SlideShare ist ein Scribd-Unternehmen logo
1 von 88
Downloaden Sie, um offline zu lesen
i
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አዘገጃጀት
(ለማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎች የማሰልጠኛ ማንዋል)
አዘጋጆች፡- ደሳለው ጌትነት
ሐይማኖት ጌታቸው
አርታዒ፡- ኤርሚያስ ፀጋዬ
ጥር 2009 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
i
ማውጫ
አርዕስት ገፅ
መግቢያ............................................................................................................................ 1
የስልጠናው ዓላማ ............................................................................................................. 4
ክፍል አንድ...................................................................................................................... 5
1.የልማታዊ ጋዜጠኝነት ንድፈ ሃሳብና የማህበረሰብ ሚዲያ ................................................... 5
1.1 የማህበረሰብ ሚዲያ ምንድን ነው?......................................................................................6
1.2 ልማታዊ ጋዜጠኝነት ማለት ምን ማለት ነው? ..................................................................7
ክፍል ሁለት..................................................................................................................... 9
2.የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አዘገጃጀት .................................................................................. 9
2.1 ዜና ........................................................................................................................... 9
2.1.1 ዜና ምንድን ነው?.............................................................................................................9
2.1.2 የዜና ዓይነቶች.................................................................................................................11
2.1.3 የዜና ጠቀሜታዎች .........................................................................................................13
2.1.4 የዜና ጥንካሬዎችና ድክመቶች........................................................................................14
2.1.5 የዜና መመዘኛ እሴቶች ..............................................................................................15
2.1.6 የዜና አላባውያን ..............................................................................................................22
2.2 የዜና ምንጮች....................................................................................................................27
2.2.1 ዜና ከየት ይገኛል?......................................................................................................27
2.2.2 የዜና ምንጮች.............................................................................................................28
2.2.3 የዜና ምንጮች አያያዝ................................................................................................30
2.2.4 መረጃ እንዴት ይገኛል?..............................................................................................32
ሀ. ምልከታ ............................................................................................................................32
ለ. ቃለ መጠይቅ ....................................................................................................................39
ሐ. ምርምርና ጥናት..............................................................................................................48
2.3 የዜና አፃፃፍ ስልት..............................................................................................................48
2.3.1 የዜና ቋንቋ...................................................................................................................49
2.3.2 መሪ አንቀፅ (Lead)....................................................................................................52
2.3.3 የአርስተ ዜና አፃፃፍ....................................................................................................53
2.3.4 የዜና መዋቅር..............................................................................................................54
ii
2.3.5 የሬዲዮ የዜና አፃጻፍ ፎርማቶች.................................................................................57
2.3.5 የሬዲዮ ዜና አፃጻፍ ደንቦች.........................................................................................63
3. የሬዲዮ ፕሮግራም...................................................................................................... 65
3.1 የሬዲዮ ፕሮግራም ማለት ምን ማለት ነው?....................................................................65
3.2 የሬዲዮ ፕሮግራም ዓይነቶች..............................................................................................65
3.2.1 የማስተማርያ ፕሮግራም.............................................................................................65
3.2.2 የማሳወቂያ ፕሮግራም.................................................................................................66
3.2.3 የመዝናኛ ፕሮግራም...................................................................................................66
3.3 የሬዲዮ ፕሮግራም ባህርያት ..............................................................................................67
3.4 የሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት................................................................................................68
3.4.1 የቅድመ-ዝግጅት ምዕራፍ............................................................................................69
3.4.2 የዝግጅት ምዕራፍ .......................................................................................................73
3.4.1 የድህረ ዝግጅት ምዕራፍ.............................................................................................74
ዋቢ መፅሐፍት............................................................................................................... 75
አባሪ፡- የሬዲዮ ፕሮግራም ፕሮፖዛል አዘገጃጀት................................................................. 76
1
መግቢያ
የጋዜጠኝነትን ፅንሰ-ሃሳብ በተለያየ መልኩ የሚተረጉሙ ብዙ አካላት አሉ፡፡ ይኸውም
ከጋዜጠኝነት ጋር ባላቸው ቅርበትና ለጋዜጠኝነት ካላቸው አመላካከት የመነጨ ነው፡፡
ለጋዜጠኝነት የተለያየ ትርጓሜ ቢኖረውም ትርጉሞቹ የተወራረሰ ባህሪ አላቸው፡፡
ከነዚህም ትርጉሞች ውስጥ አንዳንዶቹን ለመጠቃቀስ የሚከተለው ትርጓሜ አንዱ ነው፡፡
ጋዜጠኝነት ማለት መረጃዎችን ከምንጮቻቸው የመሰብሰብ፣ በዜና፣ መጣጥፍና ሃተታ
መልክ በማዘጋጀት በብዙሃን መገናኛ የማሰራጨት ሙያዊ ጥበብ ነው፡፡ ብዙሃን መገናኛ
ስንል ሰሌዳ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችን፣ በራሪ ወረቀቶችን፣ የቢሮ ውስጥ
ህትመቶችን፣ ጋዜጣ፣ መፅሔት፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣መፅሐፍ፣ ፊልምና የመሳሰሉትን
ያጠቃልላል፡፡ ይህም ማለት ጋዜጠኝነት በነዚህ ብዙሃን መገናኛ አማካኝነት መረጃን
ከመረጃው ባለቤት ወደ አንባቢው፣ አድማጩ ወይም ተመልካቹ በተለየ አዘገጃጀት
የማቅረብ ጥበብ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት የሚለውን ቃል መጀመሪያ አካባቢ የሚያገለግለው
ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን በጋዜጣ አትሞ ማውጣት ነበር፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት
ጋዜጠኝነት በጣም ሰፊ የሆነ አውድ አለው፡፡ ይኸውም ከብሮድካስትና ዌብሳይት ሚዲያ
መጀመር ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡
በሌላ መልኩ ጋዜጠኝነት መረጃን ቆፍሮና እውነታውን አጣርቶ ሁነቶችን፣ ጉዳዮችንና
ሂደቶችና ከብዙሃኑ ህዝብ በጋዜጣ፣ በመፅሔት፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣በኢንተርኔት
እና በመሳሰሉት ማዳረስ የሚቻልበት የሙያ ዘርፍ ሲሆን በዋናነት መረጃን የመሰብሰብ፣
የማጠናከር፣ የመፃፍ፣ አርትዖት ሥራ የመስራት፣ ፎቶግራፍ የማንሳት፣ የህትመት
የዲዛይን ሥራን እና የማሰራጨት ሥራዎችን አካቶ የያዘ ሙያ ነው፡፡
ህብረተሰቡ መረጃ የማድረስ ዓላማ በመያዝ ጋዜጠኝነት ግለሰቦችን፣ ድርጅቶችን፣
ተቋማትን፣ መንግስትንና የንግድ ተቋማትን እንዲሁም ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች ላይ
ትኩረት አድርጎ ሽፋን የሚሰጥ ሙያ ነው፡፡
በህንድ አገር የጋዜጠኝነት አባት በመባል የሚታወቁት ፕሮፌሰር ፓታን ዳሊ ሰፒ
ስለጋዜጠኝነት ሲናገሩ፡-
2
ጋዜጠኝነት ሰውን ልጅ ሰብዓዊ መብት የሚያስከብር፣ የታመነ
የዲሞክራሲ ስርዓት አራማጅ እንዲሁም የፍትህ ርትዕ ጠበቃና የህዝብ
ድምፅ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት በነፃ ሃሳብን የመግለጫ መሳሪያ፣ እንዲሁም
የህሊናን ነፃነት ማዳበሪያ ፍቱን ማስተላለፊያ መሳሪያ በመሆኑ
በህብረተሰብ የሙያ ዝርዝሮች ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ መያዝ የሚገባው
ተግባር ነው፡፡
እንደህንዳዊው ፕሮፌሰር ጋዜጠኝነት ከምንም በላይ ከራስ ጥቅም በፊት የማህበረሰባዊ
ጥቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት ድምፅ አልባ ለሆኑ
የማህበረሰብ አካላት ድምፅ መሆን መቻል ነው፡፡ ጋዜጠኝነት ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና
ለህግ መከበር ከፍተኛ የሆነ ሥራ የሚሰራ የሥራ መስክ ነው፡፡
የጋዜጠኝነት ዋነኛ የስራ ማሳያ የሆኑት የብዙሃን መገናኛዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ብዙሃን
መገናኛዎች ህዝባዊ የሆኑ ጉዳዮችን በመረጃና በአስተያየት ተቀሽረው የሚቀርቡበት
ነው፡፡ ጋዜጠኝነት መረጃን ጥሩውን ከድፍርሱ፣ ምርቱን ከእንክርዳዱ በመለየት
መረጃዎችን፣ አስተያየቶችን እና ሁነቶችን ከህብረተሰቡ ለህብረተሰቡ የማሰራጨት ስራ
ነው፡፡
ጋዜጠኝነት ሁነቶችን፣ ሃሳቦችን፣ መረጃዎችን እና ተቃርኖዎችን በየአውዳቸው
እየመረጠ የማስቀመጥና የማቅረብ ተግባርን የያዘ ሙያ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት
የድርጊቶችንና አስተያየቶችን እውነትን፣ ውክልናቸውንና ጠቀሜታቸውን በመገምገም
የሚቀርብበት የሙያ ዘርፍ ሲሆን የማያቋርጥ ሂደትም ጭምር ነው፡፡ የማያቋርጥ
ሂደት ሲባል ደግሞ ዓለም እስካለች ድረስ የመረጃ ፍሰት ከአንዱ የዓለማችን ክፍል ወደ
ሌላው የሚያደርገው ጉዞ ስለማይነጥፍ በመሆኑ ነው፡፡
በአጠቃላይ ጋዜጠኝነት ለዜና፣ ለመጣጥፍና ለሃተታ የሚሆኑ ጉዳዮችን ከምንጫቸው
የማሰባሰብ፣ የማዘጋጀትና በበራሪ ፅሁፎች፣ በሚበተኑ ወረቀቶች፣በጋዜጦች፣
በመፅሔቶች፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን እና በማህበራዊ ድረ ገፅ የብዙሃን መገናኛዎች
የማሰራጨት ሙያዊ ሂደት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የጋዜጠኝነትን ትርጉም ከብዙሃን
መገናኛ ጋር በተለይም ከብሮድካስት የሚዲያ ዘርፍ ጋር አያይዘው ያዩታል፡፡ ለዛም ነው
አንድ ግለሰብ ጋዜጠኛ ነኝ ሲል በቀጥታ ከቴሌቪዥን ወይም ከሬዲዮ ተቋም እንደመጣ
3
አድርገን የምንወስደው፡፡ ነገር ግን ጋዜጠኝነት ሁልጊዜም ከብዙሃን መገናኛ ጋር ብቻ
ማሰብ የተሳሳተ ግንዛቤ ነው፡፡ ምክንያቱም ብዙሃን መገናኛ የመረጃ ማስተላለፊ መንገድ
እንጂ በራሱ የጋዜጠኝነት ሙያ አይደለም፡፡ ስለዚህ በበራሪ ወረቀቶች፣ በማስታወቂያ
ሰሌዳዎች፣ በመስሪያ ቤት ህትመቶች ወዘተ የሚሰራጩ መረጃዎች በጋዜጠኝነት ዘውግ
ውስጥ ይከናወናሉ፡፡
በሬድዮ የሚደረግ የጋዜጠኝነት /የሚዲያ / አተገባበር በድምፅ የሚደረግ የቃላት ጨዋታ
ነው፡፡ በታሪካዊ አመጣጣቸው ሲታዩ ቴሌቭዥን ሬድዮን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ እንዲህ
በመሆኑም ብዙ የብዙኅን መገናኛ ጠቢባን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቴሌቭዥን እየተወደደ
በመሄዱ ሬድዮ የመሞት እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው ይላሉ፡፡ በዚህ ምክንያትም ብዙ
የጋዜጠኝነት አጥኝዎች ፍላጎታቸው ወደ ቴሌቭዥን እያጋደለ የመሄድ አዝማምያ
አሳይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የጠቢባኑ መላምት ሳይሆን ቀርቶ ሬድዮ እስከ አሁን በጣም
ተወዳጅና ተደማጭ የብዙኅን መገናኛ ዓይነት ነው፡፡ በተለይ ሬድዮ የኤሌክትሪክ
መብራት ሀይል ባላገኙ የገጠር አከባቢዎች በጣም ተፈላጊና ተመራጥ ነው፡፡
ብዙ ሰዎች ሬድዮ የሚያዳምጡበት ምክንያት ምን እየተደረገ ምን እየሆነ እና ነገሮች
ምን እንደሚመስሉ በአፋጣኝ ለማወቅ ሲፈልጉ ነው፡፡ ሬድዮ አንድ ድርጊት ሲፈፀም
ወይ ሲከወን ወድያው በፍጥነት /in speed/ ለአድማጮች ያደርሳል፡፡ ይህ አንዱ
የሬድዮ ባህርይ ነው፡፡ ሬድዮ እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ተመራጭ ከሚያደርጉት
ነገሮች አንደኛ ከቦታ ወደ ቦታ ይዞ ለመንቀሳቀስ /being portable) ሁለተኛ ሬድዮን
እያዳመጥክ ሌላ ተጓዳኝ ስራ መስራት ይቻላል፡፡ ሌላው የሬድዮ እንደ ብዙኅን መገናኛ
ተመራጭ የሚዲያደርገው የሰው ሃይል ብዛት ቆጣቢነቱ ነው፡፡ ይህ ሲባል በሬድዮ
ለሚደረግ የመረጃ ስርጭት አንድ ሰው ከስልክ በሚመጡ ብዙ ሃሳቦች ሊያስተናግድ
ይችላል፡፡ የካሜራ የመብራት ባለሞያዎች ላያስፈልጉ ይችላሉ፡፡
ይህ የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ማንዋል ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች
አሉት፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ስለማህበረሰብ ሬዲዮ ጠቅላላ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ
ሲሆን ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ለማህበረሰብ ሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አሰራር ላይ
ዝርዝር ገለፃ ይሰጣል፡፡
4
የስልጠናው ዓላማ
የዚህ ሥልጠና ዓበይት ግቡ የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎችን የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራሞችን
ሙያዊና ስኬታማ በሆነ መንገድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ማስቻል ሲሆን ሰልጣኞች ይህንን
ስልጠና ሲያጠናቅቁ የሚከተሉት ክህሎቶች ይኖሯቸዋል፡፡
 የማህበረሰብ ሬዲዮ ምንነትን ያውቃሉ፤
 ለማህበረሰብ ሬዲዮ የሚሆን ዜናን ያዘጋጃሉ፤
 የመረጃ ምንጮችን አያያዝ ያውቃሉ፤
 የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን ይለያሉ፤
 የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን ተጠቅመው መረጃን ይሰበስባሉ፤
 የሬዲዮ ፕሮግራም ፕሮፖዛሎችን ማዘጋጀት ይችላሉ፤
 ሬዲዮ ፕሮግራሞችን ያቀርባሉ፤
 ዜናና ፕሮግራሞችን በስቱዲዮ ውስጥ ማንበብ ይችላሉ፤
5
ክፍል አንድ
1. የልማታዊ ጋዜጠኝነት ንድፈ ሃሳብና የማህበረሰብ ሚዲያ
በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን የብዙሃን መገናኛ ተቋማት ዋነኛ የልማት ደጋፊ እንደሆነ
ይታመናል፡፡ ልማት ማለት ምን ማለት ነው የሚለው ጉዳይ የተለያዩ ዓይነት
ትርጓሜዎች ቢሰጠውም አሜሪካዊ ምሁር ሮጀርስ (1976) ልማት ምን እንደሆነ
የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቷል፡፡
ልማት ማለት በማህበረሰቡ ውስጥ ማህበራዊ ለውጥ የሚያመጣ አሳታፊ
የማህበራዊና የማቴሪያል ልቀት በማምጣት አብዛኛውን የማህበረሰብ
ክፍል በአካባቢው ላይ ተቆጣጣሪና ከአካባቢው ተጠቃሚ የሚያደርግ
ሂደት ነው፡፡
ከሮጀርስ ትርጉም መረዳት የሚቻለው ልማት ማለት ሂደት ነው፤ ልማት ማለት
ማህበራዊ ለውጥን ያመጣል፣ ልማት ማለት አብዛኛውን የማህበረሰብ ክፍል
ይጠቅማል፣ ልማት ማለት መሻሻል ነው፡፡
ልማትን በተመለከተ ለረዥም ጊዜ ሁለት ዓበይት አስተሳሰቦች ብቻ ነበሩ፡፡ ይኌም
ዘመናዊነት (Modernaization paradigm) ና ጥገኝነት (Dependecy paradigm)
ናቸው፡፡ ሁለቱ ፅንፍ አስተሳሰቦች ልማትን በማምጣት ድሃ የዓለማችን ክፍሎችን
ማሳደግ የሚቻልበት ሁኔታ በተለያየ መንገድ ቀይሰዋል፡፡ የዘመናዊነት አስተሳሰብ ለድሃ
አገሮች መሰረታዊ ችግራቸው ኋላቀርነታቸው ሲሆን ማደግ የሚችሉት ምዕራባውያን
አገሮች በሚሰጧቸው እርዳታ ዝግመታዊ በሆነ መልኩ ይለማሉ የሚል ነው፡፡ በአንፃሩ
የጥገኝነት አስተሳሰብ አራማጆች የሚሉት የደሃ ሃገሮች ችግር የምዕራባውያን ቅኝ
ግዛትና ጭቆና ነው ስለሆነም መፍትሄው የእነሱን እርዳታ መቀበል ሳይሆን ከእነሱ ጋር
6
ያለውን ግንኙነት በማቋረጥ ለራስ መስራት ነው ይላሉ፡፡ በዚህ መሃል የሁለቱ ፅንፍ
የወጣ አስተምህሮ ዓለማችን በግሎባላይዜሽን ዘመን አንዱ ለአንዱ አስፈላጊ ስለሆነ
የሚያስሄድ ስላልሆነ ሶስተኛ አማራጭ “ሌላው አስተምሮ” የሚል የሶስተኛ ዓለም
ሃገራት ፈጠሩ፡፡ ይህ አስተምሮ ልማትን ማየት የሚፈልግበት ዕይታ ልማት መጀመር
ያለበት ታች ካለው ተራ ህዝብ ሲሆን የሃገሩን ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሥነ-ምህዳሩን
በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ይላሉ፡፡ ስለዚህ ይህንን አማራጭ በመያዝ ማህበረሰብን
ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ሲሰሩ በዋናነት የሚከተሉት ማህበረሰቡን
ያሳተፈና ተጠቃሚ የሚያደርግ አካሄድን መሆን ይኖርበታል፡፡ ተራውን የማህበረሰብ
ክፍል ለማሳተፍ ደግሞ የመረጃ ተደራሽነት በዘልማዳዊው ሚዲያ አስቸጋሪ ስለሚሆን
የማህበረሰብ ሚዲያ ወይም የማህበረብ አገልግሎት የሚሰጡ የሬዲዮ ጣቢያዎች
በየአካባቢው መኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡
1.1 የማህበረሰብ ሚዲያ ምንድን ነው?
በአሁኑ ሰዓት የማህበረሰብ ሚዲያ በተደራሽነቱና በሚሰጠው አገልግሎት
ከመንግስታትና ከልማት ድርጅቶች በሰፊው ዕውቅናን እያተረፈ ይገኛል፡፡ ምክንያም ይህ
የሚዲያ ዘርፍ በዋናነት ድምፅ አልባ የነበሩትን ደሃና የተገለሉ/ የተረሱ የማህበረሰብ
ክፍሎችን ድምጽ የሚሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ የማህበረሰብ ሚዲያ የለውጥ አካል ሲሆን
በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ-ልቦናዊ ለውጦች እንዲመጡ
ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል፡፡ ይህ ሚዲያ ለአካባቢው ተራ የማህበረሰብ ክፍሎች
የውይይት መድረክን በመክፈት ድምጻቸው እንዲሰማ በማድረግ ያገለግላል፡፡ ይህ ሚዲያ
የሚቋቋመው ለማህበረሰቡ ሲሆን የሚያስተዳድረውም የሚደግፈውም ራሱ ማህበረሰቡ
ነው፡፡ የማህበረሰብ ሚዲያ አካባቢያዊነት፣ የብዙሃን ተሳትፎ፣ እና የለውጥ ተምሳሌት
መሆን የሚታወቅባቸው ባህርያቶቹ ናቸው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አሰራር ደግሞ የማህበረሰብ ሚዲያ ማለት
ለትርፍ ያልተቋቋሙ የሬዲዮ ወይም የቴሌቪዥን አገልግሎት ሲሆን በህዝቡ ፍላጎትና
ይሁንታ በመቋቋም የአንድ የተወሰን ቦታ ላይ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ፍላጎት
በማንፀባረቅ በእነሱው የሚቋቋምና የሚሰራ አገልግሎት ነው፡፡ ይህም ማለት
የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለቤቱም፣ ሰራተኞቹም፣ አስተዳደሮችም ራሱ የማህበረሰቡ አካላት
ማለት ነው፡፡
7
የማህበረሰብ ሬዲዮ አራቱ መርሆች ብሎ ጃን ሰርቪያስ (2007) ያስቀመጣቸው
የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ባለቤትነቱ የማህበረሰቡ ነው፤
2. የሚሰጠው አገልግሎት ለማህበረሰቡ ነው፤
3. ህዝብን አሳታፊ መሆን አለበት እና
4. ለትርፍ የማይሰራ ተቋም
የማህበረሰብ ተሳትፎ የማህበረሰብ ሚዲያ ቁልፍ ተግባር ሲሆን በሌሎች የሚዲያ
አማራጮች ድምፃቸውን ማሰማት ያልቻሉትን የማህበሰብ ክፍሎች እንዲናገሩ እና
እንዲወያዩ ማስቻል አለበት፡፡ ስለዚህ የማህበረሰቡ ክፍሎች ከአድማጭ ወደ ተሳታፊ
ይቀየራሉ ማለት ነው፡፡
የማህበረሰብ ሬዲዮ በኢትዮጵያ በሚያስገርም ፍጥነት ከመንግስትና ከግሉ ሚዲያ በኋላ
ተነስቶ በአሁኑ ሠዓት 30 የሚደርሱ የሬዲዮ ጣቢያዎች ከመንግስት ፈቃድ አግኝተው
በሥራ ላይ ናቸው፡፡ የማህበረሰብ ሬዲዮ አሰራር መመሪያ ቁጥር 04/2004 መሰረት
በኢትዮጵያ የተለያዩ የማህበረሰብ ሬዲዮ አገልግሎቶች በመከፈት ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ
የሬዲዮ ጣቢያዎች የልማታዊ ጋዜጠኝነትን ሥራ እንዲያከናውኑ በማሰብ ነው
የሚቋቋሙት፡፡
የመወያያ ጥያቄዎች
 የማህበረሰብ ሬዲዮ ምንድን ነው?
 የማህበረሰብ ሬዲዮ አገልግሎቱ ለማን ነው?
 የማህበረሰብ ሬዲዮ ከሌሎች የሬዲዮ ወይም የሚዲያ ተቋማት
በምን ይለያል?
1.2 ልማታዊ ጋዜጠኝነት ማለት ምን ማለት ነው?
ጋዜጠኝነትና ልማት እንደጓድ፣ እንደአቀጣጣይ ወይም ደግሞ እንደተች/ቃፊር ያለ ግንኙነት
አላቸው፡፡ የልማታዊ ጋዜጠኝነት ፅንሰ ሃሳብ በምዕራብ ሃገራት የዜና አሰራር ላይ ደስተኛ
ያልሆኑ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች በ1980ዎቹ ላይ የፈጠሩት የሚዲያ ፍልስፍና ነው፡፡ እንደ
ሚዲያ ንድፈ ሃሳቦች ሚዲያ ብሄራዊ ልማት እንዲፋጠን የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ
ልማቶችን በማቀናጀት ከፍተኛ ሥራ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ልማታዊ ጋዜጠኝነት ልማታዊ
8
አጀንዳዎችን በትልቁም ሆነ በትንሹ በጥልቀት እየፈተሸ ይሰራል፡፡ የልማት ፕሮጀክቶችን
ተገቢነት እና አካሄድ ላይ የመደገፍ ሥህተቶች ካሉም የማጋለጥ ሥራ ይሰራል፡፡ በአጠቃላይ
ልማታዊ ጋዜጠኝነት የሚያተኩረው ልማት ተኮር የሆኑ ዜናዎችን መረጃ በመሰብሰብ
ለማህበረሰቡ ማድረስ ላይ ነው፡፡ የልማታዊ ጋዜጠኝነት ቁልፍ ተግባራት (አጋራዋል፣ 1980)
1. በዕቅድና በትግበራ መካከል ያለውን ልዩነት መዘገብ፤ በማኅበረሸቡ ላይ ያለውን
ተፅዕኖም ማጋለጥ፤
2. በዕለት ከዕለት ዜናዎች ሳይሆን በዘላዊ የልማት ሂደቶች ላይ ማተኮር
3. ከመንግስት ነፃ ሆኖ ለመንግስት ገንቢ አስተያየቶችን መስጠት
4. ለሃገር ግንባታ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ
5. ደሃና ተራ የማህበረሰብ ክፍሎችን አቅም ማጎልበት
የቡድን ውይይት
ውድ የዚህ ስልጠና ተካፋዮች የማህበረሰብ ሬዲዮ የልማታዊ ጋዜጠኝነት
ማሳያ የልማት አጋር ነው ሲባል ምን ለማለት ተፈልጎ እንደሆነ በቡድን
ተወያይታችሁ አብራሩ፡፡
በዚህ የማህበረሰብ ሬዲዮ የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄ መመለስ
የሚቻልበትን መንገድ በመነጋገር አብራሩ፡፡
ማጠቃለያ
የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ማህበረሰቡ ድምጹን የሚያሰማባቸው፣ ሃሳቡን
የሚያስተናግድባቸው፣ የማህበረሰቡን ችግር በጋራ በመወያየት የሚፈታባቸው ራሱ
ህዝቡ የሚያቋቁማቸውና የሚሰራባቸው ሲሆኑ አሰራራቸውም ሆነ አገልግሎታቸው
ህዝባዊ ነው፡፡ ስለሆነም በሌሎች የሚዲያ ተቋማት ላይ አየር ላይ ለመዋል
ያልቻልሁትን የአካባቢው ማህበረሰብ ድምፆች ያሰማል፡፡
9
ክፍል ሁለት
2. የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አዘገጃጀት
2.1 ዜና
2.1.1 ዜና ምንድን ነው?
የመወያያ ጥያቄዎች
 ዜና ምንድን ነው?
 በየቀኑ ምን ያህል ዜና ትሰማላችሁ?
 ዜና ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም?
ዜና ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ሁሌም ለጋዜጠኝነት ሙያ ቅርብ የሆነ ሰው
ወይም ደግሞ ዘወትር ምሽት በጉጉት ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን የሚከታተል ሰው
በቀላሉ ይመልሰዋል፡፡ በርካታ ቤተሰቦች በዜና ሰዓት ህጻናትን ዝም በሉ ወይም ከሌሎች
ሰዎች ጋር ያወሩበት የነበረውን ጉዳይ ቆም አድርገው በትኩረት የሚከታተሉት
የብዙሃን መገናኛ ገፀ በረከት ዜና ነው፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ዓለማችን እንዴት ዋለች?
ለሚለው ጉዳይ በቂ መልስ የሚሰጠው ዕለታዊ ዜና ስለሆነ ነው፡፡
በማንኛውም የብዙሃን መገናኛ ማለትም በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በጋዜጣ፣ በመፅሔት
ወይም በኢንተርኔት ዜና ከሌሎች የብዙሃን መገናኛ በተሻለ አስፈላጊና የአድማጭ
ተመልካችን ቀልብ መግዛት የሚችል የጋዜጠኝነት ዘውግ ነው፡፡ ስለሆነም ጥራት ያለው
የዜና ዝግጅት ደግሞ አስፈላጊ ነው፡፡ አሁን ዓለማችን በሉላዊነት ምክንያት በጠበበችበት
ሰዓት ቴክኖሎጂ በየቀኑ እንደአሸን በሚፈላበት ወቅት ብዙ ምርጫ ያለውን አንባቢ፣
አድማጭ ወይም ተመልካች ይዞ መገኘትና መዝለቅ ትልቅ ችሎታ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ
በዚህ ውድድር በበዛበት የብዙሃን መገናኛ ሥራ ውስጥ በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና
ልምድ ያካበቱ ጋዜጠኞች ዜናን መስራት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው
ምን ያህሉ ሙያዊ ጋዜጠኞች ጥራት ላለው ዜና ትኩረት እንደሚሰጡ ነው፡፡
10
አያሌ የጋዜጠኝነት ምሁራን “ዜና” ለሚለው ቃል የተለያዩ ትርጎሞች ይሰጡታል፡፡
የትርጉማቸው መሰረተ ሃሳብ አንድ ቢሆንም የአተረጓጉም ዘይቤያቸው ግን በመጠኑ
ልዩነት አለው፡፡ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የዜና አቻ ትርጉም ነው የሚባለው “News”
የሚለውን ቃል ከቁም ትርጉሙ ሌላ ሁለት ዓበይት ቁምነገሮች ያንፀባርቃል፡፡ አንደኛው
የቃሉ ዝርዝር ፊደላት N (North) ሰሜን, E (East) ምስራቅ, W (West) ምዕራብ እና
S (South) ደቡብ ማለት ነው ይላሉ፡፡ ስለዚህ “News” በሚለው ቃል ውስጥ ያሉት
አራት ፊደላት አራቱን መልክዓ ምድራዊ የዓለም ማዕዘናት ይጠቁማሉ ማለት ነው፡፡
ሁለተኛው “News” (ዜና) ከሚለው ቃል የሚገኘው ቁም ነገር ጋዜጣ “Newspaper”
ለሚለው የእንግሊዘኛ ቃል መነሻ ወይም መሠረት መሆኑ ነው፡፡ ብዙዎቹ የሙያው
ምሁራን ዜናን ዜና የሚያደርገው በዜና መልክ መዘጋጀቱ ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰቡ
መሰራጨቱ ነው ይላሉ፡፡
የኦክስፎርድ እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት ዜና ማለት አዲስ፣ መሳጭ፣ እውነትና
ያልተለመዱ ክስተቶች ዘገባ ነው ይላል፡፡ ይህም ማለት አብዛኛው ጋዜጠኛ ስለዜና
ያለውን ግንዛቤ ማካተት የሚችል ይመስላል፡፡ ዜና ስለአንድ የህብረተሰብን ትኩረት
በብርቱ ሊስብ ስለሚችል ወይም በህዝብ ህይወት ላይ ተፅዕኖ ስላለው ክስተት ለጋዜጣ፣
ለዜና መፅሔት፣ ለዜና አገልግሎት፣ ለሬዲዮና ለቴሌቪዥን፤ በአጠቃላይ ለብዙሃን
መገናኛ የሚዘጋጅ ዘገባ ነው፡፡ ሌላው በኦክስፎርድ እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ
ካለው ትርጓሜ የምንረዳው ዜናን ዜና የሚያደርገው አዲስነቱ ነው፡፡ ሁልጊዜም ሠዎች
ከለመዱትና ከሰለቻቸው ውጭ የሆነን ጉዳይ ጆሮ ሰጥተው ስለሚያዳምጡ ነው፡፡
ለዚያም ነው የዜና ቋንጣ የለውም እየተባለ በወቅቱ አየር ላይ ወይም ህትመት ላይ
ያልዋሉ ጉዳዮች እንደዜና የማይቆጠሩት ወይም የማይቀርቡት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
ዜና ሁሌም በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡
ሌላው የጋዜጠኝነት ትርጓሜ ደግሞ የታሪክ የመጀመሪያ ንድፍ ነው ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ
በችሎላ የሚዘጋጅ ሥነ-ፅሁፍ ነው ይላሉ፡፡ ስነ-ፅሁፍም ሆነ የታሪክ ፅሁፍ በአንድ
ወቅት የዜና አካል የነበረ ስለሆነ ነው ይህንን ትርጓሜ የሚሰጡት፡፡ ለምሳሌ በአንድ
ወቅት በሃገራችን ተከስተው ያለፉ ጉዳዮች ዛሬ ላይ ታሪክ ቢሆኑም በወቅቱ ግን
በየብዙሃን መገናኛዎቹ ዋነኛ የዜና ዘገባዎች ነበሩ፡፡ በቅርብ ታሪካችን ውስጥ ያሉትን
ለመጥቀስ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ ምርጫ 97፣ የኢትዮጵያ ሚሊኒየም፣ የጠቅላይ
11
መለስ ዜናዊ ህልፈተ-ህይወት አሁን ላይ ታሪክ ቢሆኑም በወቅቱ ግን የተመረጡ
ዜናዎች ነበሩ፡፡
ዜና ሰውን የሚያስደነግጥ፣ የሚያስገርም ወይም የሚያስደንቅ፣ የሚያስደስት ወይም
የሚያሳዝን የአዳዲስ ኩነቶች መገለጥ፣ የአዳዲስ ድርጊቶች መፈፀም፣ መታወጅ፣ ወይም
የአንድ ክስተት ይፋ መሆን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዜና ማለት ሰው ሲሰማው
እውነታቸውን ነው እንዴ? በማለት በታላቅ አግራሞት እና መደናገጥ የሚቀበለው ወሬ
ወይም መረጃ ነው፡፡ አንድ አባባል አለ፤ “ውሻ ሰው በላ” እና “ሰው ውሻ በላ” የሚሉ
ሁለት ጉዳዮች ቢቀርቡ ዜና የሚሆነው “ሰው ውሻ በላ” የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም ዜና
ማለት ያልተለመደና ሲሰሙት አግራሞች የሚያጭር መሆን ስላለበት ነው፡፡
ዜና ማለት ሰዎች ናቸው የሚል ትርጉምም ይሰጠዋል፡፡ ሰዎች
የሚናገሩት፣ ሰዎች የሚሰሩት ሁሉ ዜና ነው፡፡ ስለዚህ ከሰዎች
ንግግር፣ተግባር፣ ዕቅድ፣ ሥራ፣ ግጭት እየወሰድነ የምናቀርበው
ስለሆነ ዜና ማለት ሰዎች ማለት ነው የሚል ትርጉም ለዜና
ይሰጠዋል፡፡ በአጠቃላይ ዜና የአንድን ሁነት የመንገር ጥበብ ነው፡፡
2.1.2 የዜና ዓይነቶች
ዜና ሁሌም በተመሳሳይ መልኩ አይፃፍም፡፡ ይኸውም የዜናው ዓይነትና በምን መልኩ
ቢቀርብ ይሻላል ከሚለው አንጻር ነው የሚታየው፡፡ ለምሳሌ የሚከተሉትን ዜናዎች
ተመልከቱ፡፡
1. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ፡፡
2. ኢትዮጵያን ላለፉት 38 ዓ.ም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በትግልና በአመራር ሲመሩ
ነበር፡፡ በተለይም ባለፉት 21 ዓመታት የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው
አገልግለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ካሳለፍነው የግንቦት ወር ጀምረው
ህመም ስለተሰማቸው ለህክምና ውጪ ሲመላለሱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
ትናንትና ማታ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ አረፉ፡፡
ዜና በሁለት መልኩ ሊፃፍ ይችላል፡፡ ይኸውም በቀጥታና በተዋዛ መልኩ፡፡
12
1. የቀጥታ ዜና (Hard News)
የቀጥታ ዜና አንድን ድርጊት በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወዲያኑና በወቅቱ
የሚዘገብ የዜና ዓይነት ነው፡፡ የቀጥታ ዜና የሚጀምረው በድርጊቱ ውስጥ በጣም
ጠቃሚ በሆነው ጉዳይ ሲሆን ነገሮችን በትኩሱ ማቅረብ ዋነኛ መለያው ነው፡፡
አቀራረቡም የተከሰተውን ጉዳይ ቀላል፣ ግልፅ፣ ቀጥተኛና እውነተኛ በሆነ መልኩ
ያቀርባል፡፡ የቀጥታ ዜና በአብዛኛው ኩነት-ተኮር (Event-oriented) ነው፡፡ ኩነቱን
በተመለከተ ቀጥተኛ የሆነ የዜና አቀራረብ መንገድ ይጠቀማል፡፡ በርካታ ኩነቶች በቀጥታ
የዜና አቀራረብ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል ለምሳሌ ያህል መፈንቅለ
መንግስት፣ ሹምሽር፣ ምርጫ፣ የፖሊስ ሪፖርት፣ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣ ግድያ፣
መንግስታዊ ስብሰባዎች፣ ህዝባዊ መድረኮች፣ የአየር ንብረት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የዋጋ
ጉዳይ (ገበያ ነክ ዜናዎች)፣ .. ወዘተ ናቸው፡፡
የቀጥታ ዜና በሚፃፍበት ጊዜ መረጃን ማዛባት፣ በተገቢው ቦታ አለማስቀመጥ፣ ወይም
የተሳሳተ ነገር መጨመር ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡ ምክንያቱም በዜናው መንስኤ ከፍተኛ
የሆነ ህዝባዊና አገራዊ አደጋ ስለሚያስከትል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ድምዳሜ
መስጠት፣ አሉባልታዎችን ማካተት፣ የግል አመለካከትንና ያልተጣሩ ተባራሪ ወሬዎችን
ማካተትም አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የቀጥታ ዜናዎች በአድማጭ ተመልካች ላይ
ያላቸው ተፅዕኖ ከፍተኛ ስለሆነ ነው፡፡
2. የተዋዛ ዜና (Soft News )
የተዋዛ ዜና ወይም ዋዘኛ ዜና ከቀጥታ ዜና ጋር ሲወዳደር በዜና አፃጻፉ የተለየ የራሱ
የሆኑ ባህርያት አሉት፡፡ ይኸውም ለሁነቶች እና ለጊዜ ትኩረት አይሰጥም፡፡ ይልቁንም
ለሰው ስሜት ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነውው፡ በአብዛኛው ጊዜ ለብዙዎቹ እንደ
አማራጭ የሚቀርብ የዜና ዓይነት ነው፡፡ የተዋዛ ዜና ተዋዝቶ የሰውን ስሜት በሚነካ
መልኩ የፀሐፊው ችሎታ እና አቅም ተጨምሮበት የሚፃፍ ዜና ሲሆን ለመስማት፣
ለማንበብ ወይም ለማየት ማራኪ፣ አጓጊ እና አስደሳች ሆኖ የሚቀርብ ነው፡፡ የተዋዛ
ዜና በአድማጭ ላይ እዚህ ግባ የሚባል ተፅዕኖ ማሳደር ባይችልም እንኳ በዕለት ከዕለት
ህይወት ውስጥ ያለውን የማህበራዊ ሁኔታና የሁኔታዎች ለውጥ ለማወቅ ይረዳል፡፡
13
ለምሳሌ ያህል ግለታሪኮች፣ የመዝናኛ ወሬዎች፣ ባህላዊ ወጎችና የመሳሰሉት የሚጠቀሱ
የተዋዛ ዜና ሁነታዎች ናቸው፡፡
2.1.3 የዜና ጠቀሜታዎች
በርካታ የዘርፉ ተመራማሪዎች ሠዎች ለምን ዜናን ይከታተላሉ የሚለውን ጥያቄ
ለመመለስ በርካታ ጥናት አካሂደዋል፡፡ አንዳንዶቹ የተፈጠረውን ለማወቅ፤ ሌሎች ደግሞ
የሚፈጠረውን ወይም ይፈጠራል ተብሎ የሚጠበቀውን ለማወቅ ዜናን ይከታተላሉ፡፡
የዜና ዘገባ በተወሰ ጊዜ የተለያዩ ዘርፈ-ብዙ መረጃዎችን መስጠት ስለሚያስችልም የራሱ
የሆነ አውንታዊ ሚና አለው ምን እንኳ ይህንን የሚቃወሙ ባይጠፉም፡፡
የሰው ልጆች ለምን ዜናን ይከታተላሉ ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሆኑ ዋና ዋና
ምክንያቶችን እንደሚከተለው ለማየት ተሞክሯል፡፡
1. በሰውና በንብረት ላይ ከሚደርስ አደጋ ለመጠንቀቅ፡፡ በዜና አማካኝነት በሰውና
በንብረት ላይ በጦርነት፣ ግጭት፣ በተፈጥሮ አደጋ፣ በወረርሽኝ፣ በተመረዙ
ምርቶች ወዘተ አማካኝነት የሚደርሱ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት
የማስጠንቀቂያ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ስጋት ላይ
የጣለው የኢቦላ ወረርሽኝ ብዙሃን መገናኛዎች የሚሰጡት የማስጠንቀቂያ ዜና
ለዚህ ምርጥ ምሳሌ ነው፡፡
2. ምን እንደተፈጠረና ሊፈጠር እንደሚችል መንገር፡፡ በዜና በዓለም ላይ ምን
እየተካሄደ እንዳለና ሊፈጠር የሚችል ጉዳይ እንዳለ በዜና አውታሮች አማካኝነት
ማወቅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የልማት ዘገባዎች፣ የመድኃኒት መፈብረክ፣ በጤና፣
በትምህርት፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚወጡ ልማቶችንና
ለውጦችን በተመለከተ የመንገር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ መንግስት
ለመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሬ አደረገ እና መንግስት ለመንግስት
በቡድን በቡድን ሆናችሁ አንድ ቀጥተኛ ዜናና አንድ ደግሞ የተቃዛ ዜና
ጻፉ፡፡
14
ሠራተኞች ከሃምሌ ጀምሮ የደመወዝ ጭማሬ ሊያደርግ ነው የሚሉ ዜናዎች
የዜናን የመንገር ጠቀሜታ ያሳያሉ፡፡
3. ለሰው ልጅ ነፃነት ስጋት የሆኑ ነገሮችን ማጋለጥ፡፡ ለሰው ልጅ ስጋት የሆኑትን
ጉዳዮች ማለትም ኢ-ፍትሃዊነት፣ ሙስና፣ ሽብርተኝነት፣ ሰብዓዊ መብት ረገጣ፣
የጉልበት ብዝበዛ፣ ፖለቲካዊ ጭቆና ወዘተ ዓይነት ጉዳዮች ለሰው ልጅ ነፃነት
ስጋት በመሆናቸው ሊወገዱ ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዜና የማጋለጥ ተግባር
ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ በዜና የማጋለጥ አገልግሎት ዜና እንዲከታተሉ
የሚያደርግ ምክንያት ነው፡፡
4. የህብረተሰቡን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ መሸሻል እንዲመጣ መርዳት፡፡
ስለኢኮኖሚ፣ ልማት፣ ሥራ፣ ወዘተ ዓይነት ዜናዎች የህብረተሰቡን ኑሮ
እንዲሻሻል የሚረዱ ስለሆነ ዜና የኑሮ መሻሻል እንዲመጣ ጠቀሜታ አለው፡፡
ማንኛውም የብዙሃን መገናኛ የሚሰጣቸው ጥቅሞች አሉት፡፡ ይኸውም ማሳወቅ፣
ማስተማርና ማዝናናት ናቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ የማሳወቁ ሥራ የሚሰራው
በዜና ሲሆን ይህም የኑሮን ሁኔታ መሻሻል እንዲመጣ ወይም የመጣውን
ለማወቅ ዜናን ይከታተላሉ፡፡ ለምሳሌ የማዳበሪያ ዋጋን በተመለከተ የሚሰራጭ
ዜና በአርሶ አደሩ ህይወት ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ስላለው ዜናን አፅንዖት
ሠጥተው ይከታተላሉ፡፡
5. ብልሹ የአኗኗር ዘይቤን እንዲሻሻሉ ያግዛል፡፡ ስለህዝብ ሰፈራ፣ የወንጀል
ድርጊት፣ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ አካባቢያዊ ጉዳዮች፣ የቤት ጉዳይ እና
የመሳሰሉት ዜናዎች የህብረተሰቡን የአኗኗር ችግሮችን እንዲቀርፉ
የሚነደፉትንና ሚከናወኑትን ተግባራት በዜና መከታተል ጠቃሚና የዜናን ሚና
ያመለክታል፡፡
2.1.4 የዜና ጥንካሬዎችና ድክመቶች
ዜና በጣም ከፍተኛ የሆነ ተፈላጊነት ያለው የጋዜጠኝነት ዘውግ ነውው፡ ይኸውም ሰዎች
ለተለያዩ ምክንያቶች ትኩረት ሰጥተው የሚከታተሉት ዘውግ፡፡ ዜና የራሱ የሆነ የአፃፃፍ
ስልት ያለው ሲሆን በቀጥታና በተዋዛ መል ይቀርባል፡፡ ዜና የራሱ የሆነ ጠንካራና
ደካማ ጎኖች አሉት፡፡
15
የዜና ጥንካሬዎች
 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መረጃን ይሰጣል
 አዲስና ተገቢነት ያለው መረጃ ያቀብላል
 የአድማጭ ተመልካችን አቅም ያጎለብታል
 ዕውቀትን ያሳድጋል
 ሚዛናዊነትን ያበረታታል
 አድማጭ ተመልካቾች ሃሳባቸውን እንዲገልፁ ይረዳል
የዜና ድክመቶች (ውስንነቶች)
 በጣም አስፈላጊ ነገሮችን ብቻ ያቀርባል፤ ስለሆነም ብዙ ዝርዝር መረጃዎችን
አያደርስም
 በቦታና በጊዜ የተገደበ ነው፡፡ ይኸውም የምንፅፈው ለጋዜጣ ከሆነ በወረቀቱ ልክ
ለብሮድካስት ከሆነ ደግሞ በአየር ሰዓቱ ልክ የተገደበ ነው
 ብዙ ግብዓት ይፈልጋል በተለይም የቴሌቪዥን ዜና በርካታ የሰውና የንብረት
ግብዓቶችን ይፈልጋል፡፡
2.1.5 የዜና መመዘኛ እሴቶች
የተፃፉ ዜናች ሁሉ አይታተሙም ወይም አየር ላይ አይውሉም ምክንያቱም ዜና
መሠረታዊ የሆነ የዜና አፃፃፍ እሴቶችን አሟልቶ የቃፊሮችን (Gatekeepers) መመዘኛ
አሟልቶ የይታተም ወይም የይሰራጭ ይሁንታ ማግኘት አለበት፡፡ የቃፊሩን ይሁንታ
ያላገኘ ዜና አይታተምም ወይም አየር ላይ አይውልም ማለት ነው፡፡ ቃፊር ማለት
በዕየለቱ የሚቀርቡ ዜናዎች ላይ ከፍተኛ ዋሳኔ የሚሰጡ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ
ቃፊሮች የዜናውን ጥሩነት የሚመዝኑት ደግሞ ከዜና መመዘኛ እሴቶች አንፃር ነው፡፡
ዜና በምታዳምጡበት ጊዜ በጣም ጆሮ የምትሰጡት ይዘቱ ምን ሲሆን
ነው? የማታዳምጡትስ?
16
ነገር ግን እነዚህ እሴቶች በመጠቀም ዜናው በሚገመገምበት ሰዓት ከግምት ውስጥ
የሚገቡ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነዚህመም ሁኔታዎች
1. የሪፖርተሩ የጀርባ ታሪክና ልምድ
2. የብዙሃን መገናኛ ተቋሙ መስፈርት
3. የገበያ ሁኔታ
4. የአድማጭ ተመልካች ፋላጎት ናቸው፡፡
ምንም እንኳ እነዚህ ሁኔታዎች ዜናን በዜና እሴቶች መሰረት የመመዘኑን ጉዳይ ተፅዕኖ
ቢያደርጉበትም በአብዛኛው ግን የሚታዩት ከእሴቶች አንፃር ነው፡፡ እነዚህም እሴቶች
እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
1. የጉዳዩ ቅርበት (Proximity)
ዜና በጂኦግራፊካል አቀማመጥ ወይም ለሰዎች ሥነ-ልቦና ቅርብ የሆነ ጉዳይ መሆን
አለበት፡፡ አንድ ሁነት በዜና መልክ እንዲቀርብ ከሚያደርገው ነገር አንዱ የጉዳዩ ቅርበት
ነው፡፡ የዜና ሁነቶች ለግለሰቦች ወይም ለአካባቢው የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡
አንዳንዱ ተፅዕኖ በቀጥታ ይሆናል፡፡ አካባቢያዊ ወይም ሃገራዊ ዜናዎች ለሌሎች የዓለም
ክፍል ዜናዎች የተሻለ ተደማጭነት ወይም ተነባቢነት አላቸው ምክንያቱም የአድማጭ
ተመልካች ቀልብና ሃሳብ መግዛት ስለሚችሉ እና ተገቢነትና ተፅዕኖ ስላላቸው ነው፡፡
ነገር ግን አንዳንድ ሁነቶች የዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛን ትኩረት ይስባሉ፡፡ ያም
የሚሆነው የጉዳዩን ዓለምአቀፋዊነት ሰፊ ስለሆነ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከአካባቢያዊ ወይም
