SlideShare ist ein Scribd-Unternehmen logo
1 von 4
Downloaden Sie, um offline zu lesen
በማተብዋ ልዳኝ - ወድቃ የተነሳችው
(ከስንሻው ተገኘ)
ወደ ትዝታ ዓለም ወደ ትዝታ ጊዜ በትዝታ ሰረገላ ልወስዳችሁ ነው። እኔ እንኳ በአጻጻፌ አበባዊ ቋንቋ አልወድም። ለማንኛውም ግን
አብረን እንድንነጉድ እጋብዛችኋለሁ። ወደ እንግሊዝ አገር! 1953 እ.አ.አ ወደ አንድ የለንደን ስብሰባ አዳራሽ እንገባለን። እንግዶች የነፃነት
ታጋዮች ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት የዌስት ኢንዲስ ተወላጅና የዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ንቅናቄ መሪ የሆነው ጆርጅ
ፓድሞን በአዳራሹ ውስጥ ፕሪዚደሙን ለብቻ ይዞታል። የእኔንና የእርስዎን ቡጢ (ጭብጥ) የሚያህል ወፍራሙን ትምባሆ (ቶስካኖ)
ጐርሶአል። ጐርናና ድምፁ ሰውንም አዳራሹንም የሚቆጣጠር ዓይነት ነው። ከአፉ የሚወጣው ጢስ በአካባቢው አንዳች ዓይነት ጉም
ሠርቶአል። በመካከሉ የሚያሰማው ባለ ግርማ የሆነው ሳሉ ለሰውየው ተጨማሪ ክብር አሸክሞታል።
“ ክቡራትና ክቡራን! አዳራሹ ተከፍቶ ንግግር የሚያደርጉት የአፍሪካ ነፃነት ንቅናቄ መሪዎች ወደ ውስጥ ይዝለቁ!” ጆርጅ ፓድሞን ትእዛዝ
ሰጠ። አዳራሹ ደግሞ ከግድግዳ እስከ ግድግዳ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆአል። በአራቱም ማዕዘናት ቄንጠኛ በሆኑ ረዣዥም
ሰንደቆች ላይ ወርቃማና ቀለማማ በሆነ መደብ ላይ በጉልህ የሚታዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዎች አሉ። ትርኢቱ እንባ ካልጋበዘ ስሕተቱ
የኔ ነው። ደካማ ጋዜጠኛ ሰነፍ ጸሐፊ….
አዳራሹ ተከፈተ። የማኦማኦ ንቅናቄ መሪ ወጣት የማይመስሉት ጆሞ ኬንያታ ብቅ አሉ። በደረታቸው ላይ የቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ ምስል
ያለበት ፒን አድርገዋል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንደ ሻሽ አድርገው በራሳቸው ላይ ጠምጥመውታል። ቀጥል። የጐልድኮስቱ (በኋላ
ጋና) የነፃነት ግንባር መሪ ካዋሚ እንኩሩማህ- ፈርጠም ያለ…ደልደል ያለ..ተክለ ሰውነታቸው ጉልህ የሆነ አርበኛ። ሰንደቅ ዓላማውን
በሙሉ ለብሰውታል። የጃንሆይን ምስል ደግሞ በግራ ኮታቸው ክሳድ ላይ ሰክተውታል። ሑፍዌ ቩዋኘ (ኮትዲቮር) ሔስቲንግስ ባንዳ
(ማላዊ) ወዘተ ተራ በተራ መጡ። ከመካከላቸው ጐፈር በራሳቸው ላይ ያደረጉ….በእጆቻቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ
የጃማይካ፣ የደቡባዊ አፍሪካ ታጋዮች ነበሩ። በብዙ ቁጥር። ሁሉም በመንፈስ ኢትዮጵያዊ ነበር። ያ ዘመን ደግሞ በትውልዱ ጃማይካዊ
የነበረው ማርከስ ጋርቪ (Black nationalism and Pan-Africanism)ን እንዲሁም የራስ ተፈሪያኒዝምን ፍልስፍና የሚያስፋፋበት
ነበር። የሁሉም አገር - ነፃነትዋን ለሺህ ዓመታት አስከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ናት። ዓይናችሁን ጨፍኑና ጊዜን አጣጥፋችሁ ወደዚያ
ዘመን (1952-53) ብረሩልኝ። መጀመርያ ስለዚህ ጉዳይ ዴቪድ ሜሬዲት The first dance of freedom ን መጽሐፍ አነበብሁና
(በ1985) ወዲያው እጅግ ወዳጄ ለነበሩት ለልጅ ሚካኤል እምሩ አነሳሁባቸው። በወቅቱ በእንግሊዝ አገር ስለነበሩ በግል በትኩረት
የሚያውቁት መሆናቸውን አረጋገጡልኝ። ከላይ ያቀረብሁት ዘገባም የማርቲን ሜሬዲትና የልጅ ሚካኤል እምሩ ጭምቅ ሪፖርት ነው።
(ልጅ ሚካኤል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ላይ ወደ እንግሊዝ አገር ከሄዱ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ።)
የወቅቱ ተራማጅ ሁሉ ይህንን በጽሞና ሲከታተል ኋይት ሖል (የእንግሊዝ መንግሥት) በዚያው ሰሞን (1953) በኢትዮጵያና አንድነትዋ
ላይ ትልቅ ሴራ ሲያቀጣጥል ነበር። ሊቆራርጠን። አርነስት ቤቪን የተባለው የሌበር ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶማሊያ ነፃ ስትሆን
የኢትዮጵያን ኦጋዴን፣ ሪዘርቭድ ኤርያና - ሐውድ እንዲሁም ጅቡቲንና የኬንያን ሰሜናዊ ምዕራብ ግዛት አጠቃልላ ታላቅዋን ሶማሊያ
ስትመሠርት በሌላ በኩል ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ ከአለውሀ ባሻገር ያለው መሬት በሙሉ (ማለትም ትግራይና ኤርትራ ተዋህደው
ትግራይ ትግርኝ የሚባል አገር ለመፍጠር ሽርጉድ ይዘው ነበር።) lyndon larouche የተባለውና በመደበኛው አስተሳሰብ አክራሪና
የተወናበደ የፖለቲካ ነውጠኛ የአገሩን ፖለቲካ ጨረሰና ዛሬ በመላው ዓለም እየደረሰ ያለው ችግር እንግሊዝ ዘርታ ያበቀለችው አድርጐ
ነው የሚያቀርበው። ይኽ አይጠረጠርም። በበኩሌ እንደማውቀው እንግሊዙ አርነስት ቤቪን የጀመረውን አይኤም ሌዊስ ካልፈጸምሁት
ብሎ እነ በረከት ሀብተ ሥላሴን፣ እነ መለስ ዜናዊን ይዞ ለዓመታት ተንደፋድፎአል። (መለስ በዜግነት ሶማሊያዊ ነበር)- በነገራችን ላይ እነ
በረከት ሀብተሥላሴ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ ተወልደው ያደጉባት፣ ተምረው የተሾሙባት ኢትዮጵያ፥ ዓለማቸውን ያዩባት ውብ አዲስ አበባ-
ወደ ኢምንትነት እንድትመለስ ሲፍጨረጨሩ እንደ ራስ ተፈሪ ያሉ ሕዝቦች “ቤታችን መግቢያችን (ራስታ የምንላቸው)” በማለት
ወደዚያች አገር መጉረፍ ይዘው ነበር።
ተመስገን ደሳለኝ ወደ ጐንደር ሄዶ ነበር አሉ። ባዶ እጁን አልተመለሰም። ወያኔ ያነወራት፣ እንደ ተስፋዬ ሐቢሶ ያሉ (በተቆላበት
የሚያፈሉ) ሰነፎች የተሳለቁባት፣ በመንፈሳዊና ሕዝባዊ ክብርዋ መለስ ያሾፈባት፣….ወያኔዎች በባዶ እግራቸው የረጋገጡአትና የኮሾሮ
(የአምባሻ) መያዣ ያደረጉአት….በእኔ ዕድሜ ጅማሬ ላይ “ወድቃ የተነሳችው” እየተባለች ስትጠቀስ የቆየችው ሰንደቅ ዓላማ በጐንደር
ምንኛ ታላቁን ክብርዋን ይዛ - እንዳለችና እንደምትኖር የምሥራቹን ነግሮናል። ብሥራት ነውና ምሥር ብላ! ለዚህ ጽሑፍ ያነሳሳኝ ይኸ
ወጣት ጋዜጠኛ ነው።
ኢጣሊያ የኤርትራን ደጋማ አውራጃዎች ለመያዝ የቻለችው በ1889ዓ.ም እንደ አ.አ ነው። እዚህ ላይ የንጉሠ ነገሥቱን (አጤ ዮሐንስ)
አጐት ራስ ደበብንና በኋላ ጊዜ የራስ ሥዩምን ሴት ልጅ ያገቡትን ደጃዝማች ገብረሥላሴን ማውገዝ ወይስ ማወደስ ይገባ እንደሆነ
አላወቅንም እንጂ በእነሱ ድጋፍና መሪነት ነው ኤርትራ የተያዘችው። ዛሬ አኪሩ ዞሮ ባንዳ የሚወደስበትና የሚቀደስበት፣ ወደል ወደል
መጽሐፍም በውዳሴ መልክ የሚቀርብበት በመሆኑ ነው ግራ የተጋባነው። አዎን ዓላማዬ በማንም ዜጋ ላይ የፍትሕ ድንጊያ ለመወርወር
አይደለም። የእግዜሩን መንገድ ካወቅነው ጸሎታችን “ማረን” እንጂ “አፈራርደን” መሆን የለበትም።
ኢትዮጵያን የሚታደጋት የራስዋ የኢትዮጵያ ልጅ መሆን እንደሚገባው ስንነጋገርና ስንስማማ ከቆየን በኋላ ሁሉም ነገር የተለዋወጠ
ሆኖአል። ኢትዮጵያውያን አገራቸውንም ራሳቸውንም ማዳን አቅቶአቸው በአገሪቱ የሚጫወቱት ወገኖች የተነሱለትን አጥፊ ዓላማ
ለመፈጸም አንዳች እንቅፋት አልገጠማቸውም። በተናጠል መስዋዕትነት የሚከፍሉ ግለሰብ የፖለቲካ ተዋናያውያንና ጋዜጠኞች ደግሞ
የሚሞቱለትን ሕዝብ ሊቀሰቅሱ አልቻሉም። ስለሆነም ኢትዮጵያ ያሉአት ልጆች እነዚህ ብቻ ናቸውን? እስከማለት የደረሱ አሉ።
“የኢትዮጵያ ልጆች በደማቸውም በአጥንታቸውም ኢትዮጵያን ከእልቂት ለማዳን ካልቻሉ ወዴት ይኬዳል? ወደ ማን ይጮኻል?” ነቢዩ
ዳዊት (ልበ አምላክ የሚባለው) ለዚህ አምላክ ራሱ በጆሮው የነገረው ቁም ነገር ነበር ይላሉ መጽሐፉን የሚተረጉሙ ሰዎች። “በልጆችዋ
መተማመን ያቃታት፣ ልጆችዋ በግፈኞችና በጨቋኞች ያለቁባት ኢትዮጵያ ናት፤ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር የዘረጋችው” ይሉናል። ተስፋ
ከመቁረጥ የመጣ አሳብ አይደለም። የአምላኩንም ሚና እንዳንረሳ ለማሳሰብ ነው። ውዳሴ ማርያምም ባይሆን ጥቂት እግዚኦታ!
እንደ ዛሬዋ ጐንደር ሁሉ ጣልያን ኤርትራን ከያዘ በኋላ ለስድሳ ዓመታት የኢትዮጵያ ነፃነት ምልክትና የክብርዋ ዘላለማዊ መግለጫ
የሆነችው አረንጓዴ፣ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በደብረ ቢዘን ቤተ ክርስቲያን አናት ላይ ስትውለበለብ ቆይታለች። እግዚአብሔር በቤቱ
(ቤተክርስቲያኑ) ላይ ያዋላት ለዚህ ሕዝብ መልእክት ኖሮት ይሆናል በማለት የገዳሙ አበምኔት በ1980 ገልጠውልኛል። በዚያን ዘመን
