይቻልም:: በዘመናት ዑደት ተጀምሮ እስኪያበቃ ይህን ያህል ዘመን የጠየቀ መጽሐፍ አለ ከተባለ ብቸኛው መጽሐፍ ራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው:: ምናልባት በሆነ ወቅት ተጀምረው ሳይጠናቀቁ የቀሩ ሌሎች መጻሕፍት ሊኖሩ ይችላሉ:: [ለአብነትም እንደ ኢንሳይክሎፒድያ ያሉትን በብዙ ጸሐፊዎች የሚቀናበሩትን መጻሕፍት መጥቀስ ይቻላል] መጽሐፍ ቅዱስ ከእነዚህ መጻሕፍት ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች ይለያል፦
 • 74. • ፩ መጽሐፍ ቅዱስ በውጥን የቀረ ሳይሆን ተጀምሮ በአግባቡ የተጠናቀቀ በመሆኑ አልፋ እና ዖሜጋው ይታወቃል:: ከሌሎች መጻሕፍት ምናልባትም አንዳንዶቹ ፍጻሜያቸው የማይታወቅ ሲኖሩ፣ ምንጊዜም ለእርማት እና ለመሻሻል ክፍት ከመሆናቸውም ባሻገር ገና አዳዲስ ሀሳቦችንም [ከበፊቱ የሚጋጩ ቢሆኑ እንኳ] ለማስተናገድ ያልተዘጉ ናቸው:: መጽሐፍ ቅዱስ የበርካታ ዘመናት እና የተለያዩ ቅዱሳን ውጤት ይሁን እንጂ የዘመናት መፈራረቅ አሉታዊ ተጽዕኖ ያላሳደሩበት በውስጡ ያሉት መጻሕፍትም ከዚህ የተነሳ ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚገመተው የሀሳብ ተቃርኖ ወይም ግጭት ያልደረሰበት ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው:: • ፪ የእነዚያ መጻሕፍት ጸሐፊዎች ሰዎች በመሆናቸው ዐረፍተ ዘመን እየገደባቸው መጻሕፍቱ በሂደት ላይ ወይም በጅምር ላይ መሆናቸውን እንጂ መጠናቀቃቸውን ሳያውቁ የሚቀሩበት ሁኔታ ሲኖር፤ የቅዱሳት መጻሕፍት ባለቤት ግን በባሕርዪው ኅልፈት በመንግሥቱ ሽረት የሌለበት ልዑል እግዚአብሔር ነውና የጀመረውን ፈጽሞታል:: እግዚአብሔር በባሕርዪው ሁሉን ቻይ ሁሉን ዐዋቂ እንደመሆኑ ይህ ቀረብኝ ያ ጎደለብኝ ብሎ የሚጸጸት አይደለምና:: ሊያስተላልፍ የፈለገውን ሁሉ በወሰነው ጊዜ ያለማስተሀቀር አስተላልፏል::
 • 75. • ቅዱሳት መጻሕፍቱ ሁሉ የተቀዱት ከአንድ ባሕር ነውና ምንም እንኳ ፬ሺ፻፲፬ ዓመታትን ያኽል ረጅም ዘመን የፈጀ ጊዜ ከባለቤታቸው ከእግዚአብሔር ቢመደብላቸውም ያለመዘበራረቅ እና ያለ ቅራኔ በልዩ እና ፍጹም ስምምነት የተከናወኑ ናቸው:: እየታዘዙ የጻፏቸው ሰዎች ብዙ አና በተለያየ ዘመን የኖሩ ቢሆኑም ቅሉ ምንጩ አንዱ እግዚአብሔር የማይለወጥ ፤ ዘመናት ሲሻሻሉ መሻሻል፥ ሁኔታዎች ሲጎሳቆሉ መጎሳቆል የሌለበት ጽኑዐ ባሕርዪ ስለሆነ የጊዜው መርዘም በእርሱ ዘንድ አሉታዊ ውጤት አያመጣም:: ሰው ግን ዛሬ ያሰበውን ነገ የሚለውጥ፥ አሁን የጻፈውን መልሶ የማይደግም ስለሆነ የዘመናት መፈራረቅ መሠረታዊ ለውጥ ያሳድሩበታል:: ከልምዱ [ከሚያየው ከሚሰማው ከኖረው ከተማረው] በመነሳት በብዙ የሀሳብ ውጣ ውረድ ውስጥ ይጓዛል:: ስለሆነም የአስተሳሰብ ተለዋዋጭነት ይከሰትበታል:: በአንድ ወቅት የሠራውን ወይም የጻፈውን በሌላ ጊዜ ሊለውጠው ከዚህም በላይ በተቃራኒው ሊጓዝ ይችላል:: የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር ግን ዘመናትን ይሠለጥንባቸዋል የወደደውንም ይሠራባቸዋል እንጂ አይሠለጥኑበትም:: • ጥንት መጽሐፈ ሄኖክን ሲያጽፍ የነበረው እግዚአብሔር ኋላም አቡቀለምሲስን ያጻፈው መለወጥ ሳይኖርበት ነው:: ዘመናትን አስረጃቸው እንጂ እርሱ ያው ነው:: በዘመናት በለጸገ እንጂ ለውጥ የለበትም:: ቅዱስ ዳዊት ̋አንተ ግን ያው አንተ ነህ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ̋ ሲል እንደተናገረ:: መዝ ፻፩፥፳፯:: ደግሞም በነቢዩ ላይ አድሮ «እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም» ብሎ እንዳናገረ:: ሚል ፫፥፮። ቅዱስ ጳውሎስም ̋ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬም እስከ ለዘላለምም ያው ነው ̋ እንዳለ።ዕብ፲፫፥፰።