ብሔራዊ ዜናዎች በላይ ከአድማጮች ትኩረት አያገኝም፡፡ ምንም እንኳ ሉላዊነት
እየተስፋፋ ቢሄድም ብዙውን ጊዜ ሰዎች ስለአካባቢያቸው መስማት ወይም ማወቅ
ይፈልጋሉ፡፡ ለምሳሌ ስለተፈጥሮ አደጋዎች፣ ምርጫ፣ ሽብርተኝነት፣ የልማት ወሬዎች፣
ወዘተ በአካባቢው አድማጭ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጥባቸዋል፡፡
እስኪ የሚከተሉትን ሁለት ዜናዎች አወዳድሩ፡፡
1. አይ ሲ አይ ኤስ የተባለው የሽብር ቡድን በኢራቅና በሶሪያ የሚገኙ በርካታ
ንፁሃን ዜጎችን ገደለ፡፡
2. አል-ሸባብ በኢትዮጵያ ሱማሌ ድንበር መሸገ፡፡
17
ከነዚህ ሁለት ዜናዎች የትኛው ዜና የበለጠ ለኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት
አድማጭ ተመልካች ትኩረት ይሰጠዋል? ለምን?
አንዳንድ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ደግሞ የበለጠ ቅርብ የሚሆኑበት አጋጣሚ አላቸው፡፡
ለምሳሌ የነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ የታላላቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኪሳራ፣ የአስከፊ
ወረርሽኝ መከሰት፣ ወዘተ ናቸው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት የዓለማችን አንገብጋቢ ዜናዎችን
መስራት የምንችለው ደግሞ ከአገራችን አውድ ጋር በማዛመድ ነው፡፡ ስለዚህ ዜናችን
ተፅዕኖ መፍጠር እንዲችል ተገቢነት ያስፈልገዋል፤ ተገቢነት እንዲኖረው ደግሞ ቅርበት
ሊኖረው ይገባል፡፡
በአጠቃላይ አንድ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለሚገኝ ግለሰብ መጀመሪያ ስለደብረ
ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፤ ከዚያም ስለጎጃምና አካባቢው፤ ቀጥሎ ስለአማራ፣ ስለኢትዮጵያና
ስለአፍሪካ እያለ ስለተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ቢነገረው ትኩረት የመስጠት
ሁኔታውም በየደረጃው ከፍ እያለ የሚሄድበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
2. የባለጉዳዮች ታዋቂነት (Prominence)
አንዳንድ ጊዜ ስም በራሱ ዜና የሚሆንበት አጋጣሚ አለ፡፡ ታዋቂ የሆነ ሰው ትልቅ ዜና
መሆን ይችላል፡፡ ይኸውም የሚሰራው ሥራ ሳይሆን የሰራው ሰው ታዋቂነት መሰረት
ያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ በቀላሉ የሚያውቃቸው ሰዎች የያዘ ዜና ተመራጭ
ነው፡፡ ምክንያቱም በፖለቲካው፣ በስፖርቱ፣ በሙዚቃው፣ በመዝናኛው፣ በንግዱ ወዘተ
ዘርፎች ታዋቂነት ያላቸው ሰዎችን ጉዳይ ለዜና መጠቀሙ የዜና መመዘኛ እሴቱን
ስለሚጨምር ነው፡፡
ለምሳሌ፡
1. አቶ አበበ ተሰማ አረፉ፡፡
2. አትሌት ቀነኔሳ በቀለ ጉንፋን ይዞታል፡፡
የሚሉ ሁለት ዜናዎች ብትሰሙ የትኛውን ነው የበለጠ ጆሮ የምትሰጡት? መቼም
የአቶ ናንቦኒ ሞት ከቀነኔሳ ጉንፋን የበለጠ ቢሆንም አቶ ናንቦኒ ምን እንደሆኑ
ስለማናውቅ የቀነኔሳን ጉዳይ ነው ከፍተኛ ትኩረት የምንሰጠው፡፡ ስለዚህ የታዋቂ
18
ሰዎችን የስኬት፣ የውድቀት፣ አስተዳደግ፣ ውሎና አዳር፣ ሽንፈትና ድል እንዲሁም
ውስጠ-ምስጢራቸውን ማወቅ ለሚፈልግ አድማጭ ተመልካች ያንን ይዞ መገኘት ትልቅ
የዜና እሴት ነው፡፡ በዜና ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ስም ካለበት ዜናው የዕለቱ ዜና ተደርጎ
ይቀርባል፡፡
እስኪ የሚከተሉትን ሁለት አርዕስተ-ዜናዎች በማንበብ ቀጥለው ያሉትን ጥያቄዎች
መልሱ፡፡
1. የሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ ሃይማኖቱን ቀየረ፡፡
2. አቶ አበበ ከበደ ሃይማኖቱን ቀየረ፡፡
ከሁለቱ ዜናዎች የትኛውን ማዳመጥ ነው የምትፈልጉት? ለምን?
በተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ አንዱን ዜና ከሌላው እንድናበላልጥ የሚያደርገን ምንድን
ነው?
3. ወቅታዊነት (Timeliness)
ዜናን ዜና የሚያሰኘው አዲስ ነገር ይዞ መገኘቱ ነው፡፡ በአገራችን የዜና ቋንጣ የለውም
ይባላል፡፡ ይህም ማለት አንድ ድርጊት እንደተከሰተ ወዲያውኑ መደበኛ የሆኑ የጋዜጠኛ
ጥያቄዎችን መመለስ ይጠበቅበታል፡፡ እነዚህም ጥያቄዎች በእንግሊዘኛ 5 W and H
questions በመባል ይታወቃሉ፡፡
 ምን ተከሰተ?
 ማን ፈፀመው?
 መቼ ተከፈተ?
 የት ተከሰተ?
 ለምን ተከሰተ? እና
 እንዴት ተከሰተ? የሚሉት ናቸው፡፡
ስለዚህ ድርጊቱ በተከሰተበት ፍጥነት፤ ቴክኖሎጂው እስከፈቀደ ድረስ ዜና በፍጥነት
ወቅቱን ጠብቆ መሠራት አለበት፡፡ የብሮድካስት ሚዲያ በተለይ ሬዲዮ በቀጥታ በቀላሉ
ነገሮችን ለማስተላለፍ ይረዳል፡፡ ወቅታዊነት በብሮድካስትና በህትመት የብዙሃን
19
መገናኛዎች እኩል አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንደብሮድካስት ሚዲያ በፍጥነት በህትመት
ውጤቶች ላይ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡ ይኸውም የህትመት መውጫ ቀን መጠበቅንና
ሁሉንም ሂደቶች ማለፍ ስለሚያስፈልግ ነው፡፡
ወቅታዊነት ማለት ዛሬ የሆነን ክስተት ብቻ መዘገብ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግ እስከዛሬ
ድረስ ተደብቀው የተቀመጡ መረጃዎችን እንደተገኙ ማቅረብን ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ
የቀዳማዊ ኃይለስላሴ አሟሟት እስካሁን ድረስ ግልፅ የሆነ ነገር የለውም፡፡ ነገር ግን
ከገዳዮቹ አንዱ አሁን ሊሞት ሲል የነበረውን ሂደት ቢናዘዝና መረጃ ቢወጣ
ወቅታዊነትን አያዛባም፡፡ ከወቅታዊነት ጋር በተያያዘ ግን ቶሎ ብሎ ዜናን ለማቅረብ
ያልተጣሩ መረጃዎችን ይዞ መውጣትም ይሁን ያልጠራ ፅሁፍ መስራ ተገቢ አይደለም፡፡
4. ተፅዕኖ አድራጊነት (Impact)
ተፅዕኖ ማት አንድ ስለአንድ ድርጊት የሚያትት ዜና ለህብረተሰቡ በሚሰጠው ጥቅም
ያለው አንድምታ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ህብረተሰቡ ከዜናው በኋላ ድርጊቱን
በተመለከተ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ ዜናው
በሚያሳድረው ተፅዕኖ አማካኝነት ነው ክንውኖች የሚካሄዱት፡፡ ዜናዎች የሚታተሙት
ወይም የሚሰራጩት ሊፈጥሩት የሚችሉት ተፅዕኖ ወይም ሊሰጡት የሚችሉት ፋይዳ
ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ የብዙ ሰዎችን ህይወት የሚዳስስ ዜና በሰፊው ተፅዕኖ
መፍጠር ስለሚችል ይዘገባል፡፡ ብዙ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ባሳደረ ቁጥር ብዙ ጠቃሚ
እሴቶችን የያዘ ዜና ይሆናል፡፡
5. አወዛጋቢነት (Controvesy)
አንድ ጉዳይ የሥነ-ልቦና፣ የሥነ-ምግባር ወይም ግብረገብነት ላይ ውዝግብ ሊፈጥር
ይችላል፡፡ ውዝግቡ ደግሞ ከራስ ጋር፣ ከግለሰቦች ጋር ወይም ከቡድኖች ጋር ሊሆን
ይችላል፡፡ ይህን ውዝግብ ደግሞ ዜናው ታትሞ ከወጣ ወይም አየር ላይ ከዋለ በኋላም
የሚቀጥል ይሆና፡፡ በዚህም የተነሳ ዜናውን የተመረጠ ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም
አወዛጋቢ ጉዳዮች በህይወታችን የተወሰነ ፋይዳ ስላላቸው ነው፡፡
20
ለምሳሌ፡- ሞሮኮ የ2015 የአፍሪካን ዋንጫ አላዘጋጅም አለች፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢቦላ
ወረርሽኝ መስፋፋት ነው፡፡ በሌላ በኩል የአፍሪካ ዋንጫ ኮንፌዴሬሽን ውድድሩን
የማታዘጋጅ ከሆነ ከፍተኛ የሆነ ቅጣት እንደሚጣልባት አስታውቋል፡፡
በዚህ ዜና ውስጥ ሞሮኮ ትክክል ናት አይደለችም፤ ኮንፌዴሬሽኑ ቅጣት ሊከብድ ይገባል
ወይም አይገባም በሚል ለውይይት ይጋብዛል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካታ ሰዎች ከግለሰብ
እስከ ቡድን ደረጃ በሁለት ጎራ ተከፋፍለው ስለሁኔታው እንዲነጋገሩ መድረኩ
ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ለመነጋገሪያ እንዲሆን ስለሚያደርግ አወዛጋቢነት አንድ ጥሩ የዜና
እሴት ነው፡፡
6. ተገቢነት (Relevance)
ተገቢነት ለቅርበት የተሻለ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ ቅርበቱ ሲጠብ ዜናው በአንድ ሃገር
ውስጥ የተለያዩ ቡድኖች ፍላጎት ማሟላት ይሳነዋል፡፡ ለምሳሌ የምርት ማዳበሪያ ዋጋ
መውረድ ለአርሶ አደሮች ጥሩ ዜና ነው፤ ተገቢነትም አለው፡፡ ለብረታ ብረት ኢንዱስትሪ
ባለሃብቶች ግን ተገቢነት የለውም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የብረታ ብረት ዋጋ ጭማሬ
ለኢንዱስትሪው ባሃብቶች ተገቢ ሲሆን ለአርሶ አደሮች ግን ምንም አይደለም፡፡ ይህም
የሚያሳየው የዜናዎች ጠቃሚነት በቅርበትና በተገቢነት የተወሰነ መሆኑ ነው፡፡
7. ትንግርት (Uniqueness)
የተለመዱ ሁነቶች ዜና ሊሆኑ አይችሉም፡፡ አንድ ክስተት ዜና ሊሆን የሚችለው
ለተለመደው ወይም ሰዎች ከለመዱት ውጭ ያለ ነገር ይዞ መቅረብ ሲችል ነው፡፡ ይህም
ማለት ልዩ የሆነና ያልተለመደ መሆን አለበት፡፡ የትም ቦታ ላይ ተከስቶ የማያውቅ
ወይም አልፎ አልፎ የሚከሰት ወይ ብርቅ የሆነ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያም ዜና
የሰዎች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ሳይሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የተለየና
ስለ ተገቢነት ሲወራ ሁሌም መታወቅ ያለበት
የማህበረሰቡ የተለያየ ባህርይና ፍላጎት ነው፡፡ ስለዚህ
በአካባቢው የሚገኙ ተገቢ የሆኑ ማህበራዊ ፍላጎቶች
ቅድሚያ በዜናው ውስጥ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
21
ያልተለመደ ሲሆን የዜናውን እሴት በመጨመር የአድማጭ ተመልካችን ቀልብ መግዛት
ይችላል፡፡
ለምሳሌ፡-
1. አንዲት እናት ወንድ ልጅ በሠላም ተገላገለች፡፡
2. አንዲት እናት አራት ወንድ ልጆችን በሠላም ተገላገለች፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ዜናዎች የበለጠ የዜና እሴት ያለው ሁለተኛው ነው፡፡
ምክንያም የሰው ልጅ አይቀሬ የሆኑ ጉዳዮች ልደትና ሞት የተለመዱ ሲሆኑ በነዚህ
መካከል ግን ያልተለመዱ ሁኔታዎችን እንደ አራት ልጆች በሰላም መውለድ ዓይነት
ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ግን ዜና ይሆናል፡፡
8. ሰብዓዊነት (Human Interest)
ዜና የሰው ልጅ በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሌችም የህዝብ ጉዳዮች
የሚነካካ ከሆነ ጥሩ ዜና ነው ማለት ነው፡፡ ወደ ሰው ያዘነበለ የአፃፃፍ ስልት የሚጠቀም
ሲሆን ድርጊቶች ከሰው አኗኗር ጋር አያይዞ ይተነትናል፡፡ በዜናዎቹ ውስጥም የሰዎች
ቦታ ከፍተኛ ነው፡፡ ዜና አስደሳች እሴት የሚኖረው ከሁሉም እሴቶች ጋር የሰብዓዊ ነክ
ጉዳዮችን ይዞ መቅረብ ሲችል ነው፡፡
ለምሳሌ
1. በ 250 ሚሊዮን ብር የብረታ ብረት ፋብሪካ ተቋቋመ፡፡
2. ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችል ፋብሪካ ተቋቋመ፡፡
ከነዚህ ሁለት ዜናዎች የበለጠ ሰው ሰው የሚሸት ሁለተኛው ስለሆነ ከፍተኛ የሆነ
እሴት አለው፡፡ ምክንያቱም የፋብሪካው ካፒታል ሳይሆን በዚያ ካፒታል የተቋቋመው
ፋብሪካ ለማህበረሰቡ ምን ይፈይዳል የሚለው ስለሆነ ነው፡፡
22
9. ልብ ሰቀላ (Suspense)
የዜና የልብ ሰቀላ ተፈጥሮ የድርጊቱን ጠቃሚነት የተወሰነ በማሳየጥ አድማጭ
ተመነልካችን እያጓጉ እስከመጨረሻው ይዞ የመቆየት ተግባር ነው፡፡ ይህ ዓይነት አሰራር
አብዛኛውን ጊዜ የተዋዙ ዜናዎች ላይ ይበዛል፡፡ ይህ የዜና እሴት ከሌሎች እሴቶች ጋር
አብሮ የሚሄድ ሲሆን አድማጭን ስለአንድ ጉዳይ እርግጠኛ ሳይሆን እያዋዙና እያጓጉ
እስከዜናው ፍፃሜ ድረስ ይዞ መቆየት ነው፡፡
2.1.6 የዜና አላባውያን
አንድ ዜና ተወዳዳሪና ኃላፊነት የተሰማው ለማድረግ በተሻለ አቀራረብ መቅረብ አለበት፡፡
ይኸውም አድማጭ ተመልካች በሚፈልገውና በሚጠብቀው መልኩ ቢቀርብ በጣም
ተመራጭ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ዜና የሚሰራው ለይስሙላ ሳይሆን የያዝነውን መረጃ
በትክክለኛ መልኩ በመቅረብ ነው፡፡ ለአድማጭ ተመልካች ጥሩ ጣዕም ያለው ዜናን
ለማዳረስ መካተት ያለባቸው አስፈላጊ ንጥረ-ነገሮች ሊሟሉለት ይገባል፡፡ እነዚህ የዜና
ቀመሞች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. እውነትነት (Accuracy)
2. ሚዛናዊነት (Objectivity)
3. ምልዑነት (Completeness)
4. ግልፅነት (Clarity)
5. ምንጭን መለየትና መግለፅ (Source Identification and Attribution )
23
1. እውነትነት
በጋዜጠኝነት የዕለት ተዕለት ሥራ ውስጥ እውነትን የመሻት ፍላጎት አስፈላጊ ነው፡፡
እውነት መናገር ደግሞ ለጋዜጠኝነት ሥራም ሆነ ለዜና ጥንቅር አልፋና ኦሜጋ ነው
መርህ ነው፡፡ እውነትን መናገር ሁልጊዜ የዜና ተግባር መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን
እውነት ያልሆነ መረጃን ማስተላለፍ ከፍተኛ የሆነ ችግር ያጋጥማል፡፡ አንድ እውነትን
የገደፈ ዜና ከተሰራጨ የሚከተሉት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ፡፡
 ታማኝነትን ያሳጣል
 አድማጭ ተመልካችን ያሳጥል ወይም ምርጫቸውን እንዲቀይሩ ያደርጋል
 አላስፈላጊ የሆኑ ብዥታዎችን ይፈጥራል
ስለዚህ ከነዘህ እና መሰል ችግሮች መፈጠር በፊት ዜናውን የሚያዘጋጀው ጋዜጠኛ ጊዜ
ወስዶ ያሉትን መጃዎች ደግሞ ደጋግሞ ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም የጋዜጣ
ወይም የሬዲዮ ወይም ማንኛውም ዜና በተቻላቸው መጠን እውነት የሆነውን ነገር ነው
መዘገብ ያለባቸው፡፡ እውነትነት መጓደል ከሁለት በኩል ሊከሰት ይችላል፤ ከፀሐፊውና
ከመረጃ ምንጩ፡፡ በእውነት ላይ የተመሰረተ ዜና የማይሰሩ ጋዜጠኞች እንደመንስኤ
የሚቆጠረው ደግሞ ትኩረት ባለመስጠር (በእንዝህላልነት)፣ በስንፍና፣ ባልተሟላ
መረጃ፣ በተዛባ መረጃ እና በተባራሪ ወሬዎችና አሉባልታዎች ላይ ተመርኩዘው
መስራታቸው ነው፡፡ ነገር ግን መታየት ያለበት በነዚህና መሰል መንስኤዎ ምክንያት
እውነት ያልሆነ ነገር መዘገብ በጣም ከፍተኛ የሆነ ችግር መፍጠሩ ነው፡፡
እውነትነት
ሚዛናዊነት
ምልዑነት
ግልፅነት
ምንጭን
መለየትና
መግለፅ
24
2. ሚዛናዊነት
ጋዜጠኞች እንደማንኛውም ሰው ናቸው፡፡ ስለሆነም ሙሉ በሙሉ ከአንድ ጉዳይ ፍፁም
ነፃ እና የተገለሉ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ሚዛናዊ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም
የመሆኑ ጉዳይ ጋዜጠኛው ሥራውን ሲሰራ ከራሱ የግል ስሜትና ጥቅም ተነሳስቶ
ለራሱ በሚመቸው መልኩ መስራት ሳይሆን ጉዳዩን ከተለያየ አቅጣጫ መመልከት
ይገባዋ፡፡ ብዙውን ጊዜ አንድን ጉዳይ ከተለያየ አቅጣጫ መመልከት ተገቢም አዋጭም
ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙ ሪፖርተሮች አንድን የፍርድ ቤት የችሎት ውሎ እንዲዘግቡ ቢላኩ
ይዘውት የሚመለሱት መረጃ ሁሉም ተመሳሳይ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህም ማለት
አንዳንዱ በምስክሮች ላይ ያተኩራል፣ ሌላው በተከሳሽ፣ ሌላው በከሳሽ፣ ሌሎች ደግሞ
በአቃቢ ህጉ፣የተወሰኑት ደግሞ በጠበቃውና በዳኛው ላይ ያተኮረ ዜና ይዘው ይመጣሉ፡፡
ስለዚህ የውስንነት ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ ሚዛናዊ ለማድረግ መሞከር ተገቢ ነው፡፡
ጥሩ ልምድ ያካበቱ ሪፖርተሮች ከግል እይታቸው እና እምነታቸው ውጭ ዜና
ይፅፋሉ፡፡ ይህም ሚዛናዊ ሆነው እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ጋዜጠኞች ፍትሃዊና ሚዛናዊ
በሆነ መል ዜናን ካልሰሩ እውነትን ማዛባታቸው አይቀርም፡፡ እውነት ሲዛባ ደግሞ
የአድማጭ ተመልካች እምነትን ማጥት ያስከትላል፡፡ ሰው መሆን በራሱ ራሳችንን ዜና
ውስጥ ጨምረን እንድናስብ ቢያደርገንም እንኳ እንደጋዜጠኛ ግን ዜና በሚሰበሰብበት
ጊዜ ነፃና ሚዛናዊ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ ሚዛናዊነት ከምንሰራው ሥራ ጋር
በተያያዘ በሂደቶች ውስጥ የምናደርገው መንገድ እንጂ ዉጤቱ ላይ አይደለም፡፡
ለምሳሌ፡- መንግስትና ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እየጨቆኑ
መሆኑን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታወቁ፡፡
በዚህ ዜና ውስጥ ከመንግስት፣ ከምርጫ ቦርድ እና ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር
በምናደርጋቸው ቆይታዎች በተመሳሳይና ሚዛናዊ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ነገር ግን
ጋዜጠኛው የመንግስት ደጋፊ ወይም በመንግስት የሚዲያ ተቋም ውስጥ የሚሰራ
ስለሆነ ብቻ የተቃዋሚዎችን ጉዳይ ከፀረ-ሠላም አካላት ወይም ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር
አያይዞ መናገር ከጋዜጠኛ የማይጠበቅ ነው፡፡
25
3. ምልዑነት
ዜና ከተለያየ አቅጣጫ ያሉትን ጉዳዮች በመያዝ ምልዑ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በጋዜጣና በመፅሔቶች ላይ ለሚወጣ ዜና ነገሮችን ከብዙ አቅጣጫ
በማየት ማቅረብ ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የጋዜጣውና የመፅሔቱ የህትመት ቀን
እስኪደርስ ብዙ የማጣራት ተግባራት ማከናወን ስለሚቻል ነው፡፡ ይኸውም የሌሎች
የህትመት ውጤቶችን፣ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዘገባዎችንና ትንታኔዎችን፣ በኢንተርኔት
ለላይ የሚለቀቁ መረጃዎችን በማየትና የመረጃ ምንጮችን በማነጋገር የተጠናከረ ምልዑ
ሥራ ይዘው መውጣት ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል በብሮድካስት ሚዲያ ሁሌም አወዛጋቢ
በሆኑ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ነገሮችን አሟልቶ መቅረብ ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም
ብሮድካስት ሚዲያ በዋናነት ከጊዜ ጋር ስለሚሰራ ነው፡፡ ሚዛናዊነትና እይታ በጣም
አስፈላጊ ስለሆኑ በዜና ውስጥ ከተካተቱ ዜናው ምልዑ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን
ሁሌም ከሰዓት ጋር በተያያዘ ጉዳይ ግፊት ስላለ ፍጥነትና ቅልጥፍና ይፈልጋል፡፡ አንድ
ዜና ምልዑ የሚሆነው እውነትና ሚዛናው ሲሆን ነው፡፡ ይህም ተግባራዊ የሚሆነው
የጉዳዩን ባለቤቶች ከተለያየ ጎን ይዞ መቅረብ ሲቻል ነው፡፡
4. ግልፅነት
ዜና መዘገብ ያለበት አጭርና ግልፅ በሆነ መልኩ ነው፡፡ በተለይም ለብሮድካስት ሚዲያ
መዘገብ ያለበት አንድ ጊዜ ተሰምቶ በቀላሉ ለአድማጭ ተመልካች በሚገባበት መልኩ
መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የብሮድካስት አድማጭ ተመልካቾች እንደገና ደግመው
የመስማት ዕድል የላቸውም ወይም ያልገባቸውን ነገር ከተለያዩ ነገሮች ላይ ለማጣቀስም
ሆነ ለማሰብ ጊዜ ስለሚያስፈልጋቸው ያንን ሲያደርጉ ሌሎች ዜናዎች ስለሚያልፉ ነው፡፡
ስለዚህ ዜናው ግልፅና በቀላሉ ለአድማጭ ተመልካች የሚገባ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
ለዚህ ደግሞ የዜናው ፀሐፊዎች የሚመርጧቸው ቃላትና የዓረፍተ ነገር አወቃቀራቸው
ቀላልና ያልተንዛዛ መሆን አለበት፡፡ ይህም የአድማጭ ተመልካችን ሥራ ከማቅለሉ በላይ
ዜናውን ተደማጭ ያደርገዋል፡፡
26
5. ምንጭን መለየትና መግለፅ
ዜና በሚሰራበት ጊዜ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን እንጠቀማለን፡፡ እነዚህን የመረጃ
ምንጭ ግን እየለዩ መጠቀም ከጥሩ ዜና የሚገኝ አላባ ነው፡፡ ስለዚህ የዜና ምንጮችን
በግልፅና በአግባቡ መጠቀም ከጥሩ ዜና ይጠበቃል፡፡ የመረጃ ምንጭን በተመለከተ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይጠበቃል፡፡
 ትክክለኛው የመረጃ ምንጭ ማን ነው?
 የመረጃ ምንጩ ታማኝ ነውን?
 የትኛው የመረጃ ምንጭ የበለጠ ታማኝ ነው?
እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን ከመለስን የመረጃ ምንጫችንን ለየን ማለት ነው፡፡ ከዚያ
ቀጥሎ እንዴት እንጠቀምበት የሚለው ጥያቄ መመለስ ነው፡፡
የመረጃ ምንጭ ሰዎች፣ ተቋማት ወይም የተለያዩ ሰነዶችና ዶሴዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ስለዚህ እውነትና ውሸቱን ለይተን ካየን በኋላ በምን መልኩ ልግለፃቸው (attribution)
የሚለው ወሳኝ ነው፡፡ ለመረጃ ምንጮች መጠቀስም ሆነ ክብር መስጠት ተገቢ የጥሩ
ዜና ጥንቅር አካል ነው፡፡ የመረጃ ምንጭን በአግባቡ መለየትና መጥቀስ የራሱ የሆነ
ጥቅሞች አሉት፡፡ ከነዚህ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
 የዜናውን ታማኝነት ይጨምራል
 የዜናውን ግልፅነት ያሳድጋል
 የጋዜጠኞችን የህግ ጥያቄዎች ይከላከላል፡፡ ይህም ማለት የመረጃ ምንጩ
ከተጠቀሰ ጉዳዩ የሚሆነው የምንጩ እንጂ የጋዜጠኛው አይደለም፡፡
የመረጃ ምንጮችን በምንጠቀምበት ጊዜ በብሮድካስትና በህትመት ዜና ጊዜ የአጠቃቀም
ልዩነት አለው፡፡ ይኸውም በህትመት ዜናዎች እንደፈለግን በሰጡት መረጃ ፊት፣
መሃል፣ መጨረሻ ወይም እየተቀላቀለ መጠቀም ሲቻል በብሮድካስት ዜናዎች ግን
ሁልጊዜም ከመረጃው በፊት መቀመጥ አለበት፡፡ ምክንያም ደግሞ ዜናው የሚፃፈው
በንግግር መልኩ ስለሆነ ነው፡፡
27
2.2 የዜና ምንጮች
2.2.1 ዜና ከየት ይገኛል?
የመረጃ ምንጭ ማለት ማንኛውም ግለሰብ፣ ድርጅት፣ ተቋም ወይም ቡድን በትክክል
የተዋቀረ መረጃ ማቅረብ ወይም መስጠት የሚችል ነው፡፡ እነዚህ የመረጃ ምንጮች
ከጋዜጠኛው ጋር በሚኖራቸው ጊዜ ስለድርጅታቸው ወይም ስለራሳቸው ትክክለኛ መረጃ
የመስጠት አቅም ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በተመሳሳይ ሪፖርተሩም የመረጃ ምንጮችን
አያያዝ በተመለከተ አግባብነት ያለው አካሄድ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህም ማለት በመረጃ