ኤርትራ በጣልያን ሥር ብትወድቅም በየበዓላቱ ሕዝቡ ይዞት የሚወጣው ሰንደቅ- አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። አንድ ኤርትራዊ ሲሞት
የአስክሬኑ ሳጥን በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ያሸበርቃል። ሠርጐች ግርማማ የሚሆኑት በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ሲንቆጠቆጡ ነው። አብያተ
ክርስቲያናት ይኽ ሰንደቅ ዓላማ ተለይቶአቸው አያውቅም። ለብዙ ዓመታት ወደ ኤርትራ ስመላለስ የኖርሁ፣ ሕዝቡን የማውቅና የማከብር
ስለነበርሁ ዛሬ ይኽ ወገኔ ከዚያች ከታቦት እኩል ከሚያያትና የሕልውናው ተስፋ ከነበረችው ሰንደቅ ዓላማ ሲለይ ምን ተሰማው? እያልሁ
ራሴን እጠይቃለሁ። ወይስ አዲሱ የኤርትራ ትውልድ ይኽንን ቁም ነገር አያውቀውም ነበር? እዚህ ባለሁበት አገር እንደኔው በስደት ላይ
የሚገኙ ኤርትራውያን አረጋውያን አውቃለሁ። ለሁሉም እንደ ቀልድ “አዲሱ ሰንደቅ ዓላማ የሚለመድ ነው?” እላቸዋለሁ። በሻዕቢያ
ውስጥ ከአሥርና ከአሥራ አምስት ዓመት በላይ መቆየታቸውን የሚነግሩኝ ብዙ ጐበዞችን በየቀኑ አገኛቸዋለሁ። ሁለቱ በአንድ ቀን
የአሜሪካ ዜግነት እንዳገኙ ሲነግሩኝ እንደ ቀልድ አድርጌ “አሜሪካዊ ለመሆን ነው ሰላሳ ዓመት የወጋችሁኝ?” እላቸዋለሁ።
ኤርትራውያኑ ራሳቸው በአጸፋው “እናንተስ ሰንደቅ ዓላማውን መቸ አስከበራችሁና ነው እኛን የምታሽሟጥጡን?” ሊሉን ይችላሉ።
እግዜር ይመስገን የወያኔ ሕግ በማይሰራበት በዋሽንግተን፣ በለንደን፣ በጄኔቫ…በስዊድን…የምናምንባት የእናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ
እንደ ልብ ትውለበለባለች። ስለዚህ ለኤርትራውያን ወገኖቻችንም “የተዋችኋትን ሰንደቅ ዓላማ በምትመለሱበት ጊዜም በዚያው ሞገስ
ታገኝዋታላችሁ” ለማለት ይቻላል። (የኢትዮጵያ ሕግ በማይሰራባቸው በስዊድን ወዘተ ስል እህታችን ብርቱካን ሚደቅሳ ትዝ ትለኛለች።
ለካንስ ስቶክሐልም ላይ የተናገሩት አዲስ አበባ ላይ ያስቀጣል?)
ከማንም በላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲያከብር የኖረው የኤርትራ ሕዝብ ነበር ስል ሌላው ሕዝብ ደንታ እንዳልነበረው መግለጤ
አይደለም። ግመሎቻችን፣ በጐቻችን፣ የጋማ ከብቶቻችን፣ የቤትና የዱር እንስሶቻችን አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የሆነውን የክብር ዓርማ
ያውቁታል እያሉ የሚያወጉአችሁ የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተወላጆች ብዙ ናቸው። የአውሳው ርእሰ መኳንንት ቢተወደድ አሊሚራሕ አንፍሬ
በአንድ ወቅት “እንኳን አፋሩ ሕዝባችን ግመሎቻችንም ሰንደቅ ዓላማችንን ያውቁታል” ማለታቸው ይጠቀሳል። አጋጣሚ ነገር ላንሳና
ኮማንደር ለማ ጉተማ የሐረርጌ ክፍለ ሀገር ዋና አስተዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ የመሥሪያ ቤቴን ቅርንጫፍ ሥራ ለማስተባበር ወደዚያ እመላለስ
ነበር። ሁለት ጊዜ ያህል የኢሳውን ባላባትና ሱልጣን ደጃዝማች ዑጋዝ ሐሰንን ተዋውቄአቸው ነበር። “ትልቁ ልጄን ትመስለኛለህ” ሲሉኝ
ልዩ ፍቅር አደረብኝ። ታዲያ በ1983 አካባቢ ቢትወደድ አሊ ሚራሕ የተናገሩትን ቃል በቃል ደጃዝማች (ዑጋዝ) ሐሰን ሲናገሩት
ሰምቻቸዋለሁ። ማጋነን ባይመስል ግመሎቹ ቀጥ ብለው እንደሚቆሙ ይናገራሉ። ጐበዝ! “ግመሎቻችን ለኢትዮጵያ ከእኛ የበለጠ ታማኝ
ናቸው” ብል በድፍረት ትወስዱብኝ ይሆን? ግመሎቻችን ጭምር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ያውቁታል! እነመለስ ከዚያች ቅርጽ የለሽ
እንስሳ ማነሳቸው ከተሰማችሁ አብሬአችሁ ልከሰስ እችላለሁ።
ፋሺስቶች ባላደረጉት ድፍረትና ብልግና በቀለም እኛን ይመስል የነበረው መለስ የሕገ መንግሥት ጉባዔ ሲመራ ያቺን ሰንደቅ ዓላማ እንዴት
እንዳብጠለጠለ ታስታውሳላችሁ። እዚያ ጉባዔ ውስጥ በጀግንነትና በታላቅ ወኔ ይቺን ሰንደቅ ዓላማ ያወድሱ፣ የቆሙላትና ስድቡን ሁሉ
የተሸከሙላት ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ (ነፍሰ ሄር) ብቻ ነበሩ። እዚያ አዳራሽ ውስጥ የነበሩ መንጋ ወሮበሎች ፋሺስቶች ቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ
በመንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የኢትዮጵያን ጉዳይ ሲያሰሙ ያሰማሩባቸውን ሥራ ፈቶችና ማጅራት መችዎችን አስታውሶኝ
ነበር። ይችም አገር ዛሬ (በ21ኛው ክፍለ ዘመን) በዋልጌዎች፣ በጫካ አደጐች፣ በቀማኞች…እጅ እንደገባች ሁላችንም ተከሰተልን። ያን ጊዜ
ከመታኝ ብራቅ እስካሁን አላገገምኩም።
እኛ ኢትዮጵያውያን - ከእኛም በፊት የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ትውልዶች- በነፃነት ተጸንሰን፣ በነፃነት ተወልደን በነፃነትም
ተጠልለን ኖረናል። የሰውን ልጆች እኩልነት የምትመሰክረውን ሰንደቅ ዓላማ፣ የሕዝባችንን የታሪክ ቅሬቶች፣ ሐውልቶችና የነፃነት
ምልክቶች--የክብርና የማዕረግ ሀብቶቻችንን ስንንከባከብ ኖረናል። አገሪቱ ትኖር ዘንድ በሰንደቅ ዓላማቸው ሥር ተንበርክከው የፈጸሙትን
መሐላ ያከበሩትን ጀግኖች በፈንታችን አክብረናቸዋል። በእስዋ ተመርተን ወደ ሞት አደባባዮች ነጉደናል። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ከሁለት መቶ
ሺህ ከማያንስ ሠራዊትና መሪዎቻቸው ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አድዋ ዘምታ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ድል የሆነውን ግዳይ ተወጥታለች።
ይቺ ሰንደቅ ዓላማ እኛ ባለቤትዋ ሆንን እንጂ የዓላም ጭቁን ሕዝቦች ሁሉ አለኝታ ነበረች። ያስረዳሁ ይመስለኛል።
የዚያድ በሬ ወራሪዎች ያሳደዱአት አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የክብርና የአንድነት ምልክታችን በጐዴ፣ በካራማራ፣ በጅጅጋ በገላዲ…እንደገና
ስትውለበለብ አይቻለሁ። በወረራው ወቅት የሶማሊያ እብሪተኛ ኅይል ባደረሰብን ጥቃት የተቃጠለና ያለቀሰ አንጀታችን ሰንደቅ ዓላማችን
ዳግመኛ ስትውለበለብ እንደገና ማልቀሳችን ትዝ ይለኛል። አልፎ አልፎ እንደዚያ ያለ ጥቃት አይጠላም። ለነፃነትህና ለአንድነትህ ዘወትር
እንደ ቆቅ ተጠንቅቀህ መቆምና መሞት ግዴታ መሆኑን እንዳትረሳ ያስገነዝብሃል።
የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ ሲነሣ - አሁንም ተመስገን ደሳለኝ አነሳብኝና- ከውስጤ አንድ እሳተ ጐመራ መሳይ ነገር ሊፈነዳ ይደርሳል።
ትዝታዎች አሉኝና። በኤርትራ በረሃዎች፣ ቅጥልጥል የሆኑ የመስሐሊት ሸንተረሮች፣ በሰሎሞና፣ በሸኢብ…ከኢትዮጵያ የአንድነት ሠራዊት
ጋር የዘመቱት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰንደቅ ዓላማዎችን ዛሬ ዓይኔን ጨፍኜ አያቸዋለሁ። እዚያው ከሰንደቅ ዓላማው አጠገብ ክንዳቸውን
እየተንተራሱ እየጣሉ የወደቁትን፣ በኋላም ነጭ የሰላም ዓርማ እያውለበለቡ እንኳ በፈሪዎች (ካወርድ የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል
ጠንካራ መልእክት አለው) የተረሸኑት ኅልቁ መሳፍርት የሌላቸው ወገኖቼ ከፊቴ ድቅን ይላሉ። የብዘዎቹን አዛዦች አውቃቸዋለሁ።
ለወረራ የተሰማራ ኅይል የለንም። ይልቁንም የኤርትራን ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ክብርና ነፃነት ለማስጠበቅ፣ እያስጠበቀም ለመሞት በሰንደቅ
ዓላማው “ምሎ” የተመመ ነበር። ተሳስተን ነበር ያለቅነው? ተሳስተን ነበር እንደወጣን የቀረነው - ሬሳችን የአራዊት ሲሣይ - የሆነው- ቀባሪ
ያጣው….? የኤርትራ ሕዝብ ምነው አስቀድሞ ቢነግረን ኖሮ! በአርማጌዶን እንድንገናኝ ቀጠሮ መያዝ እንችላለን።
ከጥንት ጀምሮ- ለእኔ ጥንት ከሰባ ዓመት የማይበልጠው ነው- ከዚች ሰንደቅ ዓላማ ጋር የሚያስተሳስር ታሪክ አለኝ። የራሴ ትንሽ ታሪክ!
ትንሽም ትዝታ። ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ውርስ-አረፍ ልዑልአየሁ የፋሺስቶችን እርግጫና ጡጫ ታስታውሳለች። በዚህ የተነሣ ዘወትር የአገር
ልብስዋ ጥለት በሙሉ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። ይኸ ብቻ አይደለም። በአሥራ አራት ዓመቴ ሁለተኛ ደረጃ ከገባሁ በኋላ ከ17 ዓመት