 • 76. አሥራው መጻሕፍትን በሚመለከት የተደረጉ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤያት • አሥራው መጻሕፍትን በሚመለከት የተደረጉ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤያት • ቅዱሳት መጻሕፍት ወደ አንድ ሙሉ ጥራዝ ከመጠቃለላቸው በፊት በርካታ ጉባኤያት ተካሂደዋል:: ከቤተክርስቲያን ታሪክ እንደምንገነዘበው በታላላቆች ቅዱሳን አበው አማካይነት ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሌሎች ሰርጎ ገብ ድርሳናት ለመጠበቅ ሲባል ተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ጉባኤያት ተደርገዋል:: • የቅዱሳት መጻሕፍትን ቀኖና ለመወሰን በርካታ ጉባኤያት እንደተካሄዱ መረጃዎች ያመለክታሉ:: ይሁን እንጂ ተቀባይነት ያላቸው ጉባኤያት ቤተ ክርስቲያን ሳትከፋፈል ማለትም ከጉባኤ ኬልቄዶን በፊት የተካሄዱት ብቻ በመሆናቸው እኛም ትኩረታችን በዚሁ መሠረት ይሆናል:: ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚመለከት ፮ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና ያላቸው ጉባኤያት ተካሂደዋል:: • እንደ ሰባተኛ ሊቆጠር ይገባዋል ተብሎ በብዙ ጥንታዊ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የሚታመንበት ደግሞ ጉባኤ ኒቅያ ነው:: በዚህ ጉባኤ ላይ በሰፊው ወይይት ባይደረግበትም አጀንዳው ተነሥቶ ፹፭ኛውን የሐዋርያት ቀኖና[ከዘህ በታች በዝርዝር የምንመለከተውን] አጽንቶ እንደተጠናቀቀ ይታመናል:: ይህም የሆነው የጉባኤው ተቀዳሚ እና ዐቢይ አጀንዳ የርእሰ መናፍቃን የአርዮስን ትምህርት ማውገዝ በመሆኑ እና ረዥም ጊዜ በመፍጀቱ እንደሆነ ታውቋል::
 • 77. • ከዚህ በታች የቀሩትን ፮ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና ያላቸው ጉባኤያት እንመለከታለን:: ፩᎐ ጉባኤ ሐዋርያት • ጉባኤ የተካሄደበትን በ$ ዓ.ም ነው፤ የመጀመሪያው ሲኖዶስ በመባል ይታወቃል፤ የተካሔደው በኢየሩሳሌም ሲሆን የጉባኤው መሪም ሐዋርያው ያዕቆብ ነው፡፡(የጌታ ወንድም፣ የወንጌላዊው ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ ወንድም፣ መልእክቱን የጻፈው) • ጉባኤ ሐዋርያት የዓለም አቀፍ ጉባኤያት መሠረት በመሆኑ ለተከታዮቹ የኋለኞች ጉባኤያት አረአያነቱ የሚጠቀስ ነው:: • ይህ ጉባኤ '5 አንቀጾች ሲኖሩት '5ኛው አንቀጽም ስለ መጻሕፍተ አምላካውያት የተደነገገ ነው:: • እነዚህ ቀኖናት በቅዱስ ቀሌምንጦስ ዘሮም አማከይነት ተዘጋጅተው ወደ ተለያዩ አብያተክርስቲያናት እንደተላኩ በ'5ኛው ቀኖና ላይ ተዘግቧል::