ምንጩና በጋዜጠኛው መካከል መልካም ግንኙነት ሊመሰረት ይገባል፡፡ ምክንያቱም
ያለመረጃ ምንጮች የጋዜጠኛነትን የዕለት ከዕለት የሥራ እንቅስቃሴ የተሟላ ማድረግ
ስለማይቻል ነው፡፡
በምዕራፍ አንድ የጋዜጠኝነት ትርጉም ላይ “መረጃን የሚሰበስብ፤ የሚያዘጋጅ፤ እና
የሚያሰራጭ ባለሙያ በማለት ጋዜጠኝነትን መተርጎማችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም
የመረጃ ምንጮቻችን በአግባቡ ካልተያዙና ግንኙነቱ መልካም ካልሆነ ጋዜጠኛው
የሚያሰባስበውም፣ የሚያዘጋጀውም ሆነ የሚያሰራቸው መረጃ አይኖርም ማለት ነው፡፡
ይህ ደግሞ የጋዜጠኝነትን ሥራ ያቆመዋል ማለት ነው፡፡
መረጃ ለጋዜጠንነት ሥራ በተለይም ለዜና ሥራ ደም ነው፡፡ ጋዜጠንነት አንድ የተገነባ
ሰው አድርገን ብንወስደው ዜናን ደግሞ እንደልብ ብንቆጥር መረጃው ደግሞ ደም ቢሆን
ጋዜጠኝነት በህይወት እንዲኖር ዜና መንቀሳቀስ አለበት፤ ዜና ደግሞ ብቻውን
መንቀሳቀስ ስለማይችል የግድ የሚያሰራጨው መረጃ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ የመረጃ
ምንጮቻችን ተዘጉ ማለት ለጋዜጠኝነት የሚቀርብ መረጃ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡
የተጀመረው መልካም ግንኙነት ደግሞ ሁሌም መቀጠል አለበት፡፡ መቀጠል ብቻ ሳይሆን
የመወያያ ጥያቄ
1. የመረጃ ምንጭ ምንድነው?
2. የመረጃ ምንጭ ከሪፖርተሮች ጋር ያለው ግንኙነት
እንዴት መሆን ይጠበቅበታል?
28
ተጠንክሮ መቀጠልም ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ በጋዜጠኛውና በመረጃ ምንጩ መካከል
ያለውን ግንኙነት ለማሳደግ የሚከተሉት ተግባራት መከናወን ይገባቸዋል፡፡
ሀ. የተጀመረውን ግንኙነት ማጠናከር
ለ. የመረጃ ምንጮቻችን ምስጢር መጠበቅ
ሐ. ግላዊና ተቋማዊ ክብርንና ታማኝነት ማጠናከር
መ. ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸውን መረጃዎች ማረጋገጥ፣ መመዘንና መጠቀም
ሠ. ከምንጮች ጋር አብሮ የመስራት ችሎታን ማዳበር
ረ. ሁኔታዎች በፈቀዱት መጠን ጓደኛነት መመስረትና ማጠናከር
ከላይ በተዘረዘሩት ነገሮች ጋዜጠኞች የመረጃ ምንጭ መረባቸውን ማስፋፋት ይችላሉ፡፡
ሪፖርተሮች የአንድ የብዚሃን መገናኛ አምባሳደር መሆን አለባቸው ምክንያቱም እነሱ
የሚወክሉትን ኃላፊነት ወስደው የሚንቀሳቀሱት የተቋማቸውን ህልውና ነው፡፡
ሪፖርተሮች ከመረጃ ምንጮቻቸው ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ምክንያት የብዙሃን
መገናናው ህልውና ሊቋረት ወይም ሊቀጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኞች
እንደአምባሳደርነታቸው ጤናማ የሆነ ግንኙነት የመመስረት፣ የማሳደግና የማጠናከር
ኃላፊነት አለባቸው፡፡
2.2.2 የዜና ምንጮች
ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ዜና ከተለያዩ ምንጮች ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል
የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
ሀ. የሚዲያ ተቋሙ ሪፖርተሮች፡- ተቋማት በየቦታው የሚልኳቸውና የሚመድቧቸው
ትርፍ ጊዜ ወይም የሙሉ ሰዓት ጋዜጠኞች መረጃን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ይኸውም
የተመለከቱትን ነገር እንደዜና ምንጭ በመሆን መረጃን ለብዙሃን መገናኛ ተቋማት
ያቀብላሉ፡፡
ለ. አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የዜና ማዕከላት አገልግሎቶች፡- ጋዜጦችና የብሮድካስት
ተቋማት ዜናን ከተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ወይም የሃገር ውስጥ የዜና ማዕከል ሊያገኙ
ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሃገር
ውስጥ ዜናዎችን ከሃገር ውስጥ የዜና ማዕከላት ያገኛሉ፡፡ እነዚህም የዜና
29
ማዕከላትም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)በ እና ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል
(ዋልታ) ናቸው፡፡ የውች ሃገር ዜናዎችን ደግሞ የቻይናው ሽንዋ፣ አጃንስ ፋራንስ
ፕሬስ፣ ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርንሽናል፣ ፓን አፍሪካን ኒውስ ኤጀንሲ (ፓና)፣
ሮይተርስ፣ ወዘተ የሚጠቀሱ ዋና ዋና የዜና ምንጮች ናቸው፡፡
ሐ. ኔትወርኮች፡- ይህ በኢትዮጵያ የተለመደ ባይሆንም በበለፀጉ ሃገሮች ብዙ
የብሮድካስት አገልግሎቶች መረጃን ከሚከፋፍሏባቸው ተቋማት በገመድ ወይም
በካርድ አማካንነት አማካኝነት መረጃን የመውሰድ ሁኔታ ነው፡፡ ከዚህም በጠጨማሪ
በኢንተርኮም (የውስጥ መስመር) አማካኝነት መረጃን ያገኛሉ፡፡
መ. ነፃ ጋዜጠኞች (freelancers)፡- እነዚህ ጋዜጠኞች ግለሰቦች ወይም በቡድን
ተደራጅተው ለዜና የሚሆኑ መረጃዎችን እየሰበሰቡ ዜና በመፃፍ በውል ለብዙሃን
መገናኛ ተቋማት የሚያሰራጩ ናቸው፡፡ ለሬዲዮ በፅሁፍና በድምፅ ሲቀርቡ
ለቴሊቪዥን ደግሞ ምስሉን ጨምረው ያቀርባሉ፡፡
ሠ. ከመስሪያ ቤት የሚወጡ ዜናዎች (furnished news)፡- እነዚህ ዜናዎች የሚወጡት
ከመስሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶች፣ ሲሆን በህዝብ ግንኙነቱ አማካንነት ይሰጣሉ፡፡
የሚዲያ ጥቆማና የፅሁፍ ስርጭት (ፕሬስ ሪሊዝ) የሚያካትት ነው፡፡ ይህ
በአብዛኛው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ለደንበኞቻቸውና ለባለድርሻ አካላት
የሚያሰራጩት የዜና ምንጭ ይሆናል፡፡
ረ. ኩነቶች፡- በየጊዜው የሚከሰቱና የሚካዱሄዱ ኩነቶች ለዜና ምንጭነተር ያገለግላሉ፡፡
የሚስቡና ያልተለመዱ ሲሆኑ ደግሞ የበለጠ የብዙሃን መገናኛን ቀልብ ይስባሉ፡፡
ለምሳሌ ጋዜጣዊ መግለጫ ጉባኤ፣ ምርቃት፣ ህዝባዊና ብሄራዊ በዓላት፣ አደጋዎችና
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆችወዘተ እንደኩነትነታቸው የመረጃነ ምንጭ ሆነው
ያገለግላሉ፡፡
ሰ. ህዝባዊ ትዕይንቶች፡- በርካታ ህዝብ የሚሳተፍባቸው ህዝባዊ ትዕይንቶች የዜና
ምንጭ ይሆናሉ፡፡ ሰላማዊ ሰልፎች፣ የተቃውሞ ሰልፎች፣ የድጋፍ ሰልፎች፣
ዘመቻዎች፣ ቅስቀሳዎች ዋና ዋና የህዝባዊ ትዕይት ዘርፍ ሲሆኑ የዜና
ምንችነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡
30
2.2.3 የዜና ምንጮች አያያዝ
መረጃ ምንጮችን በተገቢው መንገድ መያዝ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የመረጃ መ፣ንጮች
ስማቸው እንዳታወቅ የሚፈልጉ፣ ማንነታቸው እንዳይታወቅ የሚፈልጉ ወይም ደግሞ
ስማቸውንና ማንነታቸው በሚስጢር እንዲያዝላቸው የሚፈልጉ፣ ድምፃቸውና ምስላቸው
እንዳይቀረፅ የሚከለክሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን የመረጃ ምንጮች እንዴት መጠቀም
እንዳለበት የሚያውቅ ጋዜጠኛ ደግሞ በሥራው ከፍተኛ ትርፍ ያገኛል፡፡
መረጃ መስጠት የማይፈልጉ (reluctant) ምንጮች
ሰዎች መረጃ ከመስጠት ለምን ወደኋላ ይላሉ? ብዙውን ጊዜ ሰዎች መረጃዎችን
የማይሰጡት በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡
 በአለቆቻቸው በኩል የሚደርስባቸውን እርምጃና ከሥራ መፈናቀል በመፍራት
 ከህዝብ ግንኙነት ዌም ከቃል አቀባዩ መረጃውን እንዲሰሙ ስለሚፈልጉ
 ከዚህ ቀደም በሌላ ጋዜጠኛ በሥርዓት ሳስተናገዱ በመቅረታቸው ምክንያት
ላለመተባበር በመወሰናቸው
 የሚሰጡት አስተያየት ዌም መረጃ ጠቃሚ መስሎ ስለማይታያቸው
እነዚህን ምክንያቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት ጋዜጠኛው ለመፍታት የተለያዩ
ስትራቴጂዎችን ይመቀማሉ፡፡ ከነዚህ ስትራቴጂዎች መካከልም የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
 መረጃ በመስጠታቸው ምክንያት ምንም ዓይነት ችግር እንደማይደርስባቸው
የማሳመን ሥራ መስራት
 ጥያቄውን ከሚመለከተው አካል እንደጠየቁ በመንገር የተገኘውን መረጃ
ለማረጋገጥ ብቻ እንደምናናግራቸው በመንገር ማሳመን
 መረጃ እያላቸው መረጃ መስጠት የማይፈልጉ ሰዎች
ቢኖሩ ምን ታደርጋላችሁ?
 መረጃውን ሰጥተው ማንነታቸው እንዳይገለፅ
የሚፈልጉትንስ?
31
 ከአሁን በፊት ስላስቀየማቸው ጋዜጠኛ ይቅርታ በመጠየቅ የራስን ስብዕና
ማስረዳት
 ምንጮች የነሱ መረጃ ጠቃሚ መስሎ ካልታያቸው በጣም ጠቃሚ የሆነ መረጃ
እንሱ ጋ እንደሚገኝ ሌለ፤ ሰው ላይ ያንን መረጃ ማግኘት እንደማይቻል
በማሳመነን መረጃ እንዲሰጡ ማድረግ
ማንነታቸው እንዳታወቅ ወይም በሚስጥር እንዲያዝላቸው የሚፈልጉ
(Anonymity & Confidentiality) ምንጮች
አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ማንነታቸው እንዳታወቅ ወይም በምስጥር እንዲያዝላቸው
በመረጃ መስጠት ሂደቱ መጀመሪያ፣ መሃል ላይ ወይም መጨረሻ ላይ ሊጠይቁ
ይችላሉ፡፡ ይኸውም መረጃውን ሲሰጡ የነሱን ማንነት እንዳይገለፅ ሲፈልጉ ጋዜጠኛው
ቃል እንዲገባ ያደርጋሉ ወይም ይጠይቃሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚሰጡትን መረጃ በጣም
ጠቃሚ ስለሚሆን በስማቸውና ማንነታቸው አለመገለፅ ላይ ከጋዜጠኛው ጋር
መስማማት አለባቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ዓይነት የዜና ምንጮችን ለመጠቀም እንዴት
መያዝ አለባቸው ለሚለው የሚከተሉት መንገዶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
1. ለሚጠይቁት ጥያቄ ውል በመስጠትና ቃል በመግባት ማረጋገጥ
2. እዲቀረፁ በማግባባት አስተያየታቸውን ለመጠቀም ማሳመን
3. በመቃወም እነሱን ትቶ በመሄድ ሌለላ የሚቀረፅ ሰው ፈልጎ በመቅረፅ መጠቀም
እነዚህን አማራጮች በምንወስድበት ጊዜ የሃገሪቱን ህግና አዋጆች ከግምት ውስጥ ያስገባ
መሆን ይጠበቅበታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን የተለያዩ ሃረጎችን በመጠቀም ስማቸው
እንዳይጠቀስ የፈለጉትን የመረጃ ምንጮች እንደአማራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ለምሳሌ፡-
 ለከንቲባ ቅርብ የሆነ ምንጭ እንደተናገረው…….
 ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ አንድ የቢሮው ሠራተኛ እንደገለፁት…
 አንድ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካል እንዳሉት…..
ብዙውን ጊዜ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምንጮችም ቢኖሩ መረጃው በመቅርፀ-
ድምፅ እንዳይቀረፅ የሚፈልጉት ግን በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ መረጃ እንዳይቀረፅ
የሚፈልጉትን ምንጮች በዜና ውስጥ በቀጥታ ጥቅስ ሳናስገባ በፅሁፉ ውስጥ ፍትሃዊ
በሆነ መልኩ ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡ ጋዜጠኛው ስማቸውንና ማንነታቸውን
32
ላለመግለፅ ከተስማማ ደግሞ ስምምነቱን ማክበር ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያቱም ቃላችንን
ካላከበርነ ሌላ ጊዜ በፍፁም መረጃ ማግኘት ላይቻል ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ጋዜጠኝነት
የአንድ ቀን ሥራ ስላልሆነ የጋዜጠኝነት ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳዋል፡፡
2.2.4 መረጃ እንዴት ይገኛል?
 መረጃ እንዴት ይገኛል?
 በየትኛው መንገድ የተገኘ መረጃ ነው ለሚዲያ ፍጆታ
የሚውለው?
መረጃን በተለያየ መንገድ እናገኛለን፡፡ ለዜና ግብዓት የሚሆነንን መረጃ ደግሞ
የምንፈልገው ሠላማዊ በሆነ መንገድ ነው፡፡ አስገድዶ እየደበደቡ መረጃን ማግኘት
የጋዜጠኝነት ሥራ አይደለም፡፡ ስለዚህ የጋዜጠኛ ሁነቶችን፣ ሁኔታዎችን፣ ዝግጅቶችን
በመመልከት ቃለመጠይቅ በማድረግ እና የራሱ የሆነ ጥናትና ምርምር በአንድ ጉዳይ
ላይ በማድረግ መረጃን ይሰበስባል፡፡ እነዚህ መንገዶች በውስጣቸው የተለያዩ ቴክኒኮች
አሏቸው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ እያንዳዳቸውን አንድ በአንድ እንመለከታለን፡፡
ሀ. ምልከታ
በአንድ ጉዳይ ላይ የተሻለ ሽፋን ለመስጠት ተመራጩ መንገድ ቦታው ድረስ በመሄድ
መመልከት (Observation) ነው፡፡ ምልከታ በጋዜጠኝነት ሥራ ውስጥ የዕለት ተዕለት
ተግባር መሆን ያለበት የመረጃ መሰብሰቢያ መንገድ ነው፡፡ ጋዜጠኛው በቦታው ተገኝቶ
ሁኔታዎችን መመልከት ካልቻለ የአንድ ዜና ጥንቅር ምልዑነት አስተማማኝ አይሆንም፡፡
ምክንያቱም ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት በሌሎች መንገዶች የሚሰበሰቡትን ጉዳዮች
በዓይን ተመልክቶ የማረጋገጥ ወይም ደግሞ ውድቅ የማድረግ ሥራዎችን ለማድረግ
ተጨማሪ ኃይል ስለሚሰጥ ነው፡፡
“ማየት ማመን ነው” እንደሚባለው በዜና አሰባስባችን ውስጥ ቦታው ድረስ በመሄድ
መመልከት የራሱ የሆነ ጥቅምና ጉዳት አለው፡፡ አንድን ጉዳይ ቦታው ድረስ ሄዶ
መመልከት የሚያስገኛቸው ጥቅሞች፡-
 ሁኔታዎችን በቀላሉ ለመረዳት
 ጉዳዩን በቅርበት የበለጠ ለማረጋገጥ
33
 ከሚታየው ነገር ባሻገር ስላለው እውነት ለማወቅ
 ሠው በንግግር ሊገልፃቸው የማይችሉ ጉዳዮችን ለማግኘት ዕድል ይሰጣል
 ከባለጉዳዮች ጋር ቅርርብ መፍጠር ስለሚችል… ወዘተ
በሌላ በኩል አንድን ጉዳይ ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት ያሉት ጉዳቶች፡
 ከፍተኛ የሆነ ወጪ ይጠይቃል (የማቴሪያል፣ የገንዘብና የጉልበት ወጪ)
 ጊዜ ይፈጃል
 ወደ ቦታው ለመግባት አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መጋፈጥ ይጠይቃል
 ከጉዳዩ ባለቤቶች የሚደርሱ ክልከላዎችና ማስፈራሪያዎች ወዘተ ይገኙበታል፡፡
ምንም እንኳ አንድን ጉዳይ ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት የራሱ የሆነ ጥቅሞችና
ጉዳቶች ቢኖሩትም ስለጉዳዩ ምልዑ የሆነ መረጃ ለመሰብሰብ መድረክ ስለሚከፍት
ተመራጭ መንገድ ያደርገዋል፡፡
ለምሳሌ፡- በቦረና አካባቢ 4.5 ሚሊዮን ህዝቦች ተርበዋል የሚል ወሬ ሰምታችሁ የመረጃ
ምንጫችሁ ምናልባትም የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡትን መግልጫ ጉባኤ ከአዲስ
አበባ ብትከታተሉ ወይም ከቦረና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሚልከውን
ጋዜጣዊ መግለጫ ፅሁፍ እንደምንጭ ብትጠቀሙ ምናልባት የጉዳዩን ሁለትከመቶ
እንኳን በሚገባ መረዳት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የጉዳዩን አስከፊነት ሠዎች
ከሚነግሯችሁ በላይ ቦታው ድረስ ሂዳችሁ ብትመለከቱ የበለጠ መረዳት ስለምትችሉ
ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ አስር ሰዎች ሞተዋል ሲባል መስማትና አስር ሰዎች
በረሃብ አለንጋ ተገርፈው ቆዳቸው ከአጥንታቸው ተጣብቆ ሲሞቱ ማየት ለጋዜጠኛ
የበለጠ ትርጉም የሚሰጠው የትኛው እንደሆነ የታወቅ ነው፡፡
የምልከታ ዓይነቶች
መረጃን ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት ከድርጊቱ ድግግሞሽና ሂደት አንጻር በሁለት
ይከፈላል፡፡ እነሱም በተለያዩ ክፍሎች የአንድ ጊዜ ምልከታ (Episodic Observation)
እና ሥርዓታዊ ምልከታ (Systematic Observation) ተብለው ነው፡፡ የአንድ ጊዜ
ምልከታ የሚደረገው በተከታታይ በተጠናና በተደራጀ መደበኛ በሆነ መልኩ ሳይሆን
በኢ-መደበኛ ድንገት ቦታው ላይ በመገኘት የሚከናወን ነው፡፡ ሥርዓታዊ ምልከታ ደግሞ
34
መደበኛ በሆነ መልኩና በተደራጀ አካሄድ የሚደረግ ነው፡፡ እነዚህን የምልከታ ዓይነቶች
በውስጣቸው የተለያዩ የምልከታ ዓይነቶች ይዘዋል፡፡
የአንድ ጊዜ ምልከታ
የአንድ ጊዜ ምልከታ በራሱ ሶስት የተለያዩ የምልከታ ዓይነቶችን አካቷል፡፡ እነሱም
ሀ. ልማዳዊ ምልከታ (Conventional Observation)
ለ. ድብቅ ምልከታ (Unobtrusive Observation)
ሐ. አሳታፊ ምልከታ (Participant Observation)
እነዚህ ሶስቱ የምልከታ ዓይነቶች አንድ ድርጊት ሲፈጸም ወይም ክስተት ሲከሰት ቦታው
ላይ በመገኘት የሚከናወኑ የምልከታ ዓይነቶች ናቸው፡፡
ሀ. ልማዳዊ ምልከታ
ልማዳዊ ምልከታ አሳታፊ ያልሆነ የምልከታ ዓይነት ሲሆን የማህበራዊ
እንቅስቃሴዎችን ለማጥናት ወይም አሳታፊ ባልሆነ መልኩ መረጃን ለመሰብሰብ
ያገለግላል፡፡ የህብረተሰብ ሳይንስ ባለሙያዎች የሰዎችን ባህርይ ለማጥናት ይህንን
የምልከታ ዓይነት ይጠቀማሉ፡፡ ጋዜጠኞችም የህብረተሰብ ሳይንስ አካል እንደመሆናቸው
የሰውን ባህርይ ለማጥናት ልማዳዊ በሆነ፤ ራሳቸውን የድርጊቱ አካል ሳያደርጉ
ይጠቀሙበታል፡፡ ልማዳዊ ምልከታ ስብሰባዎችን በምንከታተልበት፣ ንግግሮችን
ስናዳምጥ፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ስንመለከት፣ ኮንሰርቶችን ስንታደም፣ የጋዜጣዊ
መግለጫ ጉባኤዎችን፣ የምርቃት መርሃ-ግብሮችን፣ ዓመታዊ በዓላትን ወዘተ
በምንመለከትበት ወቅት የምንጠቀምበት የምልከታ ዓይነት ነው፡፡ ልማዳዊ ምልከታ
ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው የመረጃ ምንጮች የጋዜጠኛውን መኖር እያወቁ ነው፡፡
ይኸውም የመረጃ ምንጮች በጋዜጠኛ እይታ ውስጥ እንደሆኑ እያወቁ ነው
የሚካሄደው፡፡
የልማዳዊ ምልከታ ጠንካራ ጎኖች፡-
 ጋዜጠኛው ሥነ-ምግባር ጠብቆ የሰዎችን ግለኝነት መብት ሳይነካ እንዲሰራ
ያደርጋል፡፡
35
 የመረጃ ምንጩ ጋዜጠኛው እንዲያይለት የሚፈልገውን ነገር በሙሉ ለማሳየት
ይጥራል፣ ይኸውም የመረጃ አድማሱን ያሰፋዋል፡፡
 ጋዜጠኛው ራሱን የጉዳዩ አካል ስለማያደርግ በተቻለ መጠን ነፃና ሚዛናዊ ሆኖ
እንዲሰራ ይጠቅማል፡፡
 ጋዜጠኛው የጋዜጠኛ የሥራ መሳሪያዎችን (ካሜራ፣ መቅርፀ- ድምፅ፣ ማስታወሻና
ሌሎችንም) እንዲጠቀም ይረዳዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ልማዳዊ ምልከታ የራሱ የሆነ ድክመቶች አሉት፡፡ ልማዳዊ ምልከታ
በአንድ የተወሰነ ጊዜ ውስጥ ውስን የሆነን እንቅስቃሴ ለማየት የሚደረግ ስለሚሆን
በዋናነት በዛች ሰዓትም የመረጃ ምንጩ የጋዜጠኛውን መኖር እያወቀ በመካሄዱ
ምክንያት የተለያዩ ድክመቶች አሉት፡፡ የጋዜጠኛውን መኖር ስለሚያውቁ ትክክለኛ
ሥራቸውንና ሰብዕናቸውን እንዲደብቁ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ጋዜጠኛው የመረጃ
ምንጩ በወቅቱ በሚያሳየው ነገር ላይ እንዲወሰን ያደርገዋል፡፡
ለምሳሌ፡- የአባይ ግድብን ለመመልከትና ስለግድቡ መረጃ እንዲኖረን የሥራ ኃላፊዎችን
ማግኘት ስላለብን የምናገኘው በልማዳዊ ምልከታ ነው፡፡
ለ. ድብቅ ምልከታ
ድብቅ ምልከታ እንደልማዳዊው ምልከታ በአንድ የተወሰነ ቦታ ተገኝቶ አንድን ጉዳይ
ለተወሰነ ጊዜ መመልከት ሲሆን ብዙውን ጊዜ ሪፖርተሮች አንድ አዲስ ነገር ከተከሰተ
ብቻ የሚያደርጉት ነው፡፡ በልማዳዊው ምልከታ የሪፖርተሩን መኖር በመረጃ ምንጮች
የታወቀ ስለሚሆን ምንጮቹ ከመደበኛው ባህርያቸው ውጭ የሆነ ተግባርና እንቅስቀቃሴ
ስለሚያሳዩ ትክክለኛ ማንነታቸውን ማወቅ ስለማይቻል የድብቅ ምልከታ ይከናወናል፡፡
የድብቅ ምልከታ በዋናነት የመረጃ ምንጩ ሳያውቅ በድብቅ በመግባት መረጃ ሰብስቦ
የመውጣት ሂደት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- አንድ ህፃናትን በጉዲፈቻ አሳድጋለሁ የሚል ሰው ሴት ህፃናትን
ወደቤቱ እያስገባ የመድፈር ሥራ ቢያደርግ ሰውየውን በልማዳዊ መንገድ
ለመከታተል ቢሞከር ልጆቹን ሲደፍርም ሆነ ሲያሰቃያቸው ማየት አይቻልም፡፡
ሰውየው በተቻለ መጠን ልጆቹን በአባትነት ስሜት ሲንከባከባቸው ነው
የሚታየው፡፡ ስለዚህ በቤት ሠራተኛ ወይንም የጥበቃ ሠራተኛ አማካኝነትና
36
እርዳታ ተደብቆ በመግባት መመልከት ይገባል፡፡ ስለዚህ የሰዎችን ድብቅ ማንነት
በድብቅ በማየት የህፃናቱን መደፈር መረጃ መሰብሰብ ይቻላል፡፡
የድብቅ ምልከታ የራሱ የሆነ ጥቅምም ተግዳሮትም አሉት፡፡ ጥቅሞችን በምናይበት ጊዜ
በልማዳዊ ምልከታ ማግኘት የማንችለውን መረጃ ማግኘት ያስችላል፡፡ ስውር ሴራዎችንና
የተደበቁ ወንጀሎችን ለማጋለጥ ይረዳል፡፡ በሌላ በኩል ግን የመረጃ መሰብሰቢያ የሆኑ
ቁሳቁሶችን (የቪዲዮ ካሜራ፣ የፎቶግራፍ ካሜራ፣ ማይክራፎን፣ መብራት፣ መቅርፀ-
ድምፅ፣ ማስታወሻ ወዘተ) መያዝ አስቸጋሪ ተግዳሮት ነው፡፡ ይህም የምንመለከተው
ሰው እንዳያውቅ ከሚደረገው እንቅስቃሴ ጋር ጋዜጠኛው መደበቅ ስላለበት በስውር
ስለሚገባና ስለሚወጣ እነዚህን ነገሮች መጠቀም አያስችልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
የመረጃ ምንጭን የግለኝነት መብት በመጣስ የጋዜጠኝነት ህግና ሥነ-ምግባር መተላለፍ
እንደተግዳሮት ይወሰዳል፡፡
ሐ. አሳታፊ ምልከታ
አሳታፊ ምልከታ አንዳንድ ጊዜ “ራስህ ስራው” ምልከታ በመባል ይታወቃል፡፡ ይኸውም
ጋዜጠኛ በጉዳዩ ውስጥ ራሱን አስገብቶና የጉዳዩ ተሳታፊ በመሆን መረጃን
የሚሰበስብበት መንገድ ስለሆነ ነው፡፡ በአሳታፊ ምልከታ የጋዜጠኛውን መኖርና
አለመኖር የመረጃ ምንጮች ሊያውቁም ላያውቁም ይችላሉ፡፡ የመረጃ ምንጮች
የጋዜጠኛውን መኖር ካላወቁ የምስጢር ተመልካች (Undercover Observer) ይሆናል
ማለት ነው፡፡ ይህ የምስጪር ተመልካች ከድብቅ ምልከታ የሚለይባቸው የራሱ የሆኑ
መንገዶች አሉት፡፡ የምስጢር ተመልካች የጋዜጠኛው መኖር ባይታወቅም ከሚመለከተው
ጉዳይ ውስጥ ራሱን በማስገባት ይሳተፋል፤ በድብቅ ምልከታ ግን ጋዜጠኛው ተሳታፊ
አይደለም፡፡ ስለዚህ አንድ ጉዳይ ውስጥ ጋዜጠኛው ራሱን አስገብቶ ለመመልከት
ጋዜጠኛ መሆናችንን እና አለመሆናችንን ለመግለፅ የሚወሰነው በጉዳዩ ክብደትና ቅለት
ነው፡፡
ለምሳሌ፡- በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ሌላ ሃገር የሚያጓጉዙ ደላላዎችን በተመለከተ
መረጃ ለመሰብሰብ እንደ አንድ ተጓዥ ስደተኛ ሆነን ልንገባ እንችላለን፡፡ በዚህ ጊዜ
የእኛን ማንነት ደላላዎች ካወቁ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማወቁ ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ
ራሳችንን ደብቀን ምስጢራዊ ተመልካች እንሆናለን ማለት ነው፡፡
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf
Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf

Weitere ähnliche Inhalte

Was ist angesagt?

Was ist angesagt? (20)

Journalism
JournalismJournalism
Journalism
 
ማህበራዊ ሚዲያ-Social media
ማህበራዊ ሚዲያ-Social mediaማህበራዊ ሚዲያ-Social media
ማህበራዊ ሚዲያ-Social media
 
The concept of news
The concept of newsThe concept of news
The concept of news
 
News Judgements
News JudgementsNews Judgements
News Judgements
 
The associated press(ap)
The associated press(ap)The associated press(ap)
The associated press(ap)
 
Overview of Public Relations Agency
Overview of Public Relations AgencyOverview of Public Relations Agency
Overview of Public Relations Agency
 
Development journalism 1
Development journalism 1Development journalism 1
Development journalism 1
 
History of news agency
History of news agencyHistory of news agency
History of news agency
 
News agencies
News agenciesNews agencies
News agencies
 
Forms of radio news
Forms of radio newsForms of radio news
Forms of radio news
 
Organization of mass media in pakistan
Organization of mass media in pakistanOrganization of mass media in pakistan
Organization of mass media in pakistan
 
News Agencies
News AgenciesNews Agencies
News Agencies
 
Media Relations
Media RelationsMedia Relations
Media Relations
 
News gathering show
News gathering showNews gathering show
News gathering show
 
The relevance of models in communication research
The relevance of models in communication researchThe relevance of models in communication research
The relevance of models in communication research
 
Broadcast writing
Broadcast writingBroadcast writing
Broadcast writing
 
Publics in pr
Publics in prPublics in pr
Publics in pr
 
Development of Reuters
Development of ReutersDevelopment of Reuters
Development of Reuters
 
The digital newsroom presentation
The digital newsroom presentationThe digital newsroom presentation
The digital newsroom presentation
 
Public relation officer
Public relation officerPublic relation officer
Public relation officer
 

Mehr von HabibBeshir

Holy Quran Amharic.pdf
Holy Quran Amharic.pdfHoly Quran Amharic.pdf
Holy Quran Amharic.pdfHabibBeshir
 
tajweed rules.pdf
tajweed rules.pdftajweed rules.pdf
tajweed rules.pdfHabibBeshir
 
Holy Quran Amhari.pdf
Holy Quran Amhari.pdfHoly Quran Amhari.pdf
Holy Quran Amhari.pdfHabibBeshir
 
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdfየፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdfHabibBeshir
 
COMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdfCOMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdfHabibBeshir
 
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdfEnglish_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdfHabibBeshir
 
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdfLogic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdfHabibBeshir
 
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdfinclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdfHabibBeshir
 
COMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdfCOMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdfHabibBeshir
 
The art of Computer Programming.pdf
The art of Computer Programming.pdfThe art of Computer Programming.pdf
The art of Computer Programming.pdfHabibBeshir
 
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdfLove the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdfHabibBeshir
 
Introduction-to-Sociology-2nd-Canadian-Edition-1612311760.pdf
Introduction-to-Sociology-2nd-Canadian-Edition-1612311760.pdfIntroduction-to-Sociology-2nd-Canadian-Edition-1612311760.pdf
Introduction-to-Sociology-2nd-Canadian-Edition-1612311760.pdfHabibBeshir
 
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdfEnglish_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdfHabibBeshir
 
Grade 12 history ppt.pdf
Grade 12 history ppt.pdfGrade 12 history ppt.pdf
Grade 12 history ppt.pdfHabibBeshir
 
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdfinclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdfHabibBeshir
 
COMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdfCOMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdfHabibBeshir
 
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdfLogic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdfHabibBeshir
 
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdfLove the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdfHabibBeshir
 
Communicative English ll.pdf
Communicative English ll.pdfCommunicative English ll.pdf
Communicative English ll.pdfHabibBeshir
 
bsw_recruiting_9_28_16.pptx
bsw_recruiting_9_28_16.pptxbsw_recruiting_9_28_16.pptx
bsw_recruiting_9_28_16.pptxHabibBeshir
 

Mehr von HabibBeshir (20)

Holy Quran Amharic.pdf
Holy Quran Amharic.pdfHoly Quran Amharic.pdf
Holy Quran Amharic.pdf
 
tajweed rules.pdf
tajweed rules.pdftajweed rules.pdf
tajweed rules.pdf
 
Holy Quran Amhari.pdf
Holy Quran Amhari.pdfHoly Quran Amhari.pdf
Holy Quran Amhari.pdf
 
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdfየፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
የፋቲሀ_እና_የአጫጭር_ሱራዎች_መማሪያ_ማሜ.pdf
 
COMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdfCOMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdf
 
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdfEnglish_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
 
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdfLogic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
 
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdfinclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
 
COMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdfCOMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdf
 
The art of Computer Programming.pdf
The art of Computer Programming.pdfThe art of Computer Programming.pdf
The art of Computer Programming.pdf
 
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdfLove the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
 
Introduction-to-Sociology-2nd-Canadian-Edition-1612311760.pdf
Introduction-to-Sociology-2nd-Canadian-Edition-1612311760.pdfIntroduction-to-Sociology-2nd-Canadian-Edition-1612311760.pdf
Introduction-to-Sociology-2nd-Canadian-Edition-1612311760.pdf
 
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdfEnglish_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
English_for_Everyone__English_Grammar_Guide.pdf
 
Grade 12 history ppt.pdf
Grade 12 history ppt.pdfGrade 12 history ppt.pdf
Grade 12 history ppt.pdf
 
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdfinclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
inclusiveness_incl1012_mid_exam_for_freshman_students_by_ቀለሜ.pdf
 
COMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdfCOMPUTER VIRUSES (1).pdf
COMPUTER VIRUSES (1).pdf
 
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdfLogic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
Logic and Critical Thinking (Final)_281019125429 (1).pdf
 
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdfLove the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
Love the Secret to Your Success - Gloria Copeland(1).pdf
 
Communicative English ll.pdf
Communicative English ll.pdfCommunicative English ll.pdf
Communicative English ll.pdf
 
bsw_recruiting_9_28_16.pptx
bsw_recruiting_9_28_16.pptxbsw_recruiting_9_28_16.pptx
bsw_recruiting_9_28_16.pptx
 

Training-Manual-on-Radio-News-and-Programme.pdf

  • 1. i ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አዘገጃጀት (ለማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎች የማሰልጠኛ ማንዋል) አዘጋጆች፡- ደሳለው ጌትነት ሐይማኖት ጌታቸው አርታዒ፡- ኤርሚያስ ፀጋዬ ጥር 2009 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ፣ ኢትዮጵያ
  • 2. i ማውጫ አርዕስት ገፅ መግቢያ............................................................................................................................ 1 የስልጠናው ዓላማ ............................................................................................................. 4 ክፍል አንድ...................................................................................................................... 5 1.የልማታዊ ጋዜጠኝነት ንድፈ ሃሳብና የማህበረሰብ ሚዲያ ................................................... 5 1.1 የማህበረሰብ ሚዲያ ምንድን ነው?......................................................................................6 1.2 ልማታዊ ጋዜጠኝነት ማለት ምን ማለት ነው? ..................................................................7 ክፍል ሁለት..................................................................................................................... 9 2.የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አዘገጃጀት .................................................................................. 9 2.1 ዜና ........................................................................................................................... 9 2.1.1 ዜና ምንድን ነው?.............................................................................................................9 2.1.2 የዜና ዓይነቶች.................................................................................................................11 2.1.3 የዜና ጠቀሜታዎች .........................................................................................................13 2.1.4 የዜና ጥንካሬዎችና ድክመቶች........................................................................................14 2.1.5 የዜና መመዘኛ እሴቶች ..............................................................................................15 2.1.6 የዜና አላባውያን ..............................................................................................................22 2.2 የዜና ምንጮች....................................................................................................................27 2.2.1 ዜና ከየት ይገኛል?......................................................................................................27 2.2.2 የዜና ምንጮች.............................................................................................................28 2.2.3 የዜና ምንጮች አያያዝ................................................................................................30 2.2.4 መረጃ እንዴት ይገኛል?..............................................................................................32 ሀ. ምልከታ ............................................................................................................................32 ለ. ቃለ መጠይቅ ....................................................................................................................39 ሐ. ምርምርና ጥናት..............................................................................................................48 2.3 የዜና አፃፃፍ ስልት..............................................................................................................48 2.3.1 የዜና ቋንቋ...................................................................................................................49 2.3.2 መሪ አንቀፅ (Lead)....................................................................................................52 2.3.3 የአርስተ ዜና አፃፃፍ....................................................................................................53 2.3.4 የዜና መዋቅር..............................................................................................................54
  • 3. ii 2.3.5 የሬዲዮ የዜና አፃጻፍ ፎርማቶች.................................................................................57 2.3.5 የሬዲዮ ዜና አፃጻፍ ደንቦች.........................................................................................63 3. የሬዲዮ ፕሮግራም...................................................................................................... 65 3.1 የሬዲዮ ፕሮግራም ማለት ምን ማለት ነው?....................................................................65 3.2 የሬዲዮ ፕሮግራም ዓይነቶች..............................................................................................65 3.2.1 የማስተማርያ ፕሮግራም.............................................................................................65 3.2.2 የማሳወቂያ ፕሮግራም.................................................................................................66 3.2.3 የመዝናኛ ፕሮግራም...................................................................................................66 3.3 የሬዲዮ ፕሮግራም ባህርያት ..............................................................................................67 3.4 የሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅት................................................................................................68 3.4.1 የቅድመ-ዝግጅት ምዕራፍ............................................................................................69 3.4.2 የዝግጅት ምዕራፍ .......................................................................................................73 3.4.1 የድህረ ዝግጅት ምዕራፍ.............................................................................................74 ዋቢ መፅሐፍት............................................................................................................... 75 አባሪ፡- የሬዲዮ ፕሮግራም ፕሮፖዛል አዘገጃጀት................................................................. 76
  • 4. 1 መግቢያ የጋዜጠኝነትን ፅንሰ-ሃሳብ በተለያየ መልኩ የሚተረጉሙ ብዙ አካላት አሉ፡፡ ይኸውም ከጋዜጠኝነት ጋር ባላቸው ቅርበትና ለጋዜጠኝነት ካላቸው አመላካከት የመነጨ ነው፡፡ ለጋዜጠኝነት የተለያየ ትርጓሜ ቢኖረውም ትርጉሞቹ የተወራረሰ ባህሪ አላቸው፡፡ ከነዚህም ትርጉሞች ውስጥ አንዳንዶቹን ለመጠቃቀስ የሚከተለው ትርጓሜ አንዱ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት ማለት መረጃዎችን ከምንጮቻቸው የመሰብሰብ፣ በዜና፣ መጣጥፍና ሃተታ መልክ በማዘጋጀት በብዙሃን መገናኛ የማሰራጨት ሙያዊ ጥበብ ነው፡፡ ብዙሃን መገናኛ ስንል ሰሌዳ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችን፣ በራሪ ወረቀቶችን፣ የቢሮ ውስጥ ህትመቶችን፣ ጋዜጣ፣ መፅሔት፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣መፅሐፍ፣ ፊልምና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡ ይህም ማለት ጋዜጠኝነት በነዚህ ብዙሃን መገናኛ አማካኝነት መረጃን ከመረጃው ባለቤት ወደ አንባቢው፣ አድማጩ ወይም ተመልካቹ በተለየ አዘገጃጀት የማቅረብ ጥበብ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት የሚለውን ቃል መጀመሪያ አካባቢ የሚያገለግለው ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን በጋዜጣ አትሞ ማውጣት ነበር፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ጋዜጠኝነት በጣም ሰፊ የሆነ አውድ አለው፡፡ ይኸውም ከብሮድካስትና ዌብሳይት ሚዲያ መጀመር ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ጋዜጠኝነት መረጃን ቆፍሮና እውነታውን አጣርቶ ሁነቶችን፣ ጉዳዮችንና ሂደቶችና ከብዙሃኑ ህዝብ በጋዜጣ፣ በመፅሔት፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣በኢንተርኔት እና በመሳሰሉት ማዳረስ የሚቻልበት የሙያ ዘርፍ ሲሆን በዋናነት መረጃን የመሰብሰብ፣ የማጠናከር፣ የመፃፍ፣ አርትዖት ሥራ የመስራት፣ ፎቶግራፍ የማንሳት፣ የህትመት የዲዛይን ሥራን እና የማሰራጨት ሥራዎችን አካቶ የያዘ ሙያ ነው፡፡ ህብረተሰቡ መረጃ የማድረስ ዓላማ በመያዝ ጋዜጠኝነት ግለሰቦችን፣ ድርጅቶችን፣ ተቋማትን፣ መንግስትንና የንግድ ተቋማትን እንዲሁም ማህበራዊና ባህላዊ እሴቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ሽፋን የሚሰጥ ሙያ ነው፡፡ በህንድ አገር የጋዜጠኝነት አባት በመባል የሚታወቁት ፕሮፌሰር ፓታን ዳሊ ሰፒ ስለጋዜጠኝነት ሲናገሩ፡-
  • 5. 2 ጋዜጠኝነት ሰውን ልጅ ሰብዓዊ መብት የሚያስከብር፣ የታመነ የዲሞክራሲ ስርዓት አራማጅ እንዲሁም የፍትህ ርትዕ ጠበቃና የህዝብ ድምፅ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት በነፃ ሃሳብን የመግለጫ መሳሪያ፣ እንዲሁም የህሊናን ነፃነት ማዳበሪያ ፍቱን ማስተላለፊያ መሳሪያ በመሆኑ በህብረተሰብ የሙያ ዝርዝሮች ውስጥ ከፍተኛውን ቦታ መያዝ የሚገባው ተግባር ነው፡፡ እንደህንዳዊው ፕሮፌሰር ጋዜጠኝነት ከምንም በላይ ከራስ ጥቅም በፊት የማህበረሰባዊ ጥቅምን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት ድምፅ አልባ ለሆኑ የማህበረሰብ አካላት ድምፅ መሆን መቻል ነው፡፡ ጋዜጠኝነት ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና ለህግ መከበር ከፍተኛ የሆነ ሥራ የሚሰራ የሥራ መስክ ነው፡፡ የጋዜጠኝነት ዋነኛ የስራ ማሳያ የሆኑት የብዙሃን መገናኛዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ብዙሃን መገናኛዎች ህዝባዊ የሆኑ ጉዳዮችን በመረጃና በአስተያየት ተቀሽረው የሚቀርቡበት ነው፡፡ ጋዜጠኝነት መረጃን ጥሩውን ከድፍርሱ፣ ምርቱን ከእንክርዳዱ በመለየት መረጃዎችን፣ አስተያየቶችን እና ሁነቶችን ከህብረተሰቡ ለህብረተሰቡ የማሰራጨት ስራ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት ሁነቶችን፣ ሃሳቦችን፣ መረጃዎችን እና ተቃርኖዎችን በየአውዳቸው እየመረጠ የማስቀመጥና የማቅረብ ተግባርን የያዘ ሙያ ነው፡፡ ጋዜጠኝነት የድርጊቶችንና አስተያየቶችን እውነትን፣ ውክልናቸውንና ጠቀሜታቸውን በመገምገም የሚቀርብበት የሙያ ዘርፍ ሲሆን የማያቋርጥ ሂደትም ጭምር ነው፡፡ የማያቋርጥ ሂደት ሲባል ደግሞ ዓለም እስካለች ድረስ የመረጃ ፍሰት ከአንዱ የዓለማችን ክፍል ወደ ሌላው የሚያደርገው ጉዞ ስለማይነጥፍ በመሆኑ ነው፡፡ በአጠቃላይ ጋዜጠኝነት ለዜና፣ ለመጣጥፍና ለሃተታ የሚሆኑ ጉዳዮችን ከምንጫቸው የማሰባሰብ፣ የማዘጋጀትና በበራሪ ፅሁፎች፣ በሚበተኑ ወረቀቶች፣በጋዜጦች፣ በመፅሔቶች፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን እና በማህበራዊ ድረ ገፅ የብዙሃን መገናኛዎች የማሰራጨት ሙያዊ ሂደት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ የጋዜጠኝነትን ትርጉም ከብዙሃን መገናኛ ጋር በተለይም ከብሮድካስት የሚዲያ ዘርፍ ጋር አያይዘው ያዩታል፡፡ ለዛም ነው አንድ ግለሰብ ጋዜጠኛ ነኝ ሲል በቀጥታ ከቴሌቪዥን ወይም ከሬዲዮ ተቋም እንደመጣ
  • 6. 3 አድርገን የምንወስደው፡፡ ነገር ግን ጋዜጠኝነት ሁልጊዜም ከብዙሃን መገናኛ ጋር ብቻ ማሰብ የተሳሳተ ግንዛቤ ነው፡፡ ምክንያቱም ብዙሃን መገናኛ የመረጃ ማስተላለፊ መንገድ እንጂ በራሱ የጋዜጠኝነት ሙያ አይደለም፡፡ ስለዚህ በበራሪ ወረቀቶች፣ በማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ በመስሪያ ቤት ህትመቶች ወዘተ የሚሰራጩ መረጃዎች በጋዜጠኝነት ዘውግ ውስጥ ይከናወናሉ፡፡ በሬድዮ የሚደረግ የጋዜጠኝነት /የሚዲያ / አተገባበር በድምፅ የሚደረግ የቃላት ጨዋታ ነው፡፡ በታሪካዊ አመጣጣቸው ሲታዩ ቴሌቭዥን ሬድዮን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ እንዲህ በመሆኑም ብዙ የብዙኅን መገናኛ ጠቢባን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቴሌቭዥን እየተወደደ በመሄዱ ሬድዮ የመሞት እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው ይላሉ፡፡ በዚህ ምክንያትም ብዙ የጋዜጠኝነት አጥኝዎች ፍላጎታቸው ወደ ቴሌቭዥን እያጋደለ የመሄድ አዝማምያ አሳይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የጠቢባኑ መላምት ሳይሆን ቀርቶ ሬድዮ እስከ አሁን በጣም ተወዳጅና ተደማጭ የብዙኅን መገናኛ ዓይነት ነው፡፡ በተለይ ሬድዮ የኤሌክትሪክ መብራት ሀይል ባላገኙ የገጠር አከባቢዎች በጣም ተፈላጊና ተመራጥ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ሬድዮ የሚያዳምጡበት ምክንያት ምን እየተደረገ ምን እየሆነ እና ነገሮች ምን እንደሚመስሉ በአፋጣኝ ለማወቅ ሲፈልጉ ነው፡፡ ሬድዮ አንድ ድርጊት ሲፈፀም ወይ ሲከወን ወድያው በፍጥነት /in speed/ ለአድማጮች ያደርሳል፡፡ ይህ አንዱ የሬድዮ ባህርይ ነው፡፡ ሬድዮ እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ተመራጭ ከሚያደርጉት ነገሮች አንደኛ ከቦታ ወደ ቦታ ይዞ ለመንቀሳቀስ /being portable) ሁለተኛ ሬድዮን እያዳመጥክ ሌላ ተጓዳኝ ስራ መስራት ይቻላል፡፡ ሌላው የሬድዮ እንደ ብዙኅን መገናኛ ተመራጭ የሚዲያደርገው የሰው ሃይል ብዛት ቆጣቢነቱ ነው፡፡ ይህ ሲባል በሬድዮ ለሚደረግ የመረጃ ስርጭት አንድ ሰው ከስልክ በሚመጡ ብዙ ሃሳቦች ሊያስተናግድ ይችላል፡፡ የካሜራ የመብራት ባለሞያዎች ላያስፈልጉ ይችላሉ፡፡ ይህ የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ማንዋል ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ስለማህበረሰብ ሬዲዮ ጠቅላላ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሲሆን ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ለማህበረሰብ ሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አሰራር ላይ ዝርዝር ገለፃ ይሰጣል፡፡
  • 7. 4 የስልጠናው ዓላማ የዚህ ሥልጠና ዓበይት ግቡ የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለሙያዎችን የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራሞችን ሙያዊና ስኬታማ በሆነ መንገድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ማስቻል ሲሆን ሰልጣኞች ይህንን ስልጠና ሲያጠናቅቁ የሚከተሉት ክህሎቶች ይኖሯቸዋል፡፡  የማህበረሰብ ሬዲዮ ምንነትን ያውቃሉ፤  ለማህበረሰብ ሬዲዮ የሚሆን ዜናን ያዘጋጃሉ፤  የመረጃ ምንጮችን አያያዝ ያውቃሉ፤  የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን ይለያሉ፤  የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶችን ተጠቅመው መረጃን ይሰበስባሉ፤  የሬዲዮ ፕሮግራም ፕሮፖዛሎችን ማዘጋጀት ይችላሉ፤  ሬዲዮ ፕሮግራሞችን ያቀርባሉ፤  ዜናና ፕሮግራሞችን በስቱዲዮ ውስጥ ማንበብ ይችላሉ፤
  • 8. 5 ክፍል አንድ 1. የልማታዊ ጋዜጠኝነት ንድፈ ሃሳብና የማህበረሰብ ሚዲያ በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን የብዙሃን መገናኛ ተቋማት ዋነኛ የልማት ደጋፊ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ልማት ማለት ምን ማለት ነው የሚለው ጉዳይ የተለያዩ ዓይነት ትርጓሜዎች ቢሰጠውም አሜሪካዊ ምሁር ሮጀርስ (1976) ልማት ምን እንደሆነ የሚከተለውን ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ልማት ማለት በማህበረሰቡ ውስጥ ማህበራዊ ለውጥ የሚያመጣ አሳታፊ የማህበራዊና የማቴሪያል ልቀት በማምጣት አብዛኛውን የማህበረሰብ ክፍል በአካባቢው ላይ ተቆጣጣሪና ከአካባቢው ተጠቃሚ የሚያደርግ ሂደት ነው፡፡ ከሮጀርስ ትርጉም መረዳት የሚቻለው ልማት ማለት ሂደት ነው፤ ልማት ማለት ማህበራዊ ለውጥን ያመጣል፣ ልማት ማለት አብዛኛውን የማህበረሰብ ክፍል ይጠቅማል፣ ልማት ማለት መሻሻል ነው፡፡ ልማትን በተመለከተ ለረዥም ጊዜ ሁለት ዓበይት አስተሳሰቦች ብቻ ነበሩ፡፡ ይኌም ዘመናዊነት (Modernaization paradigm) ና ጥገኝነት (Dependecy paradigm) ናቸው፡፡ ሁለቱ ፅንፍ አስተሳሰቦች ልማትን በማምጣት ድሃ የዓለማችን ክፍሎችን ማሳደግ የሚቻልበት ሁኔታ በተለያየ መንገድ ቀይሰዋል፡፡ የዘመናዊነት አስተሳሰብ ለድሃ አገሮች መሰረታዊ ችግራቸው ኋላቀርነታቸው ሲሆን ማደግ የሚችሉት ምዕራባውያን አገሮች በሚሰጧቸው እርዳታ ዝግመታዊ በሆነ መልኩ ይለማሉ የሚል ነው፡፡ በአንፃሩ የጥገኝነት አስተሳሰብ አራማጆች የሚሉት የደሃ ሃገሮች ችግር የምዕራባውያን ቅኝ ግዛትና ጭቆና ነው ስለሆነም መፍትሄው የእነሱን እርዳታ መቀበል ሳይሆን ከእነሱ ጋር
  • 9. 6 ያለውን ግንኙነት በማቋረጥ ለራስ መስራት ነው ይላሉ፡፡ በዚህ መሃል የሁለቱ ፅንፍ የወጣ አስተምህሮ ዓለማችን በግሎባላይዜሽን ዘመን አንዱ ለአንዱ አስፈላጊ ስለሆነ የሚያስሄድ ስላልሆነ ሶስተኛ አማራጭ “ሌላው አስተምሮ” የሚል የሶስተኛ ዓለም ሃገራት ፈጠሩ፡፡ ይህ አስተምሮ ልማትን ማየት የሚፈልግበት ዕይታ ልማት መጀመር ያለበት ታች ካለው ተራ ህዝብ ሲሆን የሃገሩን ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሥነ-ምህዳሩን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት ይላሉ፡፡ ስለዚህ ይህንን አማራጭ በመያዝ ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች ሲሰሩ በዋናነት የሚከተሉት ማህበረሰቡን ያሳተፈና ተጠቃሚ የሚያደርግ አካሄድን መሆን ይኖርበታል፡፡ ተራውን የማህበረሰብ ክፍል ለማሳተፍ ደግሞ የመረጃ ተደራሽነት በዘልማዳዊው ሚዲያ አስቸጋሪ ስለሚሆን የማህበረሰብ ሚዲያ ወይም የማህበረብ አገልግሎት የሚሰጡ የሬዲዮ ጣቢያዎች በየአካባቢው መኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡ 1.1 የማህበረሰብ ሚዲያ ምንድን ነው? በአሁኑ ሰዓት የማህበረሰብ ሚዲያ በተደራሽነቱና በሚሰጠው አገልግሎት ከመንግስታትና ከልማት ድርጅቶች በሰፊው ዕውቅናን እያተረፈ ይገኛል፡፡ ምክንያም ይህ የሚዲያ ዘርፍ በዋናነት ድምፅ አልባ የነበሩትን ደሃና የተገለሉ/ የተረሱ የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምጽ የሚሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ የማህበረሰብ ሚዲያ የለውጥ አካል ሲሆን በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ-ልቦናዊ ለውጦች እንዲመጡ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል፡፡ ይህ ሚዲያ ለአካባቢው ተራ የማህበረሰብ ክፍሎች የውይይት መድረክን በመክፈት ድምጻቸው እንዲሰማ በማድረግ ያገለግላል፡፡ ይህ ሚዲያ የሚቋቋመው ለማህበረሰቡ ሲሆን የሚያስተዳድረውም የሚደግፈውም ራሱ ማህበረሰቡ ነው፡፡ የማህበረሰብ ሚዲያ አካባቢያዊነት፣ የብዙሃን ተሳትፎ፣ እና የለውጥ ተምሳሌት መሆን የሚታወቅባቸው ባህርያቶቹ ናቸው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን አሰራር ደግሞ የማህበረሰብ ሚዲያ ማለት ለትርፍ ያልተቋቋሙ የሬዲዮ ወይም የቴሌቪዥን አገልግሎት ሲሆን በህዝቡ ፍላጎትና ይሁንታ በመቋቋም የአንድ የተወሰን ቦታ ላይ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ፍላጎት በማንፀባረቅ በእነሱው የሚቋቋምና የሚሰራ አገልግሎት ነው፡፡ ይህም ማለት የማህበረሰብ ሬዲዮ ባለቤቱም፣ ሰራተኞቹም፣ አስተዳደሮችም ራሱ የማህበረሰቡ አካላት ማለት ነው፡፡
  • 10. 7 የማህበረሰብ ሬዲዮ አራቱ መርሆች ብሎ ጃን ሰርቪያስ (2007) ያስቀመጣቸው የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. ባለቤትነቱ የማህበረሰቡ ነው፤ 2. የሚሰጠው አገልግሎት ለማህበረሰቡ ነው፤ 3. ህዝብን አሳታፊ መሆን አለበት እና 4. ለትርፍ የማይሰራ ተቋም የማህበረሰብ ተሳትፎ የማህበረሰብ ሚዲያ ቁልፍ ተግባር ሲሆን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ድምፃቸውን ማሰማት ያልቻሉትን የማህበሰብ ክፍሎች እንዲናገሩ እና እንዲወያዩ ማስቻል አለበት፡፡ ስለዚህ የማህበረሰቡ ክፍሎች ከአድማጭ ወደ ተሳታፊ ይቀየራሉ ማለት ነው፡፡ የማህበረሰብ ሬዲዮ በኢትዮጵያ በሚያስገርም ፍጥነት ከመንግስትና ከግሉ ሚዲያ በኋላ ተነስቶ በአሁኑ ሠዓት 30 የሚደርሱ የሬዲዮ ጣቢያዎች ከመንግስት ፈቃድ አግኝተው በሥራ ላይ ናቸው፡፡ የማህበረሰብ ሬዲዮ አሰራር መመሪያ ቁጥር 04/2004 መሰረት በኢትዮጵያ የተለያዩ የማህበረሰብ ሬዲዮ አገልግሎቶች በመከፈት ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ የሬዲዮ ጣቢያዎች የልማታዊ ጋዜጠኝነትን ሥራ እንዲያከናውኑ በማሰብ ነው የሚቋቋሙት፡፡ የመወያያ ጥያቄዎች  የማህበረሰብ ሬዲዮ ምንድን ነው?  የማህበረሰብ ሬዲዮ አገልግሎቱ ለማን ነው?  የማህበረሰብ ሬዲዮ ከሌሎች የሬዲዮ ወይም የሚዲያ ተቋማት በምን ይለያል? 1.2 ልማታዊ ጋዜጠኝነት ማለት ምን ማለት ነው? ጋዜጠኝነትና ልማት እንደጓድ፣ እንደአቀጣጣይ ወይም ደግሞ እንደተች/ቃፊር ያለ ግንኙነት አላቸው፡፡ የልማታዊ ጋዜጠኝነት ፅንሰ ሃሳብ በምዕራብ ሃገራት የዜና አሰራር ላይ ደስተኛ ያልሆኑ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች በ1980ዎቹ ላይ የፈጠሩት የሚዲያ ፍልስፍና ነው፡፡ እንደ ሚዲያ ንድፈ ሃሳቦች ሚዲያ ብሄራዊ ልማት እንዲፋጠን የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ልማቶችን በማቀናጀት ከፍተኛ ሥራ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ ልማታዊ ጋዜጠኝነት ልማታዊ
  • 11. 8 አጀንዳዎችን በትልቁም ሆነ በትንሹ በጥልቀት እየፈተሸ ይሰራል፡፡ የልማት ፕሮጀክቶችን ተገቢነት እና አካሄድ ላይ የመደገፍ ሥህተቶች ካሉም የማጋለጥ ሥራ ይሰራል፡፡ በአጠቃላይ ልማታዊ ጋዜጠኝነት የሚያተኩረው ልማት ተኮር የሆኑ ዜናዎችን መረጃ በመሰብሰብ ለማህበረሰቡ ማድረስ ላይ ነው፡፡ የልማታዊ ጋዜጠኝነት ቁልፍ ተግባራት (አጋራዋል፣ 1980) 1. በዕቅድና በትግበራ መካከል ያለውን ልዩነት መዘገብ፤ በማኅበረሸቡ ላይ ያለውን ተፅዕኖም ማጋለጥ፤ 2. በዕለት ከዕለት ዜናዎች ሳይሆን በዘላዊ የልማት ሂደቶች ላይ ማተኮር 3. ከመንግስት ነፃ ሆኖ ለመንግስት ገንቢ አስተያየቶችን መስጠት 4. ለሃገር ግንባታ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ 5. ደሃና ተራ የማህበረሰብ ክፍሎችን አቅም ማጎልበት የቡድን ውይይት ውድ የዚህ ስልጠና ተካፋዮች የማህበረሰብ ሬዲዮ የልማታዊ ጋዜጠኝነት ማሳያ የልማት አጋር ነው ሲባል ምን ለማለት ተፈልጎ እንደሆነ በቡድን ተወያይታችሁ አብራሩ፡፡ በዚህ የማህበረሰብ ሬዲዮ የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄ መመለስ የሚቻልበትን መንገድ በመነጋገር አብራሩ፡፡ ማጠቃለያ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ማህበረሰቡ ድምጹን የሚያሰማባቸው፣ ሃሳቡን የሚያስተናግድባቸው፣ የማህበረሰቡን ችግር በጋራ በመወያየት የሚፈታባቸው ራሱ ህዝቡ የሚያቋቁማቸውና የሚሰራባቸው ሲሆኑ አሰራራቸውም ሆነ አገልግሎታቸው ህዝባዊ ነው፡፡ ስለሆነም በሌሎች የሚዲያ ተቋማት ላይ አየር ላይ ለመዋል ያልቻልሁትን የአካባቢው ማህበረሰብ ድምፆች ያሰማል፡፡
  • 12. 9 ክፍል ሁለት 2. የሬዲዮ ዜናና ፕሮግራም አዘገጃጀት 2.1 ዜና 2.1.1 ዜና ምንድን ነው? የመወያያ ጥያቄዎች  ዜና ምንድን ነው?  በየቀኑ ምን ያህል ዜና ትሰማላችሁ?  ዜና ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? ዜና ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ሁሌም ለጋዜጠኝነት ሙያ ቅርብ የሆነ ሰው ወይም ደግሞ ዘወትር ምሽት በጉጉት ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን የሚከታተል ሰው በቀላሉ ይመልሰዋል፡፡ በርካታ ቤተሰቦች በዜና ሰዓት ህጻናትን ዝም በሉ ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር ያወሩበት የነበረውን ጉዳይ ቆም አድርገው በትኩረት የሚከታተሉት የብዙሃን መገናኛ ገፀ በረከት ዜና ነው፡፡ ምክንያቱም ደግሞ ዓለማችን እንዴት ዋለች? ለሚለው ጉዳይ በቂ መልስ የሚሰጠው ዕለታዊ ዜና ስለሆነ ነው፡፡ በማንኛውም የብዙሃን መገናኛ ማለትም በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥን፣ በጋዜጣ፣ በመፅሔት ወይም በኢንተርኔት ዜና ከሌሎች የብዙሃን መገናኛ በተሻለ አስፈላጊና የአድማጭ ተመልካችን ቀልብ መግዛት የሚችል የጋዜጠኝነት ዘውግ ነው፡፡ ስለሆነም ጥራት ያለው የዜና ዝግጅት ደግሞ አስፈላጊ ነው፡፡ አሁን ዓለማችን በሉላዊነት ምክንያት በጠበበችበት ሰዓት ቴክኖሎጂ በየቀኑ እንደአሸን በሚፈላበት ወቅት ብዙ ምርጫ ያለውን አንባቢ፣ አድማጭ ወይም ተመልካች ይዞ መገኘትና መዝለቅ ትልቅ ችሎታ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ውድድር በበዛበት የብዙሃን መገናኛ ሥራ ውስጥ በዘርፉ ከፍተኛ ዕውቀትና ልምድ ያካበቱ ጋዜጠኞች ዜናን መስራት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው ምን ያህሉ ሙያዊ ጋዜጠኞች ጥራት ላለው ዜና ትኩረት እንደሚሰጡ ነው፡፡