በፊት ወደ ስደቱ ዓለም እስክዛወር ድረስ በየዓመቱ ጋቢ ፈትላ ትልክልኛለች። ሌሎች ዘመዶቼ ጋቢ አስለምደውኛል። የወይዘሮ ውርሰአረፍ
ጋቢ ግን ሁልጊዜ በአረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ጥለት የደመቀ ነበር። ከአሥራ ሁለት ዓመት በፊት (በሞት ያረፈችበት ዘመን) የመጨረሻውን
ጋቢ ልካልኛለች። ታዲያ ይኽንን ልማዴን ታውቅ የነበረችው ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ይታይሽ ልዑልአየሁ “እቴቴን (ሟች እህታችንን)
እንድታስባት ብዬ በእስዋ ምትክ ጋቢ ልኬልሃለሁ” ብላ ወደዚህ በመጣ ሰው አደራዋን ተወጣችው። አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ
ዓላማ። ይቺኛይቱ እህቴም ወደ ታላቅዋ ዘንድ ሄደች። አላውቅም፥ ይገናኙ አይገናኙ። ለእኔ ግን ሰንደቅ ዓላማዬ ናፍቆቴ ሆኖአል።
ተከናንቤው የምተኛው ጋቢ ባላጣም። (በነገራችን ላይ ውድ ወዳጄ ጐሹ ሞገስ በዚህ ረገድ ረስቶኝ አያውቅም።)
የኢትዮጵያ ድምፅ፣ በኋላ ደግሞ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ከበደ አኒሳ እንደ እናቴ ልጅ የምቆጥረው ነው። በንጉሡ
ዘመን በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ አራት ሰዓት ላይ ይመጣና “ና ቡና ጠጥተን እንመለስ” ይልና ይዞኝ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት በኩል
ይነዳል። ልክ ቤተ መንግሥቱ አጠገብ ስንደርስ እኔም እሱም አንገታችንን አውጥተን ግቢውን እንቃኛለን። ሁለት የሰንደቅ ዓላማ መስቀያ
የብረት ምሰሶዎች አሉ። አንደኛው አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ የሚውለበለብበት ነው። ሁለተኛው (አጠር ያለው) ደግሞ
አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ዓርማ መሐል አንበሳ አለው። ያ የጃንሆይ ሰንደቅ ዓላማ ሲሆን እሳቸው በከተማው ከሌሉ አይውለበለብም። የንጉሠ
ነገሥቱ በከተማው መኖር አለመኖር ምልክት ያ ነበር። ስለዚህ ትንታጉ ጋዜጠኛ ከበደ አኒሣ “ዛሬ ጀንሆይ በአዲስ አበባ ስለሌሉ መንግሥት
በሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” ይልና ወደ ደብረ ዘይት፣ ናዝሬት፣ ሶደሬ ወዘተ እንከንፋለን። ብቻ በየሳምንቱ ከአዲስ አበባ
ለመውጣት ሰበብ የምናደርገው የጃንሆይን ሰንደቅ ዓላማ አለመውለብለብ ይሆንና “መንግስት ከሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” እያልን
እብስ ማለት እንደ ባሕል ተያዘ። በእኛ ዘመን ቡድናችን (የእግር ኳሱ-አለዚያም ጊዮርጊስ) ቢያሸንፍም በደስታ፣ ቢሸነፍም በንዴት
በቢራው ማዝገም የተለመደ ነበር። ስትናደድም ትጠጣለህ፣ ሲከፋህም ትጠጣለህ።
ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን እንደ ወረረች እነ ማርከስ ጋርቪ ሦስት ሺህ ጥቁር ወታደሮች መልምለው በክተት ተጠንቀቅ ላይ ነበሩ። አጤ
ኅይለሥላሴ የእንግሊዝን ጦር እየመሩ በመሄዳቸው ራስ ተፈሪያውያኑ ማርከስ ጋርቪና ራስ መኰንን (ራስታ) ጃንሆይን ተቀይመው
እንደነበረ በወቅቱ ሲወራ ነበር። በጽሑፍም ቆይቶናል። ይቺን አገር- ይህን ሰንደቅ ዓላማዋን- ይህን ጐላ ያለ ታሪክዋን- ወደፊትም
አውስተን የማንጨርሰውን- ትዝታዋን እነዚህ ሳንቀጣቸው ያደጉ፣ በማይምነታቸው የማያፍሩ ደፋሮች ይዘን መጓዙ ራሱ ሕመም ነው።
ኅብረተሰብ ይጠይቀናል። ሰላምን በሰንሰለት፣ ዳቦን በባርነት የሚሸምቱ ሰዎች ዘመን ላይ መድረሳችን ይገርመኛል። ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ
የሚያውቁአትና የሞቱላት ሰንደቅ ዓላማ መደፈር እንደ እብድ አድርጐአቸው እንደነበረ አስታውሳለሁ። ወዲያው ጋዜጠኞች ሰብስበው
ንግግር አድርገው አንድ ብዕር በሽልማት መልክ ሰጡኝ። እኔም ለዚች ሰንደቅ ዓላማ ምን ያህል ታማኝ እንደሆንሁ- የሻለቃ አድማሴን
ቃልም ምን ያህል እንደጠበቅሁ አላውቅም። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ደግሞ ያለ ጠባቂ መሆንዋ እውነት ነው። ያለ እስዋ ነፃነታችን ባዶ መሆኑ
ይሰማኛል። ባለ አምባሻዋን የመለስን ድሪቶ አደራችሁን በምትክነት አናንሳው!
የነፃነት እጦት የሚመሰክረው የሰንደቅ ዓላማ መዋረድና የአገር መደፈር ምን ማለት እንደሆነ ዘላለማዊው ሐዲስ ዓለማየሁ “ትዝታ”
በሚለው መጽሐፋቸው ገልጠውታል። ራስ እምሩ፣ አቶ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ አቶ ይልማ ዴሬሳ…በኢጣልያ ደሴት ታስረው በቆዩበት ጊዜ
የቪክቶር ኢማኑኤል ሳልሳዊ የባሕር ማዶ ቅኝ ግዛት ኅላፊ ራስ እምሩን እንዲያነጋግር ታዝዞ ይሄዳል። ቆፍጣናው መስፍን በመኝታ
ቤታቸው ባለችው አንዲት ወንበር ላይ ተቀምጠዋል። ሰውየው ቆሞ ሲያናግራቸው ይሉኝታ የያዛቸው የእኛ ሰዎች ወንበር ፍለጋ ወደየ
ክፍላቸው ሊሄዱ ሲሉ ራስ እምሩ “ወንበር ልታመጡለት እንዳይሆን፤ እንዳታደርጉት” በማለት ቅኝ ገዥውንና የሀገሩ ባለቤት የሆነውን
ባለሥልጣን አቁመው አነጋገሩት። በኢትዮጵያዊ ክብርና ኩራት እየተደበቡ “ ወዳጄ እኛ ዘንድ ምን አመጣህ?” ይሉታል። እሱም እንደ
ባለስልጣን ሳይሆን እንደ አሽከር ቆሞ “ ግርማዊ የኢጣልያ ንጉሥ ኢማኑኤል ሳልሳዊና የመንግስቱ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ መልካም
ፈቃዳቸው ሆኖ ያለዎትን ሀብት ንብረትዎን፣ ርስትዎንና ሌሎችንም እንደ ገንዘብ ያለውን ሀብትዎን ሊመልሱልዎ ወስነዋል። ስለዚህ
ኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን ሊረከብልዎ የሚወክሉት ሰው ካለ ይነገረውና ይረከብልዎ!” ይላቸዋል።
የራስ እምሩ ቃል ለሰውየውም እዚያ ላሉትም አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምርኮኞች እስደንጋጭ ሆነባቸው። ባልተጠበቀው መልሳቸው ራስ
እምሩ “የእኔ ሀብትና ንብረት የቀረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በተደፈረ- አገሬ በእናንተ በተረገጠች ጊዜ ነው። አሁን ሀብትና ንብረት
የለኝም። ይህን የምትጠቅበውን ሀብትና ንብረት ለምትወድደው ሰው ልትሰጠው ትችላለህ።” ይሉታል። አጭር መልስ። ዲቦኖ፣ ባዶልዩ፣
ዱካ ዳውስታ፣ ግራዚያኒ፣ ፍራንካ..ወዘተ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መርገጣቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ የለኝም። ይልቁን ቀደም
እንዳልሁት ይቺው ሰንደቅ ዓላማ በኤርትራ ምድር እንዲያ ስትከበር በማንም ላይ በምንም ጊዜ ስላደረሱት ጥቃት ብዙም አልሰማንም።
እኛ ኢትዮጵያውያን ግን አምባገነን ሥርዓት አወረድሁ በሚል ግለሰብ ዓርማችን ስትናቅና ስትገፋ ለማየት ችለናል። የት? በጣይቱ ከተማ-
በአዲስ አበባ! ባዕድና ጠላት፣ አስገባሪና ወራሪ የተባሉትም በዚህ ነው። የበላዔ ሰብን፣ የሒትለርንና የስታሊንን፣ የቀያፋን፣ የሔሮድስንና
የጲላጦስን፣ የአስቀሮቱ ይሁዳን….ኅጢአት የደመሰሰ አምላክ ይሁነውና መለስ እንደ ገና ሲያላግጥብን ትልቅዋን ዓርማችንን ቡትቱ
አስመስሎ ከማምጣቱም በላይ “የነፃነት ቻምፒዮን” ሆኖ ተከሰተ። ከቶውንም የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበርን እንደ ማካካሻ ሰጠን። ጥሩ
ተጫውቶአል። እግዜር ይመስገነው በውጭ ያለነው ከሰንደቅ ዓላማችን ጋር አልተለያየንም። እንደኔማ ቢሆን ሰው ሁሉ “ወፈፌ” ወይም
የጀማመረው ካላለኝ በየቦታው ለብሼ ብሔድ ደስታዬ ነበር።
ለእኔ ሰንደቅ ዓላማዬ ሁሉንም ነች። የነፃነት ብሥራት፣ ቀጥ ብሎ ቆሞ በክብር የመንጐራደድ ዋስትናዬ ናት። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ የአፍሪካ
ታጋይ ኅይሎች እየተመለከቱአት ቅኝ አገዛዝን ድባቅ የመቱባት ኅይል ናት። የአፍሪካ አገሮች ወደ ፍጹም አንድነት ይመጡ ዘንድ ታሪካዊ
ጥሪ ያስተላለፈች ናት። ዛሬ ደግሞ ከወደቀችበት ትነሣለች። ሰው ሁሉ ኢትዮጵያን ቢክዳት “ኢየሩሳሌም ሆይ ብከዳሽ ቀኜ ትክዳኝ” ያለው
አምላክዋ ወደ ክብርዋ ይመልሳታል። እንደ ተዋረድን አንቀርም። ወደ ታሪካዊ አንድነታችን በእርግጥ እንመለሳለን። አንዳንድ ደካማ
“ነፍሳት” (አዎን “ነፍሳት”) የሚያናፍሱት መፍረክረክ ከንቱ ከንቱ…ሆኖ ያልፋል። አሜን አሜን!
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
February 26, 2014