 • 78. • Canon 85, Let the following books be esteemed venerable and holy by you, both of the clergy and laity. Of the Old Covenant: the five books of Moses—Genesis, Exodus, Leviticus, Numbers, and Deuteronomy; one of Joshua(ኢያ) the son of Nun(ወልደ ነዌ), one of the Judges(መሳ), one of Ruth, four of the Kings(ሳሙና ነገሥት), two of the Chronicles, two of Ezra, one of Esther, one of Judith(ዮዲት), three of the Maccabees, one of Job, one hundred and fifty psalms; three books of Solomon—Proverbs, Ecclesiastes, and the Song of Songs; sixteen prophets. And besides these, take care that your young persons learn the Wisdom of the very learned Sirach. (43 Books) • But our sacred books, that is, those of the New Covenant, are these: the four Gospels of Matthew, Mark, Luke, and John; the fourteen Epistles of Paul; two Epistles of Peter, three of John, one of James, one of Jude; two Epistles of Clement; and the Constitutions dedicated to you the bishops by me Clement, in eight books; which it is not fit to publish before all, because of the mysteries contained in them; and the Acts of us the Apostles. Philip Schaff, Ante-Nicene Fathers (ANF) Vol. 07, Constitutions of the Holy Apostles. Christian Classics Ethereal Library, Grand Rapids, MI, 2004. p. 759, ANKE WANGER: The Biblical Canon of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church: p13-14 Not listed Prayer of Mianasseh, Jubilees, Enoch, Tobit, Wisdom,
 • 79. • ይኽም ውሣኔ ከስምንቱ የሐዲስ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍት በግጽው ሲኖዶስ [ረስጠጅ] 56ኛው ቀኖና 81 • እንዲሁም አብጥሊስ ሲኖዶስ [ረስጠአ ወይም ረስጣ] 80ኛው ቀኖና 81 • ትእዛዝ ሲኖዶስ [ረስጠብ] 55 የመጻሕፍት ቁጥራቸው ከ'1ዱ ቅዱሳትእንደሆኑ አስረግጠው ነግረውናል • እነዚህ ውሣኔዎች ቅድስት ቤተክርስቲያን በኋላ ለምትወሥናቸው መጻሕፍትን የሚመለከቱ ማናቸውም ድንጋጌዎች አብነቶች ናቸው:: ምክንያቱም • በቀኖና ቤተክርስቲያን የመደንገግ ሥልጣን ከጉባኤ ሐዋርያት የሚልቅ የለም:: አነርሱ የወሠኑት ሁሉ የድንጋጌዎች ወይም የቀኖናዎች ሁሉ ላዕለይ ለመሆኑ ተከራካሪ አይገኝም:: ስለሆነም ከእነርሱ በኋላ አነርሱን ተከትለው የሚከናወኑ ጉባኤያት በሙሉ የቅዱሳን ሐዋርያትን አሠረ ፍኖት የተከተሉ እንዲሆኑ ይጠበቃል:: ውሣኔዎች ሁሉ በእነርሱ መስፈርት የሚለኩ በመሆናቸው የሐዋርያት ተከታዮች የሆኑት ሐዋርያነ አበው የተቀበሉትን ባለማዛነፍ ሲከተሏቸው ታይተዋል::