  • 13. 10 አያሌ የጋዜጠኝነት ምሁራን “ዜና” ለሚለው ቃል የተለያዩ ትርጎሞች ይሰጡታል፡፡ የትርጉማቸው መሰረተ ሃሳብ አንድ ቢሆንም የአተረጓጉም ዘይቤያቸው ግን በመጠኑ ልዩነት አለው፡፡ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የዜና አቻ ትርጉም ነው የሚባለው “News” የሚለውን ቃል ከቁም ትርጉሙ ሌላ ሁለት ዓበይት ቁምነገሮች ያንፀባርቃል፡፡ አንደኛው የቃሉ ዝርዝር ፊደላት N (North) ሰሜን, E (East) ምስራቅ, W (West) ምዕራብ እና S (South) ደቡብ ማለት ነው ይላሉ፡፡ ስለዚህ “News” በሚለው ቃል ውስጥ ያሉት አራት ፊደላት አራቱን መልክዓ ምድራዊ የዓለም ማዕዘናት ይጠቁማሉ ማለት ነው፡፡ ሁለተኛው “News” (ዜና) ከሚለው ቃል የሚገኘው ቁም ነገር ጋዜጣ “Newspaper” ለሚለው የእንግሊዘኛ ቃል መነሻ ወይም መሠረት መሆኑ ነው፡፡ ብዙዎቹ የሙያው ምሁራን ዜናን ዜና የሚያደርገው በዜና መልክ መዘጋጀቱ ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰቡ መሰራጨቱ ነው ይላሉ፡፡ የኦክስፎርድ እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት ዜና ማለት አዲስ፣ መሳጭ፣ እውነትና ያልተለመዱ ክስተቶች ዘገባ ነው ይላል፡፡ ይህም ማለት አብዛኛው ጋዜጠኛ ስለዜና ያለውን ግንዛቤ ማካተት የሚችል ይመስላል፡፡ ዜና ስለአንድ የህብረተሰብን ትኩረት በብርቱ ሊስብ ስለሚችል ወይም በህዝብ ህይወት ላይ ተፅዕኖ ስላለው ክስተት ለጋዜጣ፣ ለዜና መፅሔት፣ ለዜና አገልግሎት፣ ለሬዲዮና ለቴሌቪዥን፤ በአጠቃላይ ለብዙሃን መገናኛ የሚዘጋጅ ዘገባ ነው፡፡ ሌላው በኦክስፎርድ እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ ካለው ትርጓሜ የምንረዳው ዜናን ዜና የሚያደርገው አዲስነቱ ነው፡፡ ሁልጊዜም ሠዎች ከለመዱትና ከሰለቻቸው ውጭ የሆነን ጉዳይ ጆሮ ሰጥተው ስለሚያዳምጡ ነው፡፡ ለዚያም ነው የዜና ቋንጣ የለውም እየተባለ በወቅቱ አየር ላይ ወይም ህትመት ላይ ያልዋሉ ጉዳዮች እንደዜና የማይቆጠሩት ወይም የማይቀርቡት፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዜና ሁሌም በእውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ሌላው የጋዜጠኝነት ትርጓሜ ደግሞ የታሪክ የመጀመሪያ ንድፍ ነው ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ በችሎላ የሚዘጋጅ ሥነ-ፅሁፍ ነው ይላሉ፡፡ ስነ-ፅሁፍም ሆነ የታሪክ ፅሁፍ በአንድ ወቅት የዜና አካል የነበረ ስለሆነ ነው ይህንን ትርጓሜ የሚሰጡት፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት በሃገራችን ተከስተው ያለፉ ጉዳዮች ዛሬ ላይ ታሪክ ቢሆኑም በወቅቱ ግን በየብዙሃን መገናኛዎቹ ዋነኛ የዜና ዘገባዎች ነበሩ፡፡ በቅርብ ታሪካችን ውስጥ ያሉትን ለመጥቀስ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ ምርጫ 97፣ የኢትዮጵያ ሚሊኒየም፣ የጠቅላይ
  • 14. 11 መለስ ዜናዊ ህልፈተ-ህይወት አሁን ላይ ታሪክ ቢሆኑም በወቅቱ ግን የተመረጡ ዜናዎች ነበሩ፡፡ ዜና ሰውን የሚያስደነግጥ፣ የሚያስገርም ወይም የሚያስደንቅ፣ የሚያስደስት ወይም የሚያሳዝን የአዳዲስ ኩነቶች መገለጥ፣ የአዳዲስ ድርጊቶች መፈፀም፣ መታወጅ፣ ወይም የአንድ ክስተት ይፋ መሆን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ዜና ማለት ሰው ሲሰማው እውነታቸውን ነው እንዴ? በማለት በታላቅ አግራሞት እና መደናገጥ የሚቀበለው ወሬ ወይም መረጃ ነው፡፡ አንድ አባባል አለ፤ “ውሻ ሰው በላ” እና “ሰው ውሻ በላ” የሚሉ ሁለት ጉዳዮች ቢቀርቡ ዜና የሚሆነው “ሰው ውሻ በላ” የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም ዜና ማለት ያልተለመደና ሲሰሙት አግራሞች የሚያጭር መሆን ስላለበት ነው፡፡ ዜና ማለት ሰዎች ናቸው የሚል ትርጉምም ይሰጠዋል፡፡ ሰዎች የሚናገሩት፣ ሰዎች የሚሰሩት ሁሉ ዜና ነው፡፡ ስለዚህ ከሰዎች ንግግር፣ተግባር፣ ዕቅድ፣ ሥራ፣ ግጭት እየወሰድነ የምናቀርበው ስለሆነ ዜና ማለት ሰዎች ማለት ነው የሚል ትርጉም ለዜና ይሰጠዋል፡፡ በአጠቃላይ ዜና የአንድን ሁነት የመንገር ጥበብ ነው፡፡ 2.1.2 የዜና ዓይነቶች ዜና ሁሌም በተመሳሳይ መልኩ አይፃፍም፡፡ ይኸውም የዜናው ዓይነትና በምን መልኩ ቢቀርብ ይሻላል ከሚለው አንጻር ነው የሚታየው፡፡ ለምሳሌ የሚከተሉትን ዜናዎች ተመልከቱ፡፡ 1. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ፡፡ 2. ኢትዮጵያን ላለፉት 38 ዓ.ም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በትግልና በአመራር ሲመሩ ነበር፡፡ በተለይም ባለፉት 21 ዓመታት የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ካሳለፍነው የግንቦት ወር ጀምረው ህመም ስለተሰማቸው ለህክምና ውጪ ሲመላለሱ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ትናንትና ማታ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ አረፉ፡፡ ዜና በሁለት መልኩ ሊፃፍ ይችላል፡፡ ይኸውም በቀጥታና በተዋዛ መልኩ፡፡
  • 15. 12 1. የቀጥታ ዜና (Hard News) የቀጥታ ዜና አንድን ድርጊት በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወዲያኑና በወቅቱ የሚዘገብ የዜና ዓይነት ነው፡፡ የቀጥታ ዜና የሚጀምረው በድርጊቱ ውስጥ በጣም ጠቃሚ በሆነው ጉዳይ ሲሆን ነገሮችን በትኩሱ ማቅረብ ዋነኛ መለያው ነው፡፡ አቀራረቡም የተከሰተውን ጉዳይ ቀላል፣ ግልፅ፣ ቀጥተኛና እውነተኛ በሆነ መልኩ ያቀርባል፡፡ የቀጥታ ዜና በአብዛኛው ኩነት-ተኮር (Event-oriented) ነው፡፡ ኩነቱን በተመለከተ ቀጥተኛ የሆነ የዜና አቀራረብ መንገድ ይጠቀማል፡፡ በርካታ ኩነቶች በቀጥታ የዜና አቀራረብ የሚቀርቡ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል ለምሳሌ ያህል መፈንቅለ መንግስት፣ ሹምሽር፣ ምርጫ፣ የፖሊስ ሪፖርት፣ አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣ ግድያ፣ መንግስታዊ ስብሰባዎች፣ ህዝባዊ መድረኮች፣ የአየር ንብረት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የዋጋ ጉዳይ (ገበያ ነክ ዜናዎች)፣ .. ወዘተ ናቸው፡፡ የቀጥታ ዜና በሚፃፍበት ጊዜ መረጃን ማዛባት፣ በተገቢው ቦታ አለማስቀመጥ፣ ወይም የተሳሳተ ነገር መጨመር ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡ ምክንያቱም በዜናው መንስኤ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊና አገራዊ አደጋ ስለሚያስከትል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ድምዳሜ መስጠት፣ አሉባልታዎችን ማካተት፣ የግል አመለካከትንና ያልተጣሩ ተባራሪ ወሬዎችን ማካተትም አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የቀጥታ ዜናዎች በአድማጭ ተመልካች ላይ ያላቸው ተፅዕኖ ከፍተኛ ስለሆነ ነው፡፡ 2. የተዋዛ ዜና (Soft News ) የተዋዛ ዜና ወይም ዋዘኛ ዜና ከቀጥታ ዜና ጋር ሲወዳደር በዜና አፃጻፉ የተለየ የራሱ የሆኑ ባህርያት አሉት፡፡ ይኸውም ለሁነቶች እና ለጊዜ ትኩረት አይሰጥም፡፡ ይልቁንም ለሰው ስሜት ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነውው፡ በአብዛኛው ጊዜ ለብዙዎቹ እንደ አማራጭ የሚቀርብ የዜና ዓይነት ነው፡፡ የተዋዛ ዜና ተዋዝቶ የሰውን ስሜት በሚነካ መልኩ የፀሐፊው ችሎታ እና አቅም ተጨምሮበት የሚፃፍ ዜና ሲሆን ለመስማት፣ ለማንበብ ወይም ለማየት ማራኪ፣ አጓጊ እና አስደሳች ሆኖ የሚቀርብ ነው፡፡ የተዋዛ ዜና በአድማጭ ላይ እዚህ ግባ የሚባል ተፅዕኖ ማሳደር ባይችልም እንኳ በዕለት ከዕለት ህይወት ውስጥ ያለውን የማህበራዊ ሁኔታና የሁኔታዎች ለውጥ ለማወቅ ይረዳል፡፡
  • 16. 13 ለምሳሌ ያህል ግለታሪኮች፣ የመዝናኛ ወሬዎች፣ ባህላዊ ወጎችና የመሳሰሉት የሚጠቀሱ የተዋዛ ዜና ሁነታዎች ናቸው፡፡ 2.1.3 የዜና ጠቀሜታዎች በርካታ የዘርፉ ተመራማሪዎች ሠዎች ለምን ዜናን ይከታተላሉ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ጥናት አካሂደዋል፡፡ አንዳንዶቹ የተፈጠረውን ለማወቅ፤ ሌሎች ደግሞ የሚፈጠረውን ወይም ይፈጠራል ተብሎ የሚጠበቀውን ለማወቅ ዜናን ይከታተላሉ፡፡ የዜና ዘገባ በተወሰ ጊዜ የተለያዩ ዘርፈ-ብዙ መረጃዎችን መስጠት ስለሚያስችልም የራሱ የሆነ አውንታዊ ሚና አለው ምን እንኳ ይህንን የሚቃወሙ ባይጠፉም፡፡ የሰው ልጆች ለምን ዜናን ይከታተላሉ ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሆኑ ዋና ዋና ምክንያቶችን እንደሚከተለው ለማየት ተሞክሯል፡፡ 1. በሰውና በንብረት ላይ ከሚደርስ አደጋ ለመጠንቀቅ፡፡ በዜና አማካኝነት በሰውና በንብረት ላይ በጦርነት፣ ግጭት፣ በተፈጥሮ አደጋ፣ በወረርሽኝ፣ በተመረዙ ምርቶች ወዘተ አማካኝነት የሚደርሱ አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት የማስጠንቀቂያ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ስጋት ላይ የጣለው የኢቦላ ወረርሽኝ ብዙሃን መገናኛዎች የሚሰጡት የማስጠንቀቂያ ዜና ለዚህ ምርጥ ምሳሌ ነው፡፡ 2. ምን እንደተፈጠረና ሊፈጠር እንደሚችል መንገር፡፡ በዜና በዓለም ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለና ሊፈጠር የሚችል ጉዳይ እንዳለ በዜና አውታሮች አማካኝነት ማወቅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የልማት ዘገባዎች፣ የመድኃኒት መፈብረክ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚወጡ ልማቶችንና ለውጦችን በተመለከተ የመንገር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ መንግስት ለመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሬ አደረገ እና መንግስት ለመንግስት በቡድን በቡድን ሆናችሁ አንድ ቀጥተኛ ዜናና አንድ ደግሞ የተቃዛ ዜና ጻፉ፡፡
  • 17. 14 ሠራተኞች ከሃምሌ ጀምሮ የደመወዝ ጭማሬ ሊያደርግ ነው የሚሉ ዜናዎች የዜናን የመንገር ጠቀሜታ ያሳያሉ፡፡ 3. ለሰው ልጅ ነፃነት ስጋት የሆኑ ነገሮችን ማጋለጥ፡፡ ለሰው ልጅ ስጋት የሆኑትን ጉዳዮች ማለትም ኢ-ፍትሃዊነት፣ ሙስና፣ ሽብርተኝነት፣ ሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ የጉልበት ብዝበዛ፣ ፖለቲካዊ ጭቆና ወዘተ ዓይነት ጉዳዮች ለሰው ልጅ ነፃነት ስጋት በመሆናቸው ሊወገዱ ይገባል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዜና የማጋለጥ ተግባር ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ በዜና የማጋለጥ አገልግሎት ዜና እንዲከታተሉ የሚያደርግ ምክንያት ነው፡፡ 4. የህብረተሰቡን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ መሸሻል እንዲመጣ መርዳት፡፡ ስለኢኮኖሚ፣ ልማት፣ ሥራ፣ ወዘተ ዓይነት ዜናዎች የህብረተሰቡን ኑሮ እንዲሻሻል የሚረዱ ስለሆነ ዜና የኑሮ መሻሻል እንዲመጣ ጠቀሜታ አለው፡፡ ማንኛውም የብዙሃን መገናኛ የሚሰጣቸው ጥቅሞች አሉት፡፡ ይኸውም ማሳወቅ፣ ማስተማርና ማዝናናት ናቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ የማሳወቁ ሥራ የሚሰራው በዜና ሲሆን ይህም የኑሮን ሁኔታ መሻሻል እንዲመጣ ወይም የመጣውን ለማወቅ ዜናን ይከታተላሉ፡፡ ለምሳሌ የማዳበሪያ ዋጋን በተመለከተ የሚሰራጭ ዜና በአርሶ አደሩ ህይወት ላይ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ስላለው ዜናን አፅንዖት ሠጥተው ይከታተላሉ፡፡ 5. ብልሹ የአኗኗር ዘይቤን እንዲሻሻሉ ያግዛል፡፡ ስለህዝብ ሰፈራ፣ የወንጀል ድርጊት፣ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ አካባቢያዊ ጉዳዮች፣ የቤት ጉዳይ እና የመሳሰሉት ዜናዎች የህብረተሰቡን የአኗኗር ችግሮችን እንዲቀርፉ የሚነደፉትንና ሚከናወኑትን ተግባራት በዜና መከታተል ጠቃሚና የዜናን ሚና ያመለክታል፡፡ 2.1.4 የዜና ጥንካሬዎችና ድክመቶች ዜና በጣም ከፍተኛ የሆነ ተፈላጊነት ያለው የጋዜጠኝነት ዘውግ ነውው፡ ይኸውም ሰዎች ለተለያዩ ምክንያቶች ትኩረት ሰጥተው የሚከታተሉት ዘውግ፡፡ ዜና የራሱ የሆነ የአፃፃፍ ስልት ያለው ሲሆን በቀጥታና በተዋዛ መል ይቀርባል፡፡ ዜና የራሱ የሆነ ጠንካራና ደካማ ጎኖች አሉት፡፡
  • 18. 15 የዜና ጥንካሬዎች  በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መረጃን ይሰጣል  አዲስና ተገቢነት ያለው መረጃ ያቀብላል  የአድማጭ ተመልካችን አቅም ያጎለብታል  ዕውቀትን ያሳድጋል  ሚዛናዊነትን ያበረታታል  አድማጭ ተመልካቾች ሃሳባቸውን እንዲገልፁ ይረዳል የዜና ድክመቶች (ውስንነቶች)  በጣም አስፈላጊ ነገሮችን ብቻ ያቀርባል፤ ስለሆነም ብዙ ዝርዝር መረጃዎችን አያደርስም  በቦታና በጊዜ የተገደበ ነው፡፡ ይኸውም የምንፅፈው ለጋዜጣ ከሆነ በወረቀቱ ልክ ለብሮድካስት ከሆነ ደግሞ በአየር ሰዓቱ ልክ የተገደበ ነው  ብዙ ግብዓት ይፈልጋል በተለይም የቴሌቪዥን ዜና በርካታ የሰውና የንብረት ግብዓቶችን ይፈልጋል፡፡ 2.1.5 የዜና መመዘኛ እሴቶች የተፃፉ ዜናች ሁሉ አይታተሙም ወይም አየር ላይ አይውሉም ምክንያቱም ዜና መሠረታዊ የሆነ የዜና አፃፃፍ እሴቶችን አሟልቶ የቃፊሮችን (Gatekeepers) መመዘኛ አሟልቶ የይታተም ወይም የይሰራጭ ይሁንታ ማግኘት አለበት፡፡ የቃፊሩን ይሁንታ ያላገኘ ዜና አይታተምም ወይም አየር ላይ አይውልም ማለት ነው፡፡ ቃፊር ማለት በዕየለቱ የሚቀርቡ ዜናዎች ላይ ከፍተኛ ዋሳኔ የሚሰጡ ባለሙያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ቃፊሮች የዜናውን ጥሩነት የሚመዝኑት ደግሞ ከዜና መመዘኛ እሴቶች አንፃር ነው፡፡ ዜና በምታዳምጡበት ጊዜ በጣም ጆሮ የምትሰጡት ይዘቱ ምን ሲሆን ነው? የማታዳምጡትስ?
  • 19. 16 ነገር ግን እነዚህ እሴቶች በመጠቀም ዜናው በሚገመገምበት ሰዓት ከግምት ውስጥ የሚገቡ ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነዚህመም ሁኔታዎች 1. የሪፖርተሩ የጀርባ ታሪክና ልምድ 2. የብዙሃን መገናኛ ተቋሙ መስፈርት 3. የገበያ ሁኔታ 4. የአድማጭ ተመልካች ፋላጎት ናቸው፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ ሁኔታዎች ዜናን በዜና እሴቶች መሰረት የመመዘኑን ጉዳይ ተፅዕኖ ቢያደርጉበትም በአብዛኛው ግን የሚታዩት ከእሴቶች አንፃር ነው፡፡ እነዚህም እሴቶች እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ 1. የጉዳዩ ቅርበት (Proximity) ዜና በጂኦግራፊካል አቀማመጥ ወይም ለሰዎች ሥነ-ልቦና ቅርብ የሆነ ጉዳይ መሆን አለበት፡፡ አንድ ሁነት በዜና መልክ እንዲቀርብ ከሚያደርገው ነገር አንዱ የጉዳዩ ቅርበት ነው፡፡ የዜና ሁነቶች ለግለሰቦች ወይም ለአካባቢው የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡ አንዳንዱ ተፅዕኖ በቀጥታ ይሆናል፡፡ አካባቢያዊ ወይም ሃገራዊ ዜናዎች ለሌሎች የዓለም ክፍል ዜናዎች የተሻለ ተደማጭነት ወይም ተነባቢነት አላቸው ምክንያቱም የአድማጭ ተመልካች ቀልብና ሃሳብ መግዛት ስለሚችሉ እና ተገቢነትና ተፅዕኖ ስላላቸው ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሁነቶች የዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛን ትኩረት ይስባሉ፡፡ ያም የሚሆነው የጉዳዩን ዓለምአቀፋዊነት ሰፊ ስለሆነ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከአካባቢያዊ ወይም ብሔራዊ ዜናዎች በላይ ከአድማጮች ትኩረት አያገኝም፡፡ ምንም እንኳ ሉላዊነት እየተስፋፋ ቢሄድም ብዙውን ጊዜ ሰዎች ስለአካባቢያቸው መስማት ወይም ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ለምሳሌ ስለተፈጥሮ አደጋዎች፣ ምርጫ፣ ሽብርተኝነት፣ የልማት ወሬዎች፣ ወዘተ በአካባቢው አድማጭ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጥባቸዋል፡፡ እስኪ የሚከተሉትን ሁለት ዜናዎች አወዳድሩ፡፡ 1. አይ ሲ አይ ኤስ የተባለው የሽብር ቡድን በኢራቅና በሶሪያ የሚገኙ በርካታ ንፁሃን ዜጎችን ገደለ፡፡ 2. አል-ሸባብ በኢትዮጵያ ሱማሌ ድንበር መሸገ፡፡
  • 20. 17 ከነዚህ ሁለት ዜናዎች የትኛው ዜና የበለጠ ለኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት አድማጭ ተመልካች ትኩረት ይሰጠዋል? ለምን? አንዳንድ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ደግሞ የበለጠ ቅርብ የሚሆኑበት አጋጣሚ አላቸው፡፡ ለምሳሌ የነዳጅ ዋጋ መጨመር፣ የታላላቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኪሳራ፣ የአስከፊ ወረርሽኝ መከሰት፣ ወዘተ ናቸው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት የዓለማችን አንገብጋቢ ዜናዎችን መስራት የምንችለው ደግሞ ከአገራችን አውድ ጋር በማዛመድ ነው፡፡ ስለዚህ ዜናችን ተፅዕኖ መፍጠር እንዲችል ተገቢነት ያስፈልገዋል፤ ተገቢነት እንዲኖረው ደግሞ ቅርበት ሊኖረው ይገባል፡፡ በአጠቃላይ አንድ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለሚገኝ ግለሰብ መጀመሪያ ስለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፤ ከዚያም ስለጎጃምና አካባቢው፤ ቀጥሎ ስለአማራ፣ ስለኢትዮጵያና ስለአፍሪካ እያለ ስለተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ቢነገረው ትኩረት የመስጠት ሁኔታውም በየደረጃው ከፍ እያለ የሚሄድበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ 2. የባለጉዳዮች ታዋቂነት (Prominence) አንዳንድ ጊዜ ስም በራሱ ዜና የሚሆንበት አጋጣሚ አለ፡፡ ታዋቂ የሆነ ሰው ትልቅ ዜና መሆን ይችላል፡፡ ይኸውም የሚሰራው ሥራ ሳይሆን የሰራው ሰው ታዋቂነት መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ በቀላሉ የሚያውቃቸው ሰዎች የያዘ ዜና ተመራጭ ነው፡፡ ምክንያቱም በፖለቲካው፣ በስፖርቱ፣ በሙዚቃው፣ በመዝናኛው፣ በንግዱ ወዘተ ዘርፎች ታዋቂነት ያላቸው ሰዎችን ጉዳይ ለዜና መጠቀሙ የዜና መመዘኛ እሴቱን ስለሚጨምር ነው፡፡ ለምሳሌ፡ 1. አቶ አበበ ተሰማ አረፉ፡፡ 2. አትሌት ቀነኔሳ በቀለ ጉንፋን ይዞታል፡፡ የሚሉ ሁለት ዜናዎች ብትሰሙ የትኛውን ነው የበለጠ ጆሮ የምትሰጡት? መቼም የአቶ ናንቦኒ ሞት ከቀነኔሳ ጉንፋን የበለጠ ቢሆንም አቶ ናንቦኒ ምን እንደሆኑ ስለማናውቅ የቀነኔሳን ጉዳይ ነው ከፍተኛ ትኩረት የምንሰጠው፡፡ ስለዚህ የታዋቂ
  • 21. 18 ሰዎችን የስኬት፣ የውድቀት፣ አስተዳደግ፣ ውሎና አዳር፣ ሽንፈትና ድል እንዲሁም ውስጠ-ምስጢራቸውን ማወቅ ለሚፈልግ አድማጭ ተመልካች ያንን ይዞ መገኘት ትልቅ የዜና እሴት ነው፡፡ በዜና ውስጥ የታዋቂ ሰዎች ስም ካለበት ዜናው የዕለቱ ዜና ተደርጎ ይቀርባል፡፡ እስኪ የሚከተሉትን ሁለት አርዕስተ-ዜናዎች በማንበብ ቀጥለው ያሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡ 1. የሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ ሃይማኖቱን ቀየረ፡፡ 2. አቶ አበበ ከበደ ሃይማኖቱን ቀየረ፡፡ ከሁለቱ ዜናዎች የትኛውን ማዳመጥ ነው የምትፈልጉት? ለምን? በተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ አንዱን ዜና ከሌላው እንድናበላልጥ የሚያደርገን ምንድን ነው? 3. ወቅታዊነት (Timeliness) ዜናን ዜና የሚያሰኘው አዲስ ነገር ይዞ መገኘቱ ነው፡፡ በአገራችን የዜና ቋንጣ የለውም ይባላል፡፡ ይህም ማለት አንድ ድርጊት እንደተከሰተ ወዲያውኑ መደበኛ የሆኑ የጋዜጠኛ ጥያቄዎችን መመለስ ይጠበቅበታል፡፡ እነዚህም ጥያቄዎች በእንግሊዘኛ 5 W and H questions በመባል ይታወቃሉ፡፡  ምን ተከሰተ?  ማን ፈፀመው?  መቼ ተከፈተ?  የት ተከሰተ?  ለምን ተከሰተ? እና  እንዴት ተከሰተ? የሚሉት ናቸው፡፡ ስለዚህ ድርጊቱ በተከሰተበት ፍጥነት፤ ቴክኖሎጂው እስከፈቀደ ድረስ ዜና በፍጥነት ወቅቱን ጠብቆ መሠራት አለበት፡፡ የብሮድካስት ሚዲያ በተለይ ሬዲዮ በቀጥታ በቀላሉ ነገሮችን ለማስተላለፍ ይረዳል፡፡ ወቅታዊነት በብሮድካስትና በህትመት የብዙሃን
  • 22. 19 መገናኛዎች እኩል አይደለም፡፡ ምክንያቱም እንደብሮድካስት ሚዲያ በፍጥነት በህትመት ውጤቶች ላይ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡ ይኸውም የህትመት መውጫ ቀን መጠበቅንና ሁሉንም ሂደቶች ማለፍ ስለሚያስፈልግ ነው፡፡ ወቅታዊነት ማለት ዛሬ የሆነን ክስተት ብቻ መዘገብ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግ እስከዛሬ ድረስ ተደብቀው የተቀመጡ መረጃዎችን እንደተገኙ ማቅረብን ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ አሟሟት እስካሁን ድረስ ግልፅ የሆነ ነገር የለውም፡፡ ነገር ግን ከገዳዮቹ አንዱ አሁን ሊሞት ሲል የነበረውን ሂደት ቢናዘዝና መረጃ ቢወጣ ወቅታዊነትን አያዛባም፡፡ ከወቅታዊነት ጋር በተያያዘ ግን ቶሎ ብሎ ዜናን ለማቅረብ ያልተጣሩ መረጃዎችን ይዞ መውጣትም ይሁን ያልጠራ ፅሁፍ መስራ ተገቢ አይደለም፡፡ 4. ተፅዕኖ አድራጊነት (Impact) ተፅዕኖ ማት አንድ ስለአንድ ድርጊት የሚያትት ዜና ለህብረተሰቡ በሚሰጠው ጥቅም ያለው አንድምታ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ህብረተሰቡ ከዜናው በኋላ ድርጊቱን በተመለከተ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን ይኖርበታል ማለት ነው፡፡ ዜናው በሚያሳድረው ተፅዕኖ አማካኝነት ነው ክንውኖች የሚካሄዱት፡፡ ዜናዎች የሚታተሙት ወይም የሚሰራጩት ሊፈጥሩት የሚችሉት ተፅዕኖ ወይም ሊሰጡት የሚችሉት ፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ የብዙ ሰዎችን ህይወት የሚዳስስ ዜና በሰፊው ተፅዕኖ መፍጠር ስለሚችል ይዘገባል፡፡ ብዙ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ባሳደረ ቁጥር ብዙ ጠቃሚ እሴቶችን የያዘ ዜና ይሆናል፡፡ 5. አወዛጋቢነት (Controvesy) አንድ ጉዳይ የሥነ-ልቦና፣ የሥነ-ምግባር ወይም ግብረገብነት ላይ ውዝግብ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ውዝግቡ ደግሞ ከራስ ጋር፣ ከግለሰቦች ጋር ወይም ከቡድኖች ጋር ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ውዝግብ ደግሞ ዜናው ታትሞ ከወጣ ወይም አየር ላይ ከዋለ በኋላም የሚቀጥል ይሆና፡፡ በዚህም የተነሳ ዜናውን የተመረጠ ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም አወዛጋቢ ጉዳዮች በህይወታችን የተወሰነ ፋይዳ ስላላቸው ነው፡፡
  • 23. 20 ለምሳሌ፡- ሞሮኮ የ2015 የአፍሪካን ዋንጫ አላዘጋጅም አለች፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢቦላ ወረርሽኝ መስፋፋት ነው፡፡ በሌላ በኩል የአፍሪካ ዋንጫ ኮንፌዴሬሽን ውድድሩን የማታዘጋጅ ከሆነ ከፍተኛ የሆነ ቅጣት እንደሚጣልባት አስታውቋል፡፡ በዚህ ዜና ውስጥ ሞሮኮ ትክክል ናት አይደለችም፤ ኮንፌዴሬሽኑ ቅጣት ሊከብድ ይገባል ወይም አይገባም በሚል ለውይይት ይጋብዛል፡፡ በዚህም የተነሳ በርካታ ሰዎች ከግለሰብ እስከ ቡድን ደረጃ በሁለት ጎራ ተከፋፍለው ስለሁኔታው እንዲነጋገሩ መድረኩ ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ለመነጋገሪያ እንዲሆን ስለሚያደርግ አወዛጋቢነት አንድ ጥሩ የዜና እሴት ነው፡፡ 6. ተገቢነት (Relevance) ተገቢነት ለቅርበት የተሻለ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ ቅርበቱ ሲጠብ ዜናው በአንድ ሃገር ውስጥ የተለያዩ ቡድኖች ፍላጎት ማሟላት ይሳነዋል፡፡ ለምሳሌ የምርት ማዳበሪያ ዋጋ መውረድ ለአርሶ አደሮች ጥሩ ዜና ነው፤ ተገቢነትም አለው፡፡ ለብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ባለሃብቶች ግን ተገቢነት የለውም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የብረታ ብረት ዋጋ ጭማሬ ለኢንዱስትሪው ባሃብቶች ተገቢ ሲሆን ለአርሶ አደሮች ግን ምንም አይደለም፡፡ ይህም የሚያሳየው የዜናዎች ጠቃሚነት በቅርበትና በተገቢነት የተወሰነ መሆኑ ነው፡፡ 7. ትንግርት (Uniqueness) የተለመዱ ሁነቶች ዜና ሊሆኑ አይችሉም፡፡ አንድ ክስተት ዜና ሊሆን የሚችለው ለተለመደው ወይም ሰዎች ከለመዱት ውጭ ያለ ነገር ይዞ መቅረብ ሲችል ነው፡፡ ይህም ማለት ልዩ የሆነና ያልተለመደ መሆን አለበት፡፡ የትም ቦታ ላይ ተከስቶ የማያውቅ ወይም አልፎ አልፎ የሚከሰት ወይ ብርቅ የሆነ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያም ዜና የሰዎች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ሳይሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የተለየና ስለ ተገቢነት ሲወራ ሁሌም መታወቅ ያለበት የማህበረሰቡ የተለያየ ባህርይና ፍላጎት ነው፡፡ ስለዚህ በአካባቢው የሚገኙ ተገቢ የሆኑ ማህበራዊ ፍላጎቶች ቅድሚያ በዜናው ውስጥ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
  • 24. 21 ያልተለመደ ሲሆን የዜናውን እሴት በመጨመር የአድማጭ ተመልካችን ቀልብ መግዛት ይችላል፡፡ ለምሳሌ፡- 1. አንዲት እናት ወንድ ልጅ በሠላም ተገላገለች፡፡ 2. አንዲት እናት አራት ወንድ ልጆችን በሠላም ተገላገለች፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ዜናዎች የበለጠ የዜና እሴት ያለው ሁለተኛው ነው፡፡ ምክንያም የሰው ልጅ አይቀሬ የሆኑ ጉዳዮች ልደትና ሞት የተለመዱ ሲሆኑ በነዚህ መካከል ግን ያልተለመዱ ሁኔታዎችን እንደ አራት ልጆች በሰላም መውለድ ዓይነት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ግን ዜና ይሆናል፡፡ 8. ሰብዓዊነት (Human Interest) ዜና የሰው ልጅ በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሌችም የህዝብ ጉዳዮች የሚነካካ ከሆነ ጥሩ ዜና ነው ማለት ነው፡፡ ወደ ሰው ያዘነበለ የአፃፃፍ ስልት የሚጠቀም ሲሆን ድርጊቶች ከሰው አኗኗር ጋር አያይዞ ይተነትናል፡፡ በዜናዎቹ ውስጥም የሰዎች ቦታ ከፍተኛ ነው፡፡ ዜና አስደሳች እሴት የሚኖረው ከሁሉም እሴቶች ጋር የሰብዓዊ ነክ ጉዳዮችን ይዞ መቅረብ ሲችል ነው፡፡ ለምሳሌ 1. በ 250 ሚሊዮን ብር የብረታ ብረት ፋብሪካ ተቋቋመ፡፡ 2. ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችል ፋብሪካ ተቋቋመ፡፡ ከነዚህ ሁለት ዜናዎች የበለጠ ሰው ሰው የሚሸት ሁለተኛው ስለሆነ ከፍተኛ የሆነ እሴት አለው፡፡ ምክንያቱም የፋብሪካው ካፒታል ሳይሆን በዚያ ካፒታል የተቋቋመው ፋብሪካ ለማህበረሰቡ ምን ይፈይዳል የሚለው ስለሆነ ነው፡፡
  • 25. 22 9. ልብ ሰቀላ (Suspense) የዜና የልብ ሰቀላ ተፈጥሮ የድርጊቱን ጠቃሚነት የተወሰነ በማሳየጥ አድማጭ ተመነልካችን እያጓጉ እስከመጨረሻው ይዞ የመቆየት ተግባር ነው፡፡ ይህ ዓይነት አሰራር አብዛኛውን ጊዜ የተዋዙ ዜናዎች ላይ ይበዛል፡፡ ይህ የዜና እሴት ከሌሎች እሴቶች ጋር አብሮ የሚሄድ ሲሆን አድማጭን ስለአንድ ጉዳይ እርግጠኛ ሳይሆን እያዋዙና እያጓጉ እስከዜናው ፍፃሜ ድረስ ይዞ መቆየት ነው፡፡ 2.1.6 የዜና አላባውያን አንድ ዜና ተወዳዳሪና ኃላፊነት የተሰማው ለማድረግ በተሻለ አቀራረብ መቅረብ አለበት፡፡ ይኸውም አድማጭ ተመልካች በሚፈልገውና በሚጠብቀው መልኩ ቢቀርብ በጣም ተመራጭ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ዜና የሚሰራው ለይስሙላ ሳይሆን የያዝነውን መረጃ በትክክለኛ መልኩ በመቅረብ ነው፡፡ ለአድማጭ ተመልካች ጥሩ ጣዕም ያለው ዜናን ለማዳረስ መካተት ያለባቸው አስፈላጊ ንጥረ-ነገሮች ሊሟሉለት ይገባል፡፡ እነዚህ የዜና ቀመሞች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. እውነትነት (Accuracy) 2. ሚዛናዊነት (Objectivity) 3. ምልዑነት (Completeness) 4. ግልፅነት (Clarity) 5. ምንጭን መለየትና መግለፅ (Source Identification and Attribution )
  • 26. 23 1. እውነትነት በጋዜጠኝነት የዕለት ተዕለት ሥራ ውስጥ እውነትን የመሻት ፍላጎት አስፈላጊ ነው፡፡ እውነት መናገር ደግሞ ለጋዜጠኝነት ሥራም ሆነ ለዜና ጥንቅር አልፋና ኦሜጋ ነው መርህ ነው፡፡ እውነትን መናገር ሁልጊዜ የዜና ተግባር መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን እውነት ያልሆነ መረጃን ማስተላለፍ ከፍተኛ የሆነ ችግር ያጋጥማል፡፡ አንድ እውነትን የገደፈ ዜና ከተሰራጨ የሚከተሉት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ፡፡  ታማኝነትን ያሳጣል  አድማጭ ተመልካችን ያሳጥል ወይም ምርጫቸውን እንዲቀይሩ ያደርጋል  አላስፈላጊ የሆኑ ብዥታዎችን ይፈጥራል ስለዚህ ከነዘህ እና መሰል ችግሮች መፈጠር በፊት ዜናውን የሚያዘጋጀው ጋዜጠኛ ጊዜ ወስዶ ያሉትን መጃዎች ደግሞ ደጋግሞ ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም የጋዜጣ ወይም የሬዲዮ ወይም ማንኛውም ዜና በተቻላቸው መጠን እውነት የሆነውን ነገር ነው መዘገብ ያለባቸው፡፡ እውነትነት መጓደል ከሁለት በኩል ሊከሰት ይችላል፤ ከፀሐፊውና ከመረጃ ምንጩ፡፡ በእውነት ላይ የተመሰረተ ዜና የማይሰሩ ጋዜጠኞች እንደመንስኤ የሚቆጠረው ደግሞ ትኩረት ባለመስጠር (በእንዝህላልነት)፣ በስንፍና፣ ባልተሟላ መረጃ፣ በተዛባ መረጃ እና በተባራሪ ወሬዎችና አሉባልታዎች ላይ ተመርኩዘው መስራታቸው ነው፡፡ ነገር ግን መታየት ያለበት በነዚህና መሰል መንስኤዎ ምክንያት እውነት ያልሆነ ነገር መዘገብ በጣም ከፍተኛ የሆነ ችግር መፍጠሩ ነው፡፡ እውነትነት ሚዛናዊነት ምልዑነት ግልፅነት ምንጭን መለየትና መግለፅ