Weitere ähnliche Inhalte

Ähnlich wie Bematebua lidagne

ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articlesኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articlesMuhammad Shamsaddin Megalommatis
 
Timeline Political situation in Ethiopia Amharic language, it is mainly up ab...
Timeline Political situation in Ethiopia Amharic language, it is mainly up ab...Timeline Political situation in Ethiopia Amharic language, it is mainly up ab...
Timeline Political situation in Ethiopia Amharic language, it is mainly up ab...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Saudi police in Riyadh clash with migrant workers BBC November 11, 2013
Saudi police in Riyadh clash with migrant workers  BBC  November 11, 2013Saudi police in Riyadh clash with migrant workers  BBC  November 11, 2013
Saudi police in Riyadh clash with migrant workers BBC November 11, 2013Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Yesidetegnamastawesha 131015133004-phpapp02
Yesidetegnamastawesha 131015133004-phpapp02Yesidetegnamastawesha 131015133004-phpapp02
Yesidetegnamastawesha 131015133004-phpapp02haramaya university
 
አህባሽ ማነው : ምንድ ነው ?
አህባሽ ማነው : ምንድ ነው ?አህባሽ ማነው : ምንድ ነው ?
አህባሽ ማነው : ምንድ ነው ?Nuradin Sultan
 
Yehaya amet debdabe/ A letter memories of twenty years ago, Former Ethiopia...
Yehaya amet debdabe/   A letter memories of twenty years ago, Former Ethiopia...Yehaya amet debdabe/   A letter memories of twenty years ago, Former Ethiopia...
Yehaya amet debdabe/ A letter memories of twenty years ago, Former Ethiopia...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
042117 - APPEAL TO INTERNATIONAL GOVERNMENTS (Amharic)
042117 - APPEAL TO INTERNATIONAL GOVERNMENTS (Amharic)042117 - APPEAL TO INTERNATIONAL GOVERNMENTS (Amharic)
042117 - APPEAL TO INTERNATIONAL GOVERNMENTS (Amharic)VogelDenise
 

Ähnlich wie Bematebua lidagne (10)

ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articlesኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
ኦሮሞ እና አማራ በኔ መጣጥፎች አይስማሙም - Oromo and Amhara disagree about my articles
 
Timeline Political situation in Ethiopia Amharic language, it is mainly up ab...
Timeline Political situation in Ethiopia Amharic language, it is mainly up ab...Timeline Political situation in Ethiopia Amharic language, it is mainly up ab...
Timeline Political situation in Ethiopia Amharic language, it is mainly up ab...
 
Saudi police in Riyadh clash with migrant workers BBC November 11, 2013
Saudi police in Riyadh clash with migrant workers  BBC  November 11, 2013Saudi police in Riyadh clash with migrant workers  BBC  November 11, 2013
Saudi police in Riyadh clash with migrant workers BBC November 11, 2013
 
Weyane violates own_constitution
Weyane violates own_constitutionWeyane violates own_constitution
Weyane violates own_constitution
 
Yesidetegnamastawesha 131015133004-phpapp02
Yesidetegnamastawesha 131015133004-phpapp02Yesidetegnamastawesha 131015133004-phpapp02
Yesidetegnamastawesha 131015133004-phpapp02
 
Yesidetegna mastawesha
Yesidetegna mastaweshaYesidetegna mastawesha
Yesidetegna mastawesha
 
Yesidetegnamastawesha/remembrance of the journalist refuge
Yesidetegnamastawesha/remembrance of the journalist refugeYesidetegnamastawesha/remembrance of the journalist refuge
Yesidetegnamastawesha/remembrance of the journalist refuge
 
አህባሽ ማነው : ምንድ ነው ?
አህባሽ ማነው : ምንድ ነው ?አህባሽ ማነው : ምንድ ነው ?
አህባሽ ማነው : ምንድ ነው ?
 