 • 80. • ስምንቱን የሐዲሰ ኪዳን የሥርዓት መጻሕፍት ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከሐዋርያት ተቀብሎ ያሠራጨው የቅ/ጴጥሮስ ደቀመዝሙር የሆነው ቅዱስ ቀሌምንጦስ እጅ መላኩ የመልዕክቱን ተቀባይነት አያጠራጥርም:: • በሐዋርያት ቀኖና የአሥራው መጻሕፍት ቁጥር '1 መሆኑ ከመገለጹም በላይ በአነዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት መካከል ምንም ዓይነት የደረጃ ልዩነት የሌለ መሆኑን ያረጋግጣል:: • በኋላ ዘመን አይሁድ በ፺ ዓም ባደረጉት የጃሚና ጉባኤ ፕሮቶካኖኒካል(የመጀመሪያ የቀኖና) እና ዲዮትሮካኖኒካል(ሁለተኛ የቀኖና) መጻሕፍት በማለት ከፈለዋቸዋል:: የዚህ ጉባኤ ዋና ዓላማውም ክርስትናን ለመቃወም እንዲመቻቸው የራሳቸውን የመጻሕፍት ቀኖና መደንገግ ነው:: • የአነርሱን ድርጊት በውል ከተመለከትነው ዘመነ ክርስትና ከታወጀ በኋላ ምንም ዓይነት ውሣኔ ቢወሥኑ ምንም ዓይነት ተቀባይነት እንደሌለው ያለማመንታት እንረዳበታለን:: አይሁድ ያገለሏቸውን በእግራቸው ገብቶ እነርሱን ተከትሎ ማግለል በምንም ዓይነት መለኪያ አሳማኝ ሊሆን አይችልም:: እንኳን መጻሕፍቱን ፈጣሪያቸውን የሰቀሉ ናቸውና:: • “There is currently no distinction at all between the book that are referred to as protocanoncial and deuterocanonical. Whereas the Ethiopian Orthodox Church understand and uses these terms when referring to the respective books, it does not differentiate in its own Bible between proto and deutero canon. All books accepted into the Bible are considered equally inspired, equally the Word of God, and equally instructive (albeit for different situations and circumstances.” ANKE WANGER: The Biblical Canon of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church: p .4
 • 81. • ይህ የአይሁድ ድርጊት ለጊዜውም ቢሆን እንደ እነ አባ ጀሮም(አውሳብዮስ ሄሮኒመስ፣ አባ ሄሮኒመስ) በመሰሉ አባቶች ላይ ተጽእኖ አሳድሮ ነበረ ለማለት ይቻላል:: ምክንያቱም አባ ጀሮም ቅዱሳት መጻሕፍትን ወደ ቩልገስ ቋንቋ ሲተረጉም የሥራው መጀመሪያ ያደረገው የዕብራይስጥን ቋንቋ መማር ነበር:: ይህንንም ለማሳካት ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዟል:: በዚያም ከአይሁድ ሊቃውንት ባገኘው መረጃ ምክንያት የጃሚናውን ውሣኔ ተከትሎ እነርሱ ያገለሏቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ላለመተው ሲል ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት የሚል መጠሪያ በመስጠት ተርጉሟቸዋል:: • ይህንን የተረዱት ቅዱስ አውግስጢኖስና ታዋቂው ጸሐፊ ሩፊኖስ በጉዳዩ ላይ ከአባ ጀሮም ጋር በጥልቀት ከመከሩ በኋላ አባ ጀሮምን አሳምነው ሁሉም የቀኖና መጻሕፍት ማዕርግ አግኝተው እንዲሰየሙ አድርገዋል:: • ይሁን እንጂ ይህ ጉዳይ መፍትሔ ከተሰጠው ከ፲፩፻ [ከአንድ ሺህ አንድ መቶ] ዓመታት በኋላ የተነሳው ማርቲን ሉተር የተባለ የፕሮቴስታንት እምነት መሥራች ወደኋላ ተመልሶ የአይሁድን ውሣኔ በማጽደቅ ይከተላት የነበረችውን የሮም ካቶሊክን ቀኖና በማፍረስ ዲዮትሮካኖኒካል ወይም ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት (አፖክሪፋ) ይዞ አዲስ የክህደት በር ከፈተ::