  • 27. 24 2. ሚዛናዊነት ጋዜጠኞች እንደማንኛውም ሰው ናቸው፡፡ ስለሆነም ሙሉ በሙሉ ከአንድ ጉዳይ ፍፁም ነፃ እና የተገለሉ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ሚዛናዊ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም የመሆኑ ጉዳይ ጋዜጠኛው ሥራውን ሲሰራ ከራሱ የግል ስሜትና ጥቅም ተነሳስቶ ለራሱ በሚመቸው መልኩ መስራት ሳይሆን ጉዳዩን ከተለያየ አቅጣጫ መመልከት ይገባዋ፡፡ ብዙውን ጊዜ አንድን ጉዳይ ከተለያየ አቅጣጫ መመልከት ተገቢም አዋጭም ነው፡፡ ለምሳሌ ብዙ ሪፖርተሮች አንድን የፍርድ ቤት የችሎት ውሎ እንዲዘግቡ ቢላኩ ይዘውት የሚመለሱት መረጃ ሁሉም ተመሳሳይ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህም ማለት አንዳንዱ በምስክሮች ላይ ያተኩራል፣ ሌላው በተከሳሽ፣ ሌላው በከሳሽ፣ ሌሎች ደግሞ በአቃቢ ህጉ፣የተወሰኑት ደግሞ በጠበቃውና በዳኛው ላይ ያተኮረ ዜና ይዘው ይመጣሉ፡፡ ስለዚህ የውስንነት ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ ሚዛናዊ ለማድረግ መሞከር ተገቢ ነው፡፡ ጥሩ ልምድ ያካበቱ ሪፖርተሮች ከግል እይታቸው እና እምነታቸው ውጭ ዜና ይፅፋሉ፡፡ ይህም ሚዛናዊ ሆነው እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ጋዜጠኞች ፍትሃዊና ሚዛናዊ በሆነ መል ዜናን ካልሰሩ እውነትን ማዛባታቸው አይቀርም፡፡ እውነት ሲዛባ ደግሞ የአድማጭ ተመልካች እምነትን ማጥት ያስከትላል፡፡ ሰው መሆን በራሱ ራሳችንን ዜና ውስጥ ጨምረን እንድናስብ ቢያደርገንም እንኳ እንደጋዜጠኛ ግን ዜና በሚሰበሰብበት ጊዜ ነፃና ሚዛናዊ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ ሚዛናዊነት ከምንሰራው ሥራ ጋር በተያያዘ በሂደቶች ውስጥ የምናደርገው መንገድ እንጂ ዉጤቱ ላይ አይደለም፡፡ ለምሳሌ፡- መንግስትና ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እየጨቆኑ መሆኑን ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስታወቁ፡፡ በዚህ ዜና ውስጥ ከመንግስት፣ ከምርጫ ቦርድ እና ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በምናደርጋቸው ቆይታዎች በተመሳሳይና ሚዛናዊ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ነገር ግን ጋዜጠኛው የመንግስት ደጋፊ ወይም በመንግስት የሚዲያ ተቋም ውስጥ የሚሰራ ስለሆነ ብቻ የተቃዋሚዎችን ጉዳይ ከፀረ-ሠላም አካላት ወይም ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር አያይዞ መናገር ከጋዜጠኛ የማይጠበቅ ነው፡፡
  • 28. 25 3. ምልዑነት ዜና ከተለያየ አቅጣጫ ያሉትን ጉዳዮች በመያዝ ምልዑ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በጋዜጣና በመፅሔቶች ላይ ለሚወጣ ዜና ነገሮችን ከብዙ አቅጣጫ በማየት ማቅረብ ይቻላል፡፡ ምክንያቱም የጋዜጣውና የመፅሔቱ የህትመት ቀን እስኪደርስ ብዙ የማጣራት ተግባራት ማከናወን ስለሚቻል ነው፡፡ ይኸውም የሌሎች የህትመት ውጤቶችን፣ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዘገባዎችንና ትንታኔዎችን፣ በኢንተርኔት ለላይ የሚለቀቁ መረጃዎችን በማየትና የመረጃ ምንጮችን በማነጋገር የተጠናከረ ምልዑ ሥራ ይዘው መውጣት ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል በብሮድካስት ሚዲያ ሁሌም አወዛጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ነገሮችን አሟልቶ መቅረብ ይከብዳል፡፡ ምክንያቱም ብሮድካስት ሚዲያ በዋናነት ከጊዜ ጋር ስለሚሰራ ነው፡፡ ሚዛናዊነትና እይታ በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ በዜና ውስጥ ከተካተቱ ዜናው ምልዑ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ሁሌም ከሰዓት ጋር በተያያዘ ጉዳይ ግፊት ስላለ ፍጥነትና ቅልጥፍና ይፈልጋል፡፡ አንድ ዜና ምልዑ የሚሆነው እውነትና ሚዛናው ሲሆን ነው፡፡ ይህም ተግባራዊ የሚሆነው የጉዳዩን ባለቤቶች ከተለያየ ጎን ይዞ መቅረብ ሲቻል ነው፡፡ 4. ግልፅነት ዜና መዘገብ ያለበት አጭርና ግልፅ በሆነ መልኩ ነው፡፡ በተለይም ለብሮድካስት ሚዲያ መዘገብ ያለበት አንድ ጊዜ ተሰምቶ በቀላሉ ለአድማጭ ተመልካች በሚገባበት መልኩ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም የብሮድካስት አድማጭ ተመልካቾች እንደገና ደግመው የመስማት ዕድል የላቸውም ወይም ያልገባቸውን ነገር ከተለያዩ ነገሮች ላይ ለማጣቀስም ሆነ ለማሰብ ጊዜ ስለሚያስፈልጋቸው ያንን ሲያደርጉ ሌሎች ዜናዎች ስለሚያልፉ ነው፡፡ ስለዚህ ዜናው ግልፅና በቀላሉ ለአድማጭ ተመልካች የሚገባ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ለዚህ ደግሞ የዜናው ፀሐፊዎች የሚመርጧቸው ቃላትና የዓረፍተ ነገር አወቃቀራቸው ቀላልና ያልተንዛዛ መሆን አለበት፡፡ ይህም የአድማጭ ተመልካችን ሥራ ከማቅለሉ በላይ ዜናውን ተደማጭ ያደርገዋል፡፡
  • 29. 26 5. ምንጭን መለየትና መግለፅ ዜና በሚሰራበት ጊዜ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን እንጠቀማለን፡፡ እነዚህን የመረጃ ምንጭ ግን እየለዩ መጠቀም ከጥሩ ዜና የሚገኝ አላባ ነው፡፡ ስለዚህ የዜና ምንጮችን በግልፅና በአግባቡ መጠቀም ከጥሩ ዜና ይጠበቃል፡፡ የመረጃ ምንጭን በተመለከተ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይጠበቃል፡፡  ትክክለኛው የመረጃ ምንጭ ማን ነው?  የመረጃ ምንጩ ታማኝ ነውን?  የትኛው የመረጃ ምንጭ የበለጠ ታማኝ ነው? እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን ከመለስን የመረጃ ምንጫችንን ለየን ማለት ነው፡፡ ከዚያ ቀጥሎ እንዴት እንጠቀምበት የሚለው ጥያቄ መመለስ ነው፡፡ የመረጃ ምንጭ ሰዎች፣ ተቋማት ወይም የተለያዩ ሰነዶችና ዶሴዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ እውነትና ውሸቱን ለይተን ካየን በኋላ በምን መልኩ ልግለፃቸው (attribution) የሚለው ወሳኝ ነው፡፡ ለመረጃ ምንጮች መጠቀስም ሆነ ክብር መስጠት ተገቢ የጥሩ ዜና ጥንቅር አካል ነው፡፡ የመረጃ ምንጭን በአግባቡ መለየትና መጥቀስ የራሱ የሆነ ጥቅሞች አሉት፡፡ ከነዚህ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡  የዜናውን ታማኝነት ይጨምራል  የዜናውን ግልፅነት ያሳድጋል  የጋዜጠኞችን የህግ ጥያቄዎች ይከላከላል፡፡ ይህም ማለት የመረጃ ምንጩ ከተጠቀሰ ጉዳዩ የሚሆነው የምንጩ እንጂ የጋዜጠኛው አይደለም፡፡ የመረጃ ምንጮችን በምንጠቀምበት ጊዜ በብሮድካስትና በህትመት ዜና ጊዜ የአጠቃቀም ልዩነት አለው፡፡ ይኸውም በህትመት ዜናዎች እንደፈለግን በሰጡት መረጃ ፊት፣ መሃል፣ መጨረሻ ወይም እየተቀላቀለ መጠቀም ሲቻል በብሮድካስት ዜናዎች ግን ሁልጊዜም ከመረጃው በፊት መቀመጥ አለበት፡፡ ምክንያም ደግሞ ዜናው የሚፃፈው በንግግር መልኩ ስለሆነ ነው፡፡
  • 30. 27 2.2 የዜና ምንጮች 2.2.1 ዜና ከየት ይገኛል? የመረጃ ምንጭ ማለት ማንኛውም ግለሰብ፣ ድርጅት፣ ተቋም ወይም ቡድን በትክክል የተዋቀረ መረጃ ማቅረብ ወይም መስጠት የሚችል ነው፡፡ እነዚህ የመረጃ ምንጮች ከጋዜጠኛው ጋር በሚኖራቸው ጊዜ ስለድርጅታቸው ወይም ስለራሳቸው ትክክለኛ መረጃ የመስጠት አቅም ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በተመሳሳይ ሪፖርተሩም የመረጃ ምንጮችን አያያዝ በተመለከተ አግባብነት ያለው አካሄድ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህም ማለት በመረጃ ምንጩና በጋዜጠኛው መካከል መልካም ግንኙነት ሊመሰረት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ያለመረጃ ምንጮች የጋዜጠኛነትን የዕለት ከዕለት የሥራ እንቅስቃሴ የተሟላ ማድረግ ስለማይቻል ነው፡፡ በምዕራፍ አንድ የጋዜጠኝነት ትርጉም ላይ “መረጃን የሚሰበስብ፤ የሚያዘጋጅ፤ እና የሚያሰራጭ ባለሙያ በማለት ጋዜጠኝነትን መተርጎማችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የመረጃ ምንጮቻችን በአግባቡ ካልተያዙና ግንኙነቱ መልካም ካልሆነ ጋዜጠኛው የሚያሰባስበውም፣ የሚያዘጋጀውም ሆነ የሚያሰራቸው መረጃ አይኖርም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የጋዜጠኝነትን ሥራ ያቆመዋል ማለት ነው፡፡ መረጃ ለጋዜጠንነት ሥራ በተለይም ለዜና ሥራ ደም ነው፡፡ ጋዜጠንነት አንድ የተገነባ ሰው አድርገን ብንወስደው ዜናን ደግሞ እንደልብ ብንቆጥር መረጃው ደግሞ ደም ቢሆን ጋዜጠኝነት በህይወት እንዲኖር ዜና መንቀሳቀስ አለበት፤ ዜና ደግሞ ብቻውን መንቀሳቀስ ስለማይችል የግድ የሚያሰራጨው መረጃ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ የመረጃ ምንጮቻችን ተዘጉ ማለት ለጋዜጠኝነት የሚቀርብ መረጃ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡ የተጀመረው መልካም ግንኙነት ደግሞ ሁሌም መቀጠል አለበት፡፡ መቀጠል ብቻ ሳይሆን የመወያያ ጥያቄ 1. የመረጃ ምንጭ ምንድነው? 2. የመረጃ ምንጭ ከሪፖርተሮች ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት መሆን ይጠበቅበታል?
  • 31. 28 ተጠንክሮ መቀጠልም ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ በጋዜጠኛውና በመረጃ ምንጩ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሳደግ የሚከተሉት ተግባራት መከናወን ይገባቸዋል፡፡ ሀ. የተጀመረውን ግንኙነት ማጠናከር ለ. የመረጃ ምንጮቻችን ምስጢር መጠበቅ ሐ. ግላዊና ተቋማዊ ክብርንና ታማኝነት ማጠናከር መ. ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸውን መረጃዎች ማረጋገጥ፣ መመዘንና መጠቀም ሠ. ከምንጮች ጋር አብሮ የመስራት ችሎታን ማዳበር ረ. ሁኔታዎች በፈቀዱት መጠን ጓደኛነት መመስረትና ማጠናከር ከላይ በተዘረዘሩት ነገሮች ጋዜጠኞች የመረጃ ምንጭ መረባቸውን ማስፋፋት ይችላሉ፡፡ ሪፖርተሮች የአንድ የብዚሃን መገናኛ አምባሳደር መሆን አለባቸው ምክንያቱም እነሱ የሚወክሉትን ኃላፊነት ወስደው የሚንቀሳቀሱት የተቋማቸውን ህልውና ነው፡፡ ሪፖርተሮች ከመረጃ ምንጮቻቸው ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ምክንያት የብዙሃን መገናናው ህልውና ሊቋረት ወይም ሊቀጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኞች እንደአምባሳደርነታቸው ጤናማ የሆነ ግንኙነት የመመስረት፣ የማሳደግና የማጠናከር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ 2.2.2 የዜና ምንጮች ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ዜና ከተለያዩ ምንጮች ይገኛል፡፡ ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ ሀ. የሚዲያ ተቋሙ ሪፖርተሮች፡- ተቋማት በየቦታው የሚልኳቸውና የሚመድቧቸው ትርፍ ጊዜ ወይም የሙሉ ሰዓት ጋዜጠኞች መረጃን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ይኸውም የተመለከቱትን ነገር እንደዜና ምንጭ በመሆን መረጃን ለብዙሃን መገናኛ ተቋማት ያቀብላሉ፡፡ ለ. አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የዜና ማዕከላት አገልግሎቶች፡- ጋዜጦችና የብሮድካስት ተቋማት ዜናን ከተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ወይም የሃገር ውስጥ የዜና ማዕከል ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሃገር ውስጥ ዜናዎችን ከሃገር ውስጥ የዜና ማዕከላት ያገኛሉ፡፡ እነዚህም የዜና
  • 32. 29 ማዕከላትም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)በ እና ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል (ዋልታ) ናቸው፡፡ የውች ሃገር ዜናዎችን ደግሞ የቻይናው ሽንዋ፣ አጃንስ ፋራንስ ፕሬስ፣ ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርንሽናል፣ ፓን አፍሪካን ኒውስ ኤጀንሲ (ፓና)፣ ሮይተርስ፣ ወዘተ የሚጠቀሱ ዋና ዋና የዜና ምንጮች ናቸው፡፡ ሐ. ኔትወርኮች፡- ይህ በኢትዮጵያ የተለመደ ባይሆንም በበለፀጉ ሃገሮች ብዙ የብሮድካስት አገልግሎቶች መረጃን ከሚከፋፍሏባቸው ተቋማት በገመድ ወይም በካርድ አማካንነት አማካኝነት መረጃን የመውሰድ ሁኔታ ነው፡፡ ከዚህም በጠጨማሪ በኢንተርኮም (የውስጥ መስመር) አማካኝነት መረጃን ያገኛሉ፡፡ መ. ነፃ ጋዜጠኞች (freelancers)፡- እነዚህ ጋዜጠኞች ግለሰቦች ወይም በቡድን ተደራጅተው ለዜና የሚሆኑ መረጃዎችን እየሰበሰቡ ዜና በመፃፍ በውል ለብዙሃን መገናኛ ተቋማት የሚያሰራጩ ናቸው፡፡ ለሬዲዮ በፅሁፍና በድምፅ ሲቀርቡ ለቴሊቪዥን ደግሞ ምስሉን ጨምረው ያቀርባሉ፡፡ ሠ. ከመስሪያ ቤት የሚወጡ ዜናዎች (furnished news)፡- እነዚህ ዜናዎች የሚወጡት ከመስሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶች፣ ሲሆን በህዝብ ግንኙነቱ አማካንነት ይሰጣሉ፡፡ የሚዲያ ጥቆማና የፅሁፍ ስርጭት (ፕሬስ ሪሊዝ) የሚያካትት ነው፡፡ ይህ በአብዛኛው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ለደንበኞቻቸውና ለባለድርሻ አካላት የሚያሰራጩት የዜና ምንጭ ይሆናል፡፡ ረ. ኩነቶች፡- በየጊዜው የሚከሰቱና የሚካዱሄዱ ኩነቶች ለዜና ምንጭነተር ያገለግላሉ፡፡ የሚስቡና ያልተለመዱ ሲሆኑ ደግሞ የበለጠ የብዙሃን መገናኛን ቀልብ ይስባሉ፡፡ ለምሳሌ ጋዜጣዊ መግለጫ ጉባኤ፣ ምርቃት፣ ህዝባዊና ብሄራዊ በዓላት፣ አደጋዎችና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆችወዘተ እንደኩነትነታቸው የመረጃነ ምንጭ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ ሰ. ህዝባዊ ትዕይንቶች፡- በርካታ ህዝብ የሚሳተፍባቸው ህዝባዊ ትዕይንቶች የዜና ምንጭ ይሆናሉ፡፡ ሰላማዊ ሰልፎች፣ የተቃውሞ ሰልፎች፣ የድጋፍ ሰልፎች፣ ዘመቻዎች፣ ቅስቀሳዎች ዋና ዋና የህዝባዊ ትዕይት ዘርፍ ሲሆኑ የዜና ምንችነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡
  • 33. 30 2.2.3 የዜና ምንጮች አያያዝ መረጃ ምንጮችን በተገቢው መንገድ መያዝ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የመረጃ መ፣ንጮች ስማቸው እንዳታወቅ የሚፈልጉ፣ ማንነታቸው እንዳይታወቅ የሚፈልጉ ወይም ደግሞ ስማቸውንና ማንነታቸው በሚስጢር እንዲያዝላቸው የሚፈልጉ፣ ድምፃቸውና ምስላቸው እንዳይቀረፅ የሚከለክሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን የመረጃ ምንጮች እንዴት መጠቀም እንዳለበት የሚያውቅ ጋዜጠኛ ደግሞ በሥራው ከፍተኛ ትርፍ ያገኛል፡፡ መረጃ መስጠት የማይፈልጉ (reluctant) ምንጮች ሰዎች መረጃ ከመስጠት ለምን ወደኋላ ይላሉ? ብዙውን ጊዜ ሰዎች መረጃዎችን የማይሰጡት በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡  በአለቆቻቸው በኩል የሚደርስባቸውን እርምጃና ከሥራ መፈናቀል በመፍራት  ከህዝብ ግንኙነት ዌም ከቃል አቀባዩ መረጃውን እንዲሰሙ ስለሚፈልጉ  ከዚህ ቀደም በሌላ ጋዜጠኛ በሥርዓት ሳስተናገዱ በመቅረታቸው ምክንያት ላለመተባበር በመወሰናቸው  የሚሰጡት አስተያየት ዌም መረጃ ጠቃሚ መስሎ ስለማይታያቸው እነዚህን ምክንያቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት ጋዜጠኛው ለመፍታት የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ይመቀማሉ፡፡ ከነዚህ ስትራቴጂዎች መካከልም የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡  መረጃ በመስጠታቸው ምክንያት ምንም ዓይነት ችግር እንደማይደርስባቸው የማሳመን ሥራ መስራት  ጥያቄውን ከሚመለከተው አካል እንደጠየቁ በመንገር የተገኘውን መረጃ ለማረጋገጥ ብቻ እንደምናናግራቸው በመንገር ማሳመን  መረጃ እያላቸው መረጃ መስጠት የማይፈልጉ ሰዎች ቢኖሩ ምን ታደርጋላችሁ?  መረጃውን ሰጥተው ማንነታቸው እንዳይገለፅ የሚፈልጉትንስ?
  • 34. 31  ከአሁን በፊት ስላስቀየማቸው ጋዜጠኛ ይቅርታ በመጠየቅ የራስን ስብዕና ማስረዳት  ምንጮች የነሱ መረጃ ጠቃሚ መስሎ ካልታያቸው በጣም ጠቃሚ የሆነ መረጃ እንሱ ጋ እንደሚገኝ ሌለ፤ ሰው ላይ ያንን መረጃ ማግኘት እንደማይቻል በማሳመነን መረጃ እንዲሰጡ ማድረግ ማንነታቸው እንዳታወቅ ወይም በሚስጥር እንዲያዝላቸው የሚፈልጉ (Anonymity & Confidentiality) ምንጮች አንዳንድ የመረጃ ምንጮች ማንነታቸው እንዳታወቅ ወይም በምስጥር እንዲያዝላቸው በመረጃ መስጠት ሂደቱ መጀመሪያ፣ መሃል ላይ ወይም መጨረሻ ላይ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ይኸውም መረጃውን ሲሰጡ የነሱን ማንነት እንዳይገለፅ ሲፈልጉ ጋዜጠኛው ቃል እንዲገባ ያደርጋሉ ወይም ይጠይቃሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚሰጡትን መረጃ በጣም ጠቃሚ ስለሚሆን በስማቸውና ማንነታቸው አለመገለፅ ላይ ከጋዜጠኛው ጋር መስማማት አለባቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ዓይነት የዜና ምንጮችን ለመጠቀም እንዴት መያዝ አለባቸው ለሚለው የሚከተሉት መንገዶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ 1. ለሚጠይቁት ጥያቄ ውል በመስጠትና ቃል በመግባት ማረጋገጥ 2. እዲቀረፁ በማግባባት አስተያየታቸውን ለመጠቀም ማሳመን 3. በመቃወም እነሱን ትቶ በመሄድ ሌለላ የሚቀረፅ ሰው ፈልጎ በመቅረፅ መጠቀም እነዚህን አማራጮች በምንወስድበት ጊዜ የሃገሪቱን ህግና አዋጆች ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን የተለያዩ ሃረጎችን በመጠቀም ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉትን የመረጃ ምንጮች እንደአማራጭ እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ለምሳሌ፡-  ለከንቲባ ቅርብ የሆነ ምንጭ እንደተናገረው…….  ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ አንድ የቢሮው ሠራተኛ እንደገለፁት…  አንድ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካል እንዳሉት….. ብዙውን ጊዜ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምንጮችም ቢኖሩ መረጃው በመቅርፀ- ድምፅ እንዳይቀረፅ የሚፈልጉት ግን በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ መረጃ እንዳይቀረፅ የሚፈልጉትን ምንጮች በዜና ውስጥ በቀጥታ ጥቅስ ሳናስገባ በፅሁፉ ውስጥ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡ ጋዜጠኛው ስማቸውንና ማንነታቸውን
  • 35. 32 ላለመግለፅ ከተስማማ ደግሞ ስምምነቱን ማክበር ይጠበቅበታል፡፡ ምክንያቱም ቃላችንን ካላከበርነ ሌላ ጊዜ በፍፁም መረጃ ማግኘት ላይቻል ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ጋዜጠኝነት የአንድ ቀን ሥራ ስላልሆነ የጋዜጠኝነት ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳዋል፡፡ 2.2.4 መረጃ እንዴት ይገኛል?  መረጃ እንዴት ይገኛል?  በየትኛው መንገድ የተገኘ መረጃ ነው ለሚዲያ ፍጆታ የሚውለው? መረጃን በተለያየ መንገድ እናገኛለን፡፡ ለዜና ግብዓት የሚሆነንን መረጃ ደግሞ የምንፈልገው ሠላማዊ በሆነ መንገድ ነው፡፡ አስገድዶ እየደበደቡ መረጃን ማግኘት የጋዜጠኝነት ሥራ አይደለም፡፡ ስለዚህ የጋዜጠኛ ሁነቶችን፣ ሁኔታዎችን፣ ዝግጅቶችን በመመልከት ቃለመጠይቅ በማድረግ እና የራሱ የሆነ ጥናትና ምርምር በአንድ ጉዳይ ላይ በማድረግ መረጃን ይሰበስባል፡፡ እነዚህ መንገዶች በውስጣቸው የተለያዩ ቴክኒኮች አሏቸው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ እያንዳዳቸውን አንድ በአንድ እንመለከታለን፡፡ ሀ. ምልከታ በአንድ ጉዳይ ላይ የተሻለ ሽፋን ለመስጠት ተመራጩ መንገድ ቦታው ድረስ በመሄድ መመልከት (Observation) ነው፡፡ ምልከታ በጋዜጠኝነት ሥራ ውስጥ የዕለት ተዕለት ተግባር መሆን ያለበት የመረጃ መሰብሰቢያ መንገድ ነው፡፡ ጋዜጠኛው በቦታው ተገኝቶ ሁኔታዎችን መመልከት ካልቻለ የአንድ ዜና ጥንቅር ምልዑነት አስተማማኝ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት በሌሎች መንገዶች የሚሰበሰቡትን ጉዳዮች በዓይን ተመልክቶ የማረጋገጥ ወይም ደግሞ ውድቅ የማድረግ ሥራዎችን ለማድረግ ተጨማሪ ኃይል ስለሚሰጥ ነው፡፡ “ማየት ማመን ነው” እንደሚባለው በዜና አሰባስባችን ውስጥ ቦታው ድረስ በመሄድ መመልከት የራሱ የሆነ ጥቅምና ጉዳት አለው፡፡ አንድን ጉዳይ ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት የሚያስገኛቸው ጥቅሞች፡-  ሁኔታዎችን በቀላሉ ለመረዳት  ጉዳዩን በቅርበት የበለጠ ለማረጋገጥ
  • 36. 33  ከሚታየው ነገር ባሻገር ስላለው እውነት ለማወቅ  ሠው በንግግር ሊገልፃቸው የማይችሉ ጉዳዮችን ለማግኘት ዕድል ይሰጣል  ከባለጉዳዮች ጋር ቅርርብ መፍጠር ስለሚችል… ወዘተ በሌላ በኩል አንድን ጉዳይ ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት ያሉት ጉዳቶች፡  ከፍተኛ የሆነ ወጪ ይጠይቃል (የማቴሪያል፣ የገንዘብና የጉልበት ወጪ)  ጊዜ ይፈጃል  ወደ ቦታው ለመግባት አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መጋፈጥ ይጠይቃል  ከጉዳዩ ባለቤቶች የሚደርሱ ክልከላዎችና ማስፈራሪያዎች ወዘተ ይገኙበታል፡፡ ምንም እንኳ አንድን ጉዳይ ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት የራሱ የሆነ ጥቅሞችና ጉዳቶች ቢኖሩትም ስለጉዳዩ ምልዑ የሆነ መረጃ ለመሰብሰብ መድረክ ስለሚከፍት ተመራጭ መንገድ ያደርገዋል፡፡ ለምሳሌ፡- በቦረና አካባቢ 4.5 ሚሊዮን ህዝቦች ተርበዋል የሚል ወሬ ሰምታችሁ የመረጃ ምንጫችሁ ምናልባትም የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡትን መግልጫ ጉባኤ ከአዲስ አበባ ብትከታተሉ ወይም ከቦረና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሚልከውን ጋዜጣዊ መግለጫ ፅሁፍ እንደምንጭ ብትጠቀሙ ምናልባት የጉዳዩን ሁለትከመቶ እንኳን በሚገባ መረዳት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም የጉዳዩን አስከፊነት ሠዎች ከሚነግሯችሁ በላይ ቦታው ድረስ ሂዳችሁ ብትመለከቱ የበለጠ መረዳት ስለምትችሉ ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ አስር ሰዎች ሞተዋል ሲባል መስማትና አስር ሰዎች በረሃብ አለንጋ ተገርፈው ቆዳቸው ከአጥንታቸው ተጣብቆ ሲሞቱ ማየት ለጋዜጠኛ የበለጠ ትርጉም የሚሰጠው የትኛው እንደሆነ የታወቅ ነው፡፡ የምልከታ ዓይነቶች መረጃን ቦታው ድረስ ሄዶ መመልከት ከድርጊቱ ድግግሞሽና ሂደት አንጻር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነሱም በተለያዩ ክፍሎች የአንድ ጊዜ ምልከታ (Episodic Observation) እና ሥርዓታዊ ምልከታ (Systematic Observation) ተብለው ነው፡፡ የአንድ ጊዜ ምልከታ የሚደረገው በተከታታይ በተጠናና በተደራጀ መደበኛ በሆነ መልኩ ሳይሆን በኢ-መደበኛ ድንገት ቦታው ላይ በመገኘት የሚከናወን ነው፡፡ ሥርዓታዊ ምልከታ ደግሞ
  • 37. 34 መደበኛ በሆነ መልኩና በተደራጀ አካሄድ የሚደረግ ነው፡፡ እነዚህን የምልከታ ዓይነቶች በውስጣቸው የተለያዩ የምልከታ ዓይነቶች ይዘዋል፡፡ የአንድ ጊዜ ምልከታ የአንድ ጊዜ ምልከታ በራሱ ሶስት የተለያዩ የምልከታ ዓይነቶችን አካቷል፡፡ እነሱም ሀ. ልማዳዊ ምልከታ (Conventional Observation) ለ. ድብቅ ምልከታ (Unobtrusive Observation) ሐ. አሳታፊ ምልከታ (Participant Observation) እነዚህ ሶስቱ የምልከታ ዓይነቶች አንድ ድርጊት ሲፈጸም ወይም ክስተት ሲከሰት ቦታው ላይ በመገኘት የሚከናወኑ የምልከታ ዓይነቶች ናቸው፡፡ ሀ. ልማዳዊ ምልከታ ልማዳዊ ምልከታ አሳታፊ ያልሆነ የምልከታ ዓይነት ሲሆን የማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን ለማጥናት ወይም አሳታፊ ባልሆነ መልኩ መረጃን ለመሰብሰብ ያገለግላል፡፡ የህብረተሰብ ሳይንስ ባለሙያዎች የሰዎችን ባህርይ ለማጥናት ይህንን የምልከታ ዓይነት ይጠቀማሉ፡፡ ጋዜጠኞችም የህብረተሰብ ሳይንስ አካል እንደመሆናቸው የሰውን ባህርይ ለማጥናት ልማዳዊ በሆነ፤ ራሳቸውን የድርጊቱ አካል ሳያደርጉ ይጠቀሙበታል፡፡ ልማዳዊ ምልከታ ስብሰባዎችን በምንከታተልበት፣ ንግግሮችን ስናዳምጥ፣ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ስንመለከት፣ ኮንሰርቶችን ስንታደም፣ የጋዜጣዊ መግለጫ ጉባኤዎችን፣ የምርቃት መርሃ-ግብሮችን፣ ዓመታዊ በዓላትን ወዘተ በምንመለከትበት ወቅት የምንጠቀምበት የምልከታ ዓይነት ነው፡፡ ልማዳዊ ምልከታ ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው የመረጃ ምንጮች የጋዜጠኛውን መኖር እያወቁ ነው፡፡ ይኸውም የመረጃ ምንጮች በጋዜጠኛ እይታ ውስጥ እንደሆኑ እያወቁ ነው የሚካሄደው፡፡ የልማዳዊ ምልከታ ጠንካራ ጎኖች፡-  ጋዜጠኛው ሥነ-ምግባር ጠብቆ የሰዎችን ግለኝነት መብት ሳይነካ እንዲሰራ ያደርጋል፡፡
  • 38. 35  የመረጃ ምንጩ ጋዜጠኛው እንዲያይለት የሚፈልገውን ነገር በሙሉ ለማሳየት ይጥራል፣ ይኸውም የመረጃ አድማሱን ያሰፋዋል፡፡  ጋዜጠኛው ራሱን የጉዳዩ አካል ስለማያደርግ በተቻለ መጠን ነፃና ሚዛናዊ ሆኖ እንዲሰራ ይጠቅማል፡፡  ጋዜጠኛው የጋዜጠኛ የሥራ መሳሪያዎችን (ካሜራ፣ መቅርፀ- ድምፅ፣ ማስታወሻና ሌሎችንም) እንዲጠቀም ይረዳዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ልማዳዊ ምልከታ የራሱ የሆነ ድክመቶች አሉት፡፡ ልማዳዊ ምልከታ በአንድ የተወሰነ ጊዜ ውስጥ ውስን የሆነን እንቅስቃሴ ለማየት የሚደረግ ስለሚሆን በዋናነት በዛች ሰዓትም የመረጃ ምንጩ የጋዜጠኛውን መኖር እያወቀ በመካሄዱ ምክንያት የተለያዩ ድክመቶች አሉት፡፡ የጋዜጠኛውን መኖር ስለሚያውቁ ትክክለኛ ሥራቸውንና ሰብዕናቸውን እንዲደብቁ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ጋዜጠኛው የመረጃ ምንጩ በወቅቱ በሚያሳየው ነገር ላይ እንዲወሰን ያደርገዋል፡፡ ለምሳሌ፡- የአባይ ግድብን ለመመልከትና ስለግድቡ መረጃ እንዲኖረን የሥራ ኃላፊዎችን ማግኘት ስላለብን የምናገኘው በልማዳዊ ምልከታ ነው፡፡ ለ. ድብቅ ምልከታ ድብቅ ምልከታ እንደልማዳዊው ምልከታ በአንድ የተወሰነ ቦታ ተገኝቶ አንድን ጉዳይ ለተወሰነ ጊዜ መመልከት ሲሆን ብዙውን ጊዜ ሪፖርተሮች አንድ አዲስ ነገር ከተከሰተ ብቻ የሚያደርጉት ነው፡፡ በልማዳዊው ምልከታ የሪፖርተሩን መኖር በመረጃ ምንጮች የታወቀ ስለሚሆን ምንጮቹ ከመደበኛው ባህርያቸው ውጭ የሆነ ተግባርና እንቅስቀቃሴ ስለሚያሳዩ ትክክለኛ ማንነታቸውን ማወቅ ስለማይቻል የድብቅ ምልከታ ይከናወናል፡፡ የድብቅ ምልከታ በዋናነት የመረጃ ምንጩ ሳያውቅ በድብቅ በመግባት መረጃ ሰብስቦ የመውጣት ሂደት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ ህፃናትን በጉዲፈቻ አሳድጋለሁ የሚል ሰው ሴት ህፃናትን ወደቤቱ እያስገባ የመድፈር ሥራ ቢያደርግ ሰውየውን በልማዳዊ መንገድ ለመከታተል ቢሞከር ልጆቹን ሲደፍርም ሆነ ሲያሰቃያቸው ማየት አይቻልም፡፡ ሰውየው በተቻለ መጠን ልጆቹን በአባትነት ስሜት ሲንከባከባቸው ነው የሚታየው፡፡ ስለዚህ በቤት ሠራተኛ ወይንም የጥበቃ ሠራተኛ አማካኝነትና
  • 39. 36 እርዳታ ተደብቆ በመግባት መመልከት ይገባል፡፡ ስለዚህ የሰዎችን ድብቅ ማንነት በድብቅ በማየት የህፃናቱን መደፈር መረጃ መሰብሰብ ይቻላል፡፡ የድብቅ ምልከታ የራሱ የሆነ ጥቅምም ተግዳሮትም አሉት፡፡ ጥቅሞችን በምናይበት ጊዜ በልማዳዊ ምልከታ ማግኘት የማንችለውን መረጃ ማግኘት ያስችላል፡፡ ስውር ሴራዎችንና የተደበቁ ወንጀሎችን ለማጋለጥ ይረዳል፡፡ በሌላ በኩል ግን የመረጃ መሰብሰቢያ የሆኑ ቁሳቁሶችን (የቪዲዮ ካሜራ፣ የፎቶግራፍ ካሜራ፣ ማይክራፎን፣ መብራት፣ መቅርፀ- ድምፅ፣ ማስታወሻ ወዘተ) መያዝ አስቸጋሪ ተግዳሮት ነው፡፡ ይህም የምንመለከተው ሰው እንዳያውቅ ከሚደረገው እንቅስቃሴ ጋር ጋዜጠኛው መደበቅ ስላለበት በስውር ስለሚገባና ስለሚወጣ እነዚህን ነገሮች መጠቀም አያስችልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመረጃ ምንጭን የግለኝነት መብት በመጣስ የጋዜጠኝነት ህግና ሥነ-ምግባር መተላለፍ እንደተግዳሮት ይወሰዳል፡፡ ሐ. አሳታፊ ምልከታ አሳታፊ ምልከታ አንዳንድ ጊዜ “ራስህ ስራው” ምልከታ በመባል ይታወቃል፡፡ ይኸውም ጋዜጠኛ በጉዳዩ ውስጥ ራሱን አስገብቶና የጉዳዩ ተሳታፊ በመሆን መረጃን የሚሰበስብበት መንገድ ስለሆነ ነው፡፡ በአሳታፊ ምልከታ የጋዜጠኛውን መኖርና አለመኖር የመረጃ ምንጮች ሊያውቁም ላያውቁም ይችላሉ፡፡ የመረጃ ምንጮች የጋዜጠኛውን መኖር ካላወቁ የምስጢር ተመልካች (Undercover Observer) ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ የምስጪር ተመልካች ከድብቅ ምልከታ የሚለይባቸው የራሱ የሆኑ መንገዶች አሉት፡፡ የምስጢር ተመልካች የጋዜጠኛው መኖር ባይታወቅም ከሚመለከተው ጉዳይ ውስጥ ራሱን በማስገባት ይሳተፋል፤ በድብቅ ምልከታ ግን ጋዜጠኛው ተሳታፊ አይደለም፡፡ ስለዚህ አንድ ጉዳይ ውስጥ ጋዜጠኛው ራሱን አስገብቶ ለመመልከት ጋዜጠኛ መሆናችንን እና አለመሆናችንን ለመግለፅ የሚወሰነው በጉዳዩ ክብደትና ቅለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ሌላ ሃገር የሚያጓጉዙ ደላላዎችን በተመለከተ መረጃ ለመሰብሰብ እንደ አንድ ተጓዥ ስደተኛ ሆነን ልንገባ እንችላለን፡፡ በዚህ ጊዜ የእኛን ማንነት ደላላዎች ካወቁ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማወቁ ቀላል ነው፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ደብቀን ምስጢራዊ ተመልካች እንሆናለን ማለት ነው፡፡