Yehaya amet debdabe/ A letter memories of twenty years ago, Former Ethiopia...
Yehaya amet debdabe/   A letter memories of twenty years ago, Former Ethiopia...Yehaya amet debdabe/   A letter memories of twenty years ago, Former Ethiopia...
Yehaya amet debdabe/ A letter memories of twenty years ago, Former Ethiopia...
 
042117 - APPEAL TO INTERNATIONAL GOVERNMENTS (Amharic)
042117 - APPEAL TO INTERNATIONAL GOVERNMENTS (Amharic)042117 - APPEAL TO INTERNATIONAL GOVERNMENTS (Amharic)
042117 - APPEAL TO INTERNATIONAL GOVERNMENTS (Amharic)
 

Mehr von Ethio-Afric News en Views Media!!

VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capitalAddis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capitalEthio-Afric News en Views Media!!
 
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the... conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...Ethio-Afric News en Views Media!!
 
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethio-Afric News en Views Media!!
 

Mehr von Ethio-Afric News en Views Media!! (20)

The impact of_the_ethiopian oromo_protests 2016
The impact of_the_ethiopian oromo_protests 2016The impact of_the_ethiopian oromo_protests 2016
The impact of_the_ethiopian oromo_protests 2016
 
History of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
History of Ethiopian General Jagema kealo , in AmharicHistory of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
History of Ethiopian General Jagema kealo , in Amharic
 
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...VRIJE UNIVERSITEIT  A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
VRIJE UNIVERSITEIT A political history of the Tigray Pe ople’s Liberation Fr...
 
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capitalAddis ababa master plan  ethiopian government denies dozens killed in capital
Addis ababa master plan ethiopian government denies dozens killed in capital
 
Ethiopia eritrea contradictions 2015
Ethiopia eritrea contradictions 2015Ethiopia eritrea contradictions 2015
Ethiopia eritrea contradictions 2015
 
Thanks/ Misgana
Thanks/ MisganaThanks/ Misgana
Thanks/ Misgana
 
Joint statement on_the_election
Joint statement on_the_electionJoint statement on_the_election
Joint statement on_the_election
 
The ark of the covenant
The ark of the covenant The ark of the covenant
The ark of the covenant
 
Arkofthecovenent
ArkofthecovenentArkofthecovenent
Arkofthecovenent
 
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
CIA, perpetrated by the EPLE-TPLF guerrilla in ERITREA-Tigrai during the year...
 
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the... conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
conversation with Ethiopian PM Meles of Ethiopia Dec 2012, shortly after the...
 
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
Ethiopian economy under EPRDF TPLF 1991-2014
 
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
A Tabot is a consecrated wooden altar slab, made of wood or stone, which symb...
 
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
On the identity_of_pm_meles_zenawi_Eritrea Ethiopian by_negussay_ayele_june07
 
Coment on-ato-girma- seyfu speeches, on x eth pm meles
Coment on-ato-girma- seyfu  speeches, on  x eth pm  melesComent on-ato-girma- seyfu  speeches, on  x eth pm  meles
Coment on-ato-girma- seyfu speeches, on x eth pm meles
 
Moto menesat sene1999
Moto menesat sene1999Moto menesat sene1999
Moto menesat sene1999
 
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...Ethiopian 100 years ruling party Amhara people  Story from where to where And...
Ethiopian 100 years ruling party Amhara people Story from where to where And...
 
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
Human rights watch is dedicated to protecting the human rights of people arou...
 
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
Ethiopian government's management of the media during the ethio eritrea war 1...
 
King of kings yohannes & ethiopian unity 5
King of kings yohannes & ethiopian unity 5King of kings yohannes & ethiopian unity 5
King of kings yohannes & ethiopian unity 5
 

Bematebua lidagne

  • 1. በማተብዋ ልዳኝ - ወድቃ የተነሳችው (ከስንሻው ተገኘ) ወደ ትዝታ ዓለም ወደ ትዝታ ጊዜ በትዝታ ሰረገላ ልወስዳችሁ ነው። እኔ እንኳ በአጻጻፌ አበባዊ ቋንቋ አልወድም። ለማንኛውም ግን አብረን እንድንነጉድ እጋብዛችኋለሁ። ወደ እንግሊዝ አገር! 1953 እ.አ.አ ወደ አንድ የለንደን ስብሰባ አዳራሽ እንገባለን። እንግዶች የነፃነት ታጋዮች ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት የዌስት ኢንዲስ ተወላጅና የዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ንቅናቄ መሪ የሆነው ጆርጅ ፓድሞን በአዳራሹ ውስጥ ፕሪዚደሙን ለብቻ ይዞታል። የእኔንና የእርስዎን ቡጢ (ጭብጥ) የሚያህል ወፍራሙን ትምባሆ (ቶስካኖ) ጐርሶአል። ጐርናና ድምፁ ሰውንም አዳራሹንም የሚቆጣጠር ዓይነት ነው። ከአፉ የሚወጣው ጢስ በአካባቢው አንዳች ዓይነት ጉም ሠርቶአል። በመካከሉ የሚያሰማው ባለ ግርማ የሆነው ሳሉ ለሰውየው ተጨማሪ ክብር አሸክሞታል። “ ክቡራትና ክቡራን! አዳራሹ ተከፍቶ ንግግር የሚያደርጉት የአፍሪካ ነፃነት ንቅናቄ መሪዎች ወደ ውስጥ ይዝለቁ!” ጆርጅ ፓድሞን ትእዛዝ ሰጠ። አዳራሹ ደግሞ ከግድግዳ እስከ ግድግዳ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆአል። በአራቱም ማዕዘናት ቄንጠኛ በሆኑ ረዣዥም ሰንደቆች ላይ ወርቃማና ቀለማማ በሆነ መደብ ላይ በጉልህ የሚታዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዎች አሉ። ትርኢቱ እንባ ካልጋበዘ ስሕተቱ የኔ ነው። ደካማ ጋዜጠኛ ሰነፍ ጸሐፊ…. አዳራሹ ተከፈተ። የማኦማኦ ንቅናቄ መሪ ወጣት የማይመስሉት ጆሞ ኬንያታ ብቅ አሉ። በደረታቸው ላይ የቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ ምስል ያለበት ፒን አድርገዋል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንደ ሻሽ አድርገው በራሳቸው ላይ ጠምጥመውታል። ቀጥል። የጐልድኮስቱ (በኋላ ጋና) የነፃነት ግንባር መሪ ካዋሚ እንኩሩማህ- ፈርጠም ያለ…ደልደል ያለ..ተክለ ሰውነታቸው ጉልህ የሆነ አርበኛ። ሰንደቅ ዓላማውን በሙሉ ለብሰውታል። የጃንሆይን ምስል ደግሞ በግራ ኮታቸው ክሳድ ላይ ሰክተውታል። ሑፍዌ ቩዋኘ (ኮትዲቮር) ሔስቲንግስ ባንዳ (ማላዊ) ወዘተ ተራ በተራ መጡ። ከመካከላቸው ጐፈር በራሳቸው ላይ ያደረጉ….በእጆቻቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ የጃማይካ፣ የደቡባዊ አፍሪካ ታጋዮች ነበሩ። በብዙ ቁጥር። ሁሉም በመንፈስ ኢትዮጵያዊ ነበር። ያ ዘመን ደግሞ በትውልዱ ጃማይካዊ የነበረው ማርከስ ጋርቪ (Black nationalism and Pan-Africanism)ን እንዲሁም የራስ ተፈሪያኒዝምን ፍልስፍና የሚያስፋፋበት ነበር። የሁሉም አገር - ነፃነትዋን ለሺህ ዓመታት አስከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ናት። ዓይናችሁን ጨፍኑና ጊዜን አጣጥፋችሁ ወደዚያ ዘመን (1952-53) ብረሩልኝ። መጀመርያ ስለዚህ ጉዳይ ዴቪድ ሜሬዲት The first dance of freedom ን መጽሐፍ አነበብሁና (በ1985) ወዲያው እጅግ ወዳጄ ለነበሩት ለልጅ ሚካኤል እምሩ አነሳሁባቸው። በወቅቱ በእንግሊዝ አገር ስለነበሩ በግል በትኩረት የሚያውቁት መሆናቸውን አረጋገጡልኝ። ከላይ ያቀረብሁት ዘገባም የማርቲን ሜሬዲትና የልጅ ሚካኤል እምሩ ጭምቅ ሪፖርት ነው። (ልጅ ሚካኤል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ላይ ወደ እንግሊዝ አገር ከሄዱ ተማሪዎች አንዱ ነበሩ።) የወቅቱ ተራማጅ ሁሉ ይህንን በጽሞና ሲከታተል ኋይት ሖል (የእንግሊዝ መንግሥት) በዚያው ሰሞን (1953) በኢትዮጵያና አንድነትዋ ላይ ትልቅ ሴራ ሲያቀጣጥል ነበር። ሊቆራርጠን። አርነስት ቤቪን የተባለው የሌበር ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶማሊያ ነፃ ስትሆን የኢትዮጵያን ኦጋዴን፣ ሪዘርቭድ ኤርያና - ሐውድ እንዲሁም ጅቡቲንና የኬንያን ሰሜናዊ ምዕራብ ግዛት አጠቃልላ ታላቅዋን ሶማሊያ ስትመሠርት በሌላ በኩል ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ ከአለውሀ ባሻገር ያለው መሬት በሙሉ (ማለትም ትግራይና ኤርትራ ተዋህደው ትግራይ ትግርኝ የሚባል አገር ለመፍጠር ሽርጉድ ይዘው ነበር።) lyndon larouche የተባለውና በመደበኛው አስተሳሰብ አክራሪና የተወናበደ የፖለቲካ ነውጠኛ የአገሩን ፖለቲካ ጨረሰና ዛሬ በመላው ዓለም እየደረሰ ያለው ችግር እንግሊዝ ዘርታ ያበቀለችው አድርጐ ነው የሚያቀርበው። ይኽ አይጠረጠርም። በበኩሌ እንደማውቀው እንግሊዙ አርነስት ቤቪን የጀመረውን አይኤም ሌዊስ ካልፈጸምሁት ብሎ እነ በረከት ሀብተ ሥላሴን፣ እነ መለስ ዜናዊን ይዞ ለዓመታት ተንደፋድፎአል። (መለስ በዜግነት ሶማሊያዊ ነበር)- በነገራችን ላይ እነ በረከት ሀብተሥላሴ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ ተወልደው ያደጉባት፣ ተምረው የተሾሙባት ኢትዮጵያ፥ ዓለማቸውን ያዩባት ውብ አዲስ አበባ- ወደ ኢምንትነት እንድትመለስ ሲፍጨረጨሩ እንደ ራስ ተፈሪ ያሉ ሕዝቦች “ቤታችን መግቢያችን (ራስታ የምንላቸው)” በማለት ወደዚያች አገር መጉረፍ ይዘው ነበር። ተመስገን ደሳለኝ ወደ ጐንደር ሄዶ ነበር አሉ። ባዶ እጁን አልተመለሰም። ወያኔ ያነወራት፣ እንደ ተስፋዬ ሐቢሶ ያሉ (በተቆላበት የሚያፈሉ) ሰነፎች የተሳለቁባት፣ በመንፈሳዊና ሕዝባዊ ክብርዋ መለስ ያሾፈባት፣….ወያኔዎች በባዶ እግራቸው የረጋገጡአትና የኮሾሮ (የአምባሻ) መያዣ ያደረጉአት….በእኔ ዕድሜ ጅማሬ ላይ “ወድቃ የተነሳችው” እየተባለች ስትጠቀስ የቆየችው ሰንደቅ ዓላማ በጐንደር ምንኛ ታላቁን ክብርዋን ይዛ - እንዳለችና እንደምትኖር የምሥራቹን ነግሮናል። ብሥራት ነውና ምሥር ብላ! ለዚህ ጽሑፍ ያነሳሳኝ ይኸ ወጣት ጋዜጠኛ ነው። ኢጣሊያ የኤርትራን ደጋማ አውራጃዎች ለመያዝ የቻለችው በ1889ዓ.ም እንደ አ.አ ነው። እዚህ ላይ የንጉሠ ነገሥቱን (አጤ ዮሐንስ) አጐት ራስ ደበብንና በኋላ ጊዜ የራስ ሥዩምን ሴት ልጅ ያገቡትን ደጃዝማች ገብረሥላሴን ማውገዝ ወይስ ማወደስ ይገባ እንደሆነ አላወቅንም እንጂ በእነሱ ድጋፍና መሪነት ነው ኤርትራ የተያዘችው። ዛሬ አኪሩ ዞሮ ባንዳ የሚወደስበትና የሚቀደስበት፣ ወደል ወደል
  • 2. መጽሐፍም በውዳሴ መልክ የሚቀርብበት በመሆኑ ነው ግራ የተጋባነው። አዎን ዓላማዬ በማንም ዜጋ ላይ የፍትሕ ድንጊያ ለመወርወር አይደለም። የእግዜሩን መንገድ ካወቅነው ጸሎታችን “ማረን” እንጂ “አፈራርደን” መሆን የለበትም። ኢትዮጵያን የሚታደጋት የራስዋ የኢትዮጵያ ልጅ መሆን እንደሚገባው ስንነጋገርና ስንስማማ ከቆየን በኋላ ሁሉም ነገር የተለዋወጠ ሆኖአል። ኢትዮጵያውያን አገራቸውንም ራሳቸውንም ማዳን አቅቶአቸው በአገሪቱ የሚጫወቱት ወገኖች የተነሱለትን አጥፊ ዓላማ ለመፈጸም አንዳች እንቅፋት አልገጠማቸውም። በተናጠል መስዋዕትነት የሚከፍሉ ግለሰብ የፖለቲካ ተዋናያውያንና ጋዜጠኞች ደግሞ የሚሞቱለትን ሕዝብ ሊቀሰቅሱ አልቻሉም። ስለሆነም ኢትዮጵያ ያሉአት ልጆች እነዚህ ብቻ ናቸውን? እስከማለት የደረሱ አሉ። “የኢትዮጵያ ልጆች በደማቸውም በአጥንታቸውም ኢትዮጵያን ከእልቂት ለማዳን ካልቻሉ ወዴት ይኬዳል? ወደ ማን ይጮኻል?” ነቢዩ ዳዊት (ልበ አምላክ የሚባለው) ለዚህ አምላክ ራሱ በጆሮው የነገረው ቁም ነገር ነበር ይላሉ መጽሐፉን የሚተረጉሙ ሰዎች። “በልጆችዋ መተማመን ያቃታት፣ ልጆችዋ በግፈኞችና በጨቋኞች ያለቁባት ኢትዮጵያ ናት፤ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር የዘረጋችው” ይሉናል። ተስፋ ከመቁረጥ የመጣ አሳብ አይደለም። የአምላኩንም ሚና እንዳንረሳ ለማሳሰብ ነው። ውዳሴ ማርያምም ባይሆን ጥቂት እግዚኦታ! እንደ ዛሬዋ ጐንደር ሁሉ ጣልያን ኤርትራን ከያዘ በኋላ ለስድሳ ዓመታት የኢትዮጵያ ነፃነት ምልክትና የክብርዋ ዘላለማዊ መግለጫ የሆነችው አረንጓዴ፣ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በደብረ ቢዘን ቤተ ክርስቲያን አናት ላይ ስትውለበለብ ቆይታለች። እግዚአብሔር በቤቱ (ቤተክርስቲያኑ) ላይ ያዋላት ለዚህ ሕዝብ መልእክት ኖሮት ይሆናል በማለት የገዳሙ አበምኔት በ1980 ገልጠውልኛል። በዚያን ዘመን ኤርትራ በጣልያን ሥር ብትወድቅም በየበዓላቱ ሕዝቡ ይዞት የሚወጣው ሰንደቅ- አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። አንድ ኤርትራዊ ሲሞት የአስክሬኑ ሳጥን በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ያሸበርቃል። ሠርጐች ግርማማ የሚሆኑት በዚችው ሰንደቅ ዓላማ ሲንቆጠቆጡ ነው። አብያተ ክርስቲያናት ይኽ ሰንደቅ ዓላማ ተለይቶአቸው አያውቅም። ለብዙ ዓመታት ወደ ኤርትራ ስመላለስ የኖርሁ፣ ሕዝቡን የማውቅና የማከብር ስለነበርሁ ዛሬ ይኽ ወገኔ ከዚያች ከታቦት እኩል ከሚያያትና የሕልውናው ተስፋ ከነበረችው ሰንደቅ ዓላማ ሲለይ ምን ተሰማው? እያልሁ ራሴን እጠይቃለሁ። ወይስ አዲሱ የኤርትራ ትውልድ ይኽንን ቁም ነገር አያውቀውም ነበር? እዚህ ባለሁበት አገር እንደኔው በስደት ላይ የሚገኙ ኤርትራውያን አረጋውያን አውቃለሁ። ለሁሉም እንደ ቀልድ “አዲሱ ሰንደቅ ዓላማ የሚለመድ ነው?” እላቸዋለሁ። በሻዕቢያ ውስጥ ከአሥርና ከአሥራ አምስት ዓመት በላይ መቆየታቸውን የሚነግሩኝ ብዙ ጐበዞችን በየቀኑ አገኛቸዋለሁ። ሁለቱ በአንድ ቀን የአሜሪካ ዜግነት እንዳገኙ ሲነግሩኝ እንደ ቀልድ አድርጌ “አሜሪካዊ ለመሆን ነው ሰላሳ ዓመት የወጋችሁኝ?” እላቸዋለሁ። ኤርትራውያኑ ራሳቸው በአጸፋው “እናንተስ ሰንደቅ ዓላማውን መቸ አስከበራችሁና ነው እኛን የምታሽሟጥጡን?” ሊሉን ይችላሉ። እግዜር ይመስገን የወያኔ ሕግ በማይሰራበት በዋሽንግተን፣ በለንደን፣ በጄኔቫ…በስዊድን…የምናምንባት የእናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንደ ልብ ትውለበለባለች። ስለዚህ ለኤርትራውያን ወገኖቻችንም “የተዋችኋትን ሰንደቅ ዓላማ በምትመለሱበት ጊዜም በዚያው ሞገስ ታገኝዋታላችሁ” ለማለት ይቻላል። (የኢትዮጵያ ሕግ በማይሰራባቸው በስዊድን ወዘተ ስል እህታችን ብርቱካን ሚደቅሳ ትዝ ትለኛለች። ለካንስ ስቶክሐልም ላይ የተናገሩት አዲስ አበባ ላይ ያስቀጣል?) ከማንም በላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲያከብር የኖረው የኤርትራ ሕዝብ ነበር ስል ሌላው ሕዝብ ደንታ እንዳልነበረው መግለጤ አይደለም። ግመሎቻችን፣ በጐቻችን፣ የጋማ ከብቶቻችን፣ የቤትና የዱር እንስሶቻችን አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የሆነውን የክብር ዓርማ ያውቁታል እያሉ የሚያወጉአችሁ የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተወላጆች ብዙ ናቸው። የአውሳው ርእሰ መኳንንት ቢተወደድ አሊሚራሕ አንፍሬ በአንድ ወቅት “እንኳን አፋሩ ሕዝባችን ግመሎቻችንም ሰንደቅ ዓላማችንን ያውቁታል” ማለታቸው ይጠቀሳል። አጋጣሚ ነገር ላንሳና ኮማንደር ለማ ጉተማ የሐረርጌ ክፍለ ሀገር ዋና አስተዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ የመሥሪያ ቤቴን ቅርንጫፍ ሥራ ለማስተባበር ወደዚያ እመላለስ ነበር። ሁለት ጊዜ ያህል የኢሳውን ባላባትና ሱልጣን ደጃዝማች ዑጋዝ ሐሰንን ተዋውቄአቸው ነበር። “ትልቁ ልጄን ትመስለኛለህ” ሲሉኝ ልዩ ፍቅር አደረብኝ። ታዲያ በ1983 አካባቢ ቢትወደድ አሊ ሚራሕ የተናገሩትን ቃል በቃል ደጃዝማች (ዑጋዝ) ሐሰን ሲናገሩት ሰምቻቸዋለሁ። ማጋነን ባይመስል ግመሎቹ ቀጥ ብለው እንደሚቆሙ ይናገራሉ። ጐበዝ! “ግመሎቻችን ለኢትዮጵያ ከእኛ የበለጠ ታማኝ ናቸው” ብል በድፍረት ትወስዱብኝ ይሆን? ግመሎቻችን ጭምር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ያውቁታል! እነመለስ ከዚያች ቅርጽ የለሽ እንስሳ ማነሳቸው ከተሰማችሁ አብሬአችሁ ልከሰስ እችላለሁ። ፋሺስቶች ባላደረጉት ድፍረትና ብልግና በቀለም እኛን ይመስል የነበረው መለስ የሕገ መንግሥት ጉባዔ ሲመራ ያቺን ሰንደቅ ዓላማ እንዴት እንዳብጠለጠለ ታስታውሳላችሁ። እዚያ ጉባዔ ውስጥ በጀግንነትና በታላቅ ወኔ ይቺን ሰንደቅ ዓላማ ያወድሱ፣ የቆሙላትና ስድቡን ሁሉ የተሸከሙላት ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ (ነፍሰ ሄር) ብቻ ነበሩ። እዚያ አዳራሽ ውስጥ የነበሩ መንጋ ወሮበሎች ፋሺስቶች ቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ በመንግሥታት ማኅበር (ሊግ ኦፍ ኔሽንስ) የኢትዮጵያን ጉዳይ ሲያሰሙ ያሰማሩባቸውን ሥራ ፈቶችና ማጅራት መችዎችን አስታውሶኝ ነበር። ይችም አገር ዛሬ (በ21ኛው ክፍለ ዘመን) በዋልጌዎች፣ በጫካ አደጐች፣ በቀማኞች…እጅ እንደገባች ሁላችንም ተከሰተልን። ያን ጊዜ ከመታኝ ብራቅ እስካሁን አላገገምኩም። እኛ ኢትዮጵያውያን - ከእኛም በፊት የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ትውልዶች- በነፃነት ተጸንሰን፣ በነፃነት ተወልደን በነፃነትም ተጠልለን ኖረናል። የሰውን ልጆች እኩልነት የምትመሰክረውን ሰንደቅ ዓላማ፣ የሕዝባችንን የታሪክ ቅሬቶች፣ ሐውልቶችና የነፃነት
  • 3. ምልክቶች--የክብርና የማዕረግ ሀብቶቻችንን ስንንከባከብ ኖረናል። አገሪቱ ትኖር ዘንድ በሰንደቅ ዓላማቸው ሥር ተንበርክከው የፈጸሙትን መሐላ ያከበሩትን ጀግኖች በፈንታችን አክብረናቸዋል። በእስዋ ተመርተን ወደ ሞት አደባባዮች ነጉደናል። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ከሁለት መቶ ሺህ ከማያንስ ሠራዊትና መሪዎቻቸው ጋር ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አድዋ ዘምታ ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ድል የሆነውን ግዳይ ተወጥታለች። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ እኛ ባለቤትዋ ሆንን እንጂ የዓላም ጭቁን ሕዝቦች ሁሉ አለኝታ ነበረች። ያስረዳሁ ይመስለኛል። የዚያድ በሬ ወራሪዎች ያሳደዱአት አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የክብርና የአንድነት ምልክታችን በጐዴ፣ በካራማራ፣ በጅጅጋ በገላዲ…እንደገና ስትውለበለብ አይቻለሁ። በወረራው ወቅት የሶማሊያ እብሪተኛ ኅይል ባደረሰብን ጥቃት የተቃጠለና ያለቀሰ አንጀታችን ሰንደቅ ዓላማችን ዳግመኛ ስትውለበለብ እንደገና ማልቀሳችን ትዝ ይለኛል። አልፎ አልፎ እንደዚያ ያለ ጥቃት አይጠላም። ለነፃነትህና ለአንድነትህ ዘወትር እንደ ቆቅ ተጠንቅቀህ መቆምና መሞት ግዴታ መሆኑን እንዳትረሳ ያስገነዝብሃል። የሰንደቅ ዓላማ ጉዳይ ሲነሣ - አሁንም ተመስገን ደሳለኝ አነሳብኝና- ከውስጤ አንድ እሳተ ጐመራ መሳይ ነገር ሊፈነዳ ይደርሳል። ትዝታዎች አሉኝና። በኤርትራ በረሃዎች፣ ቅጥልጥል የሆኑ የመስሐሊት ሸንተረሮች፣ በሰሎሞና፣ በሸኢብ…ከኢትዮጵያ የአንድነት ሠራዊት ጋር የዘመቱት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰንደቅ ዓላማዎችን ዛሬ ዓይኔን ጨፍኜ አያቸዋለሁ። እዚያው ከሰንደቅ ዓላማው አጠገብ ክንዳቸውን እየተንተራሱ እየጣሉ የወደቁትን፣ በኋላም ነጭ የሰላም ዓርማ እያውለበለቡ እንኳ በፈሪዎች (ካወርድ የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል ጠንካራ መልእክት አለው) የተረሸኑት ኅልቁ መሳፍርት የሌላቸው ወገኖቼ ከፊቴ ድቅን ይላሉ። የብዘዎቹን አዛዦች አውቃቸዋለሁ። ለወረራ የተሰማራ ኅይል የለንም። ይልቁንም የኤርትራን ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ክብርና ነፃነት ለማስጠበቅ፣ እያስጠበቀም ለመሞት በሰንደቅ ዓላማው “ምሎ” የተመመ ነበር። ተሳስተን ነበር ያለቅነው? ተሳስተን ነበር እንደወጣን የቀረነው - ሬሳችን የአራዊት ሲሣይ - የሆነው- ቀባሪ ያጣው….? የኤርትራ ሕዝብ ምነው አስቀድሞ ቢነግረን ኖሮ! በአርማጌዶን እንድንገናኝ ቀጠሮ መያዝ እንችላለን። ከጥንት ጀምሮ- ለእኔ ጥንት ከሰባ ዓመት የማይበልጠው ነው- ከዚች ሰንደቅ ዓላማ ጋር የሚያስተሳስር ታሪክ አለኝ። የራሴ ትንሽ ታሪክ! ትንሽም ትዝታ። ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ውርስ-አረፍ ልዑልአየሁ የፋሺስቶችን እርግጫና ጡጫ ታስታውሳለች። በዚህ የተነሣ ዘወትር የአገር ልብስዋ ጥለት በሙሉ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ነበር። ይኸ ብቻ አይደለም። በአሥራ አራት ዓመቴ ሁለተኛ ደረጃ ከገባሁ በኋላ ከ17 ዓመት በፊት ወደ ስደቱ ዓለም እስክዛወር ድረስ በየዓመቱ ጋቢ ፈትላ ትልክልኛለች። ሌሎች ዘመዶቼ ጋቢ አስለምደውኛል። የወይዘሮ ውርሰአረፍ ጋቢ ግን ሁልጊዜ በአረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ጥለት የደመቀ ነበር። ከአሥራ ሁለት ዓመት በፊት (በሞት ያረፈችበት ዘመን) የመጨረሻውን ጋቢ ልካልኛለች። ታዲያ ይኽንን ልማዴን ታውቅ የነበረችው ታላቅ እህቴ ወይዘሮ ይታይሽ ልዑልአየሁ “እቴቴን (ሟች እህታችንን) እንድታስባት ብዬ በእስዋ ምትክ ጋቢ ልኬልሃለሁ” ብላ ወደዚህ በመጣ ሰው አደራዋን ተወጣችው። አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ። ይቺኛይቱ እህቴም ወደ ታላቅዋ ዘንድ ሄደች። አላውቅም፥ ይገናኙ አይገናኙ። ለእኔ ግን ሰንደቅ ዓላማዬ ናፍቆቴ ሆኖአል። ተከናንቤው የምተኛው ጋቢ ባላጣም። (በነገራችን ላይ ውድ ወዳጄ ጐሹ ሞገስ በዚህ ረገድ ረስቶኝ አያውቅም።) የኢትዮጵያ ድምፅ፣ በኋላ ደግሞ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ከበደ አኒሳ እንደ እናቴ ልጅ የምቆጥረው ነው። በንጉሡ ዘመን በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ አራት ሰዓት ላይ ይመጣና “ና ቡና ጠጥተን እንመለስ” ይልና ይዞኝ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት በኩል ይነዳል። ልክ ቤተ መንግሥቱ አጠገብ ስንደርስ እኔም እሱም አንገታችንን አውጥተን ግቢውን እንቃኛለን። ሁለት የሰንደቅ ዓላማ መስቀያ የብረት ምሰሶዎች አሉ። አንደኛው አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ የሚውለበለብበት ነው። ሁለተኛው (አጠር ያለው) ደግሞ አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ ዓርማ መሐል አንበሳ አለው። ያ የጃንሆይ ሰንደቅ ዓላማ ሲሆን እሳቸው በከተማው ከሌሉ አይውለበለብም። የንጉሠ ነገሥቱ በከተማው መኖር አለመኖር ምልክት ያ ነበር። ስለዚህ ትንታጉ ጋዜጠኛ ከበደ አኒሣ “ዛሬ ጀንሆይ በአዲስ አበባ ስለሌሉ መንግሥት በሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” ይልና ወደ ደብረ ዘይት፣ ናዝሬት፣ ሶደሬ ወዘተ እንከንፋለን። ብቻ በየሳምንቱ ከአዲስ አበባ ለመውጣት ሰበብ የምናደርገው የጃንሆይን ሰንደቅ ዓላማ አለመውለብለብ ይሆንና “መንግስት ከሌለበት ከተማ ምን እናደርጋለን?” እያልን እብስ ማለት እንደ ባሕል ተያዘ። በእኛ ዘመን ቡድናችን (የእግር ኳሱ-አለዚያም ጊዮርጊስ) ቢያሸንፍም በደስታ፣ ቢሸነፍም በንዴት በቢራው ማዝገም የተለመደ ነበር። ስትናደድም ትጠጣለህ፣ ሲከፋህም ትጠጣለህ። ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን እንደ ወረረች እነ ማርከስ ጋርቪ ሦስት ሺህ ጥቁር ወታደሮች መልምለው በክተት ተጠንቀቅ ላይ ነበሩ። አጤ ኅይለሥላሴ የእንግሊዝን ጦር እየመሩ በመሄዳቸው ራስ ተፈሪያውያኑ ማርከስ ጋርቪና ራስ መኰንን (ራስታ) ጃንሆይን ተቀይመው እንደነበረ በወቅቱ ሲወራ ነበር። በጽሑፍም ቆይቶናል። ይቺን አገር- ይህን ሰንደቅ ዓላማዋን- ይህን ጐላ ያለ ታሪክዋን- ወደፊትም አውስተን የማንጨርሰውን- ትዝታዋን እነዚህ ሳንቀጣቸው ያደጉ፣ በማይምነታቸው የማያፍሩ ደፋሮች ይዘን መጓዙ ራሱ ሕመም ነው። ኅብረተሰብ ይጠይቀናል። ሰላምን በሰንሰለት፣ ዳቦን በባርነት የሚሸምቱ ሰዎች ዘመን ላይ መድረሳችን ይገርመኛል። ሻለቃ አድማሴ ዘለቀ የሚያውቁአትና የሞቱላት ሰንደቅ ዓላማ መደፈር እንደ እብድ አድርጐአቸው እንደነበረ አስታውሳለሁ። ወዲያው ጋዜጠኞች ሰብስበው ንግግር አድርገው አንድ ብዕር በሽልማት መልክ ሰጡኝ። እኔም ለዚች ሰንደቅ ዓላማ ምን ያህል ታማኝ እንደሆንሁ- የሻለቃ አድማሴን ቃልም ምን ያህል እንደጠበቅሁ አላውቅም። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ ደግሞ ያለ ጠባቂ መሆንዋ እውነት ነው። ያለ እስዋ ነፃነታችን ባዶ መሆኑ ይሰማኛል። ባለ አምባሻዋን የመለስን ድሪቶ አደራችሁን በምትክነት አናንሳው!
  • 4. የነፃነት እጦት የሚመሰክረው የሰንደቅ ዓላማ መዋረድና የአገር መደፈር ምን ማለት እንደሆነ ዘላለማዊው ሐዲስ ዓለማየሁ “ትዝታ” በሚለው መጽሐፋቸው ገልጠውታል። ራስ እምሩ፣ አቶ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ አቶ ይልማ ዴሬሳ…በኢጣልያ ደሴት ታስረው በቆዩበት ጊዜ የቪክቶር ኢማኑኤል ሳልሳዊ የባሕር ማዶ ቅኝ ግዛት ኅላፊ ራስ እምሩን እንዲያነጋግር ታዝዞ ይሄዳል። ቆፍጣናው መስፍን በመኝታ ቤታቸው ባለችው አንዲት ወንበር ላይ ተቀምጠዋል። ሰውየው ቆሞ ሲያናግራቸው ይሉኝታ የያዛቸው የእኛ ሰዎች ወንበር ፍለጋ ወደየ ክፍላቸው ሊሄዱ ሲሉ ራስ እምሩ “ወንበር ልታመጡለት እንዳይሆን፤ እንዳታደርጉት” በማለት ቅኝ ገዥውንና የሀገሩ ባለቤት የሆነውን ባለሥልጣን አቁመው አነጋገሩት። በኢትዮጵያዊ ክብርና ኩራት እየተደበቡ “ ወዳጄ እኛ ዘንድ ምን አመጣህ?” ይሉታል። እሱም እንደ ባለስልጣን ሳይሆን እንደ አሽከር ቆሞ “ ግርማዊ የኢጣልያ ንጉሥ ኢማኑኤል ሳልሳዊና የመንግስቱ መሪ ቤኒቶ ሙሶሊኒ መልካም ፈቃዳቸው ሆኖ ያለዎትን ሀብት ንብረትዎን፣ ርስትዎንና ሌሎችንም እንደ ገንዘብ ያለውን ሀብትዎን ሊመልሱልዎ ወስነዋል። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ይህንን ሊረከብልዎ የሚወክሉት ሰው ካለ ይነገረውና ይረከብልዎ!” ይላቸዋል። የራስ እምሩ ቃል ለሰውየውም እዚያ ላሉትም አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ምርኮኞች እስደንጋጭ ሆነባቸው። ባልተጠበቀው መልሳቸው ራስ እምሩ “የእኔ ሀብትና ንብረት የቀረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በተደፈረ- አገሬ በእናንተ በተረገጠች ጊዜ ነው። አሁን ሀብትና ንብረት የለኝም። ይህን የምትጠቅበውን ሀብትና ንብረት ለምትወድደው ሰው ልትሰጠው ትችላለህ።” ይሉታል። አጭር መልስ። ዲቦኖ፣ ባዶልዩ፣ ዱካ ዳውስታ፣ ግራዚያኒ፣ ፍራንካ..ወዘተ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መርገጣቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ የለኝም። ይልቁን ቀደም እንዳልሁት ይቺው ሰንደቅ ዓላማ በኤርትራ ምድር እንዲያ ስትከበር በማንም ላይ በምንም ጊዜ ስላደረሱት ጥቃት ብዙም አልሰማንም። እኛ ኢትዮጵያውያን ግን አምባገነን ሥርዓት አወረድሁ በሚል ግለሰብ ዓርማችን ስትናቅና ስትገፋ ለማየት ችለናል። የት? በጣይቱ ከተማ- በአዲስ አበባ! ባዕድና ጠላት፣ አስገባሪና ወራሪ የተባሉትም በዚህ ነው። የበላዔ ሰብን፣ የሒትለርንና የስታሊንን፣ የቀያፋን፣ የሔሮድስንና የጲላጦስን፣ የአስቀሮቱ ይሁዳን….ኅጢአት የደመሰሰ አምላክ ይሁነውና መለስ እንደ ገና ሲያላግጥብን ትልቅዋን ዓርማችንን ቡትቱ አስመስሎ ከማምጣቱም በላይ “የነፃነት ቻምፒዮን” ሆኖ ተከሰተ። ከቶውንም የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበርን እንደ ማካካሻ ሰጠን። ጥሩ ተጫውቶአል። እግዜር ይመስገነው በውጭ ያለነው ከሰንደቅ ዓላማችን ጋር አልተለያየንም። እንደኔማ ቢሆን ሰው ሁሉ “ወፈፌ” ወይም የጀማመረው ካላለኝ በየቦታው ለብሼ ብሔድ ደስታዬ ነበር። ለእኔ ሰንደቅ ዓላማዬ ሁሉንም ነች። የነፃነት ብሥራት፣ ቀጥ ብሎ ቆሞ በክብር የመንጐራደድ ዋስትናዬ ናት። ይቺ ሰንደቅ ዓላማ የአፍሪካ ታጋይ ኅይሎች እየተመለከቱአት ቅኝ አገዛዝን ድባቅ የመቱባት ኅይል ናት። የአፍሪካ አገሮች ወደ ፍጹም አንድነት ይመጡ ዘንድ ታሪካዊ ጥሪ ያስተላለፈች ናት። ዛሬ ደግሞ ከወደቀችበት ትነሣለች። ሰው ሁሉ ኢትዮጵያን ቢክዳት “ኢየሩሳሌም ሆይ ብከዳሽ ቀኜ ትክዳኝ” ያለው አምላክዋ ወደ ክብርዋ ይመልሳታል። እንደ ተዋረድን አንቀርም። ወደ ታሪካዊ አንድነታችን በእርግጥ እንመለሳለን። አንዳንድ ደካማ “ነፍሳት” (አዎን “ነፍሳት”) የሚያናፍሱት መፍረክረክ ከንቱ ከንቱ…ሆኖ ያልፋል። አሜን አሜን! ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com February 26, 